መለኮታዊ የወላጅነት ትምህርቶች
ወላጆች ውድ ልጆቻቸው ወደ ገነት ተመልሰው እንዲሄዱ ለመምራት ከሰማይ አባታቸው ጋር ይተባበራሉ።
ገና አዲስ የተወለደን ህጻን በእቅፋችሁ ውስጥ ይዛችሁ ታውቃላቹ? ከእያንዳንዱ አራስ ልጅ የወላጆቻቸውን ልብ በደስታ ሊሞላ የሚችል ልዩ የፍቅር ማሰሪያን የሚያፈልቅ ብርሃን አለ።1 አንድ ሜክሲኳዊ ጸሃፊ እንዲ ሲል ጽፋል፣ “አዲስ የተወለደ ጨቅላ ህጻን የአባቱን ጣት በትንሽ እጁ ሲጨምቅ ለዘለአለም እንደያዘው ተረድቻለሁ።”2
ወላጅነት በህይወት ውስጥ ካሉት እጅግ በጣም አስደናቂ ተሞክሮዎች ውስጥ አንዱ ነው። ወላጆች ውድ ልጆቻቸው ወደ ገነት ተመልሰው እንዲሄዱ ለመምራት ከሰማይ አባት ጋር ይተባበራሉ።3 ዛሬ፣ የወላጅነት አርአያ የሚሆን ታሪክን እንድንተው የሚረዱን በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኙትን እና በሕይወት ያሉ ነቢያት ያስተማሩትን የወላጅነት መልካም ትምህርቶችን ላካፍል እፈልጋለሁ።
የወንጌል ባህል ወደሆነው ከፍተኛው ስፍራ ላይ መውጣት
ከቤተሰባችን ጋር ወደ ከፍተኛው የወንጌል ባህል ስፍራ ላይ መውጣት አለብን። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳወጁት፦ “ቤተሰቦች ከገነት መመሪያን መቀበል ይገባቸዋል። ወላጆች ከግል ተሞክሮ፣ ፍርሃት ወይም ርኅራኄ በመነሳት ልጆችን በበቂ ሁኔታ መምከር አይችሉም።”4
ምንም እንኳን የባህል ታሪኮቻችን፣ የወላጅነት ስልቶቻችን እና የግል ልምዶቻችን ለወላጅነት ጠቃሚ ሊሆኑ ቢችሉም እነዚህ ችሎታዎች ልጆቻችን ወደ ሰማይ እንዲመለሱ ለመርዳት በቂ አይደሉም። ይበልጥ ከፍ ያለ “የምግባር ስብስብ እና ልምምዶች፣”5 ከልጆቻችን ጋር ይበልጥ “ከፍ ባለ እና ቅድስና በሆነ መንገድ” የምንገናኝበትን የፍቅርና ወደፊት ይሆናሉ ብለን የምንጠብቅባቸው ባህል ማግኘት እንፈልጋለን።6 ፕሬዘደንት ዳልን ኤች. ኦክስ የወንጌልን ባህል እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል፦ “ልዩ የህይወት መንገድ ምግባሮች፣ መሆን አለበት ብለን የምናስባቸው እና የተግባር ስብስቦች ናቸው። … የወንጌል ባህል የሚመጣው ከደህንነት እቅድ፣ ከእግዚአብሔር ትእዛዛት እና በህያዋን ነቢያት አስተምህሮቶች ነው። ቤተሰባችንን በምናሳድግበት መንገድ ወይም የግል ህይወታችንን በምንኖርበት መንገድ ይመራናል።”7
ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህ ወንጌል ባህል ማዕከል ነው። የእምነት ዘር የሚያብብበት የሚሆንበትን አካባቢ ለመፍጠር የወንጌልን ባህል በቤተሰባችን ውስጥ መለማመድ ወሳኝ ነው። ከፍተኛ ስፍራን ለመውጣት ፕሬዘደንት ኦክስ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትምህርቶች ጋር የሚቃረኑ ማናቸውንም የግል ወይም የቤተሰብ ወጎች ወይም ልማዶች እንድንተው”8 ይጋብዙናል። ወላጆች፣ በእኛ በኩል የወንጌልን ባህል ለመመስረት ዓይናፋር መሆን ጠላት በቤታችን ወይም ከዛም ብሶ በልጆቻችን ልብ ውስጥ መሠረተ ቢስነትን እንዲፈጥር ሊፈቅድለት ይችላል።
በቤተሰባችን ውስጥ የወንጌል ባህልን ዋና ባህል ለማድረግ ስንመርጥ፣ ሀያል በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ9 አሁን ላይ ያለው የወላጅነት [የማሳደግ] መንገዶቻችን፣ ወጎቻችን እና ልማዶቻችን የተጣሩ፣ የተስተካከሉ፣ የታነጹ እና የተሻሻሉ ይሆናሉ።
ቤትን የወንጌል ትምህርት ማዕከል አድርጉ
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን ቤት “የወንጌል መማሪያ ማዕከል” መሆን እንዳለበት አስተምረዋል።10 ወንጌልን የመማር አላማ “በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ በጥልቅ እንድንለወጥ እና እነርሱን እንድንመስል እኛን መርዳት ነው።”11 በህይወታችን ውስጥ ይበልጥ ከፍ ያለ የወንጌል ባህልን ለመመስረት ሊረዱን የሚችሉ በነቢያት እና በሐዋርያት የተገለጹ ሶስት ወሳኝ የወላጅነት ሃላፊነቶችን እናስብባቸው።
በመጀመሪያ፦ በነጻነት አስተምሩ
የሰማይ አባት ኢየሱስ ክርስቶስን እና ወንጌሉን በተመለከተ ለአዳም መመሪያን ሰጥታል። “ስለዚህ እነዚህን ነገሮች በነጻ [ለልጆቹ]” እንዲያስተምር አስተምሮታል።12 በሌላ አባባል፣ የሰማይ አባት አዳምን እነዚህን ነገሮች በነጻነት፣ በልግስና እና ያለ ገደብ እንዲያስተምር አስተማረው።13 ቅዱሳት መጻህፍት “አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ስም [እንደ]ባረኩ፣ እና ሁሉንም ነገሮች ለሴቶችና ለወንዶች ልጆቻቸው [እንዳሳወቁ]” ይናገራሉ።14
ትርጉም ያለው ጊዜን ከእነርሱ ጋር ስናሳልፍ ልጆቻችንን በርከት ባለ ሁኔታ እናስተምራለን። እንደ የእጅ ስልክ ወይም ታብሊት የሚጠቀሙበት ጊዜ ያሉ ስሜታዊ ጉዳዮችን በምንወያይ ጊዜ፣ ቤተክርስቲያን እንዲገኝ ያመቻቸችውን መገልገያን በመጠቀም ያለ ገደብ እናስተምራለን።15 ኑ፣ ተከተሉኝን በመጠቀም ቅዱሳት መጻህፍቶችን ከልጆቻችን ጋር ስናጠና እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ አስተማሪው እንዲሆን ስንፈቅድ፣ በነጻነት እናስተምራለን።
ሁለተኛ፦ የደቀመዝሙርነት መልካም አርአያ
በመፅሐፈ ዮሐንስ ውስጥ፣ ብዙ አይሁዶች አዳኙን ስለ ምግባሩ ሲጠይቁት፣ ኢየሱስ ትኩረትን ለእርሱ ምሳሌ ወደሆነው ወደ አባቱ እንዳመራ እናነባለን። እንዳስተማረውም፣ “አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋል።”16 ወላጆች ለልጆቻችን ምን አርአያን ማሳየት ያስፈልገናል? ደቀ መዝሙርትነት።
እንደ ወላጆች፣ ስለ መጀመሪያው ትእዛዝ ስንወያይ እግዚአብሔርን የማስቀደም አስፈላጊነትን ማስተማር እንችላለን፣ ነገር ግን ዓለማዊ ትኩረቶችን ስናስወግድ እና በየሳምንቱ የሰንበትን ቀን ስንቀድስ አርአያ እንሆናለን። ስለሰለስቲያል ትዳር ትምህርት ስናወራ ስለ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች ወሳኝነት ልናስተምር እንችላለን፣ ነገር ግን ቃል ኪዳኖቻችንን ስናከብር፣ የትዳር ጓደኛችንን በማክበር አረአያ እንሆናለን።
ሶስተኛ፦ እንዲተገብሩ ጋብዙ
በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን የልጆቻችን ምስክሮች መሰረት መሆን አለበት፣ እና እነዚህ ምስክርነቶች በእያንዳንዱ ልጅ በግል መገለጥ በኩል መምጣት አለባቸው።17 ልጆቻችንን ምስክራቸውን እንዲገነቡ ለመርዳት፣ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ለመምረጥ ነጻ ምርጫቸውን እንዲጠቀሙ18 እና በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ በህይወታችሁ ሙሉ ለመቆየት እንዲዘጋጁ እናበረታታቸዋለን።19
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ ወንጌሉ ባላቸው ምስክርነት ሃላፊነት እንዲወስዱ፣ ምስክርነትን ለማግኘት እንዲሰሩ፣ እንዲያድግም እንዲንከባከቡት፣ እውነትን እንዲመግቡት እና በማያምኑ የወንድ እና የሴት የውሸት ፍልስፍናዎች እንዳይበክሉት ፕሬዘደንት ኔልሰን የሰጡትን ግብዣ እያንዳንዳቸው ልጆቻችን እንዲቀበሉ ማበረታታት ጥበባዊ ነው።20
ጻድቃዊ፣ አላማ ያለው እና በጥንቃቄ የሚደረግ ወላጅነት
የሰማይ አባታችን እንደ ወላጅ ያለው መለኮታዊ ሃሳብ ለሙሴ በተሰጠው ራዕይ ላይ እንዲታወቅ ተደርጓል፦ “እነሆ፣ የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት ስራዬ እና ክብሬ ይህ ነው።”21 ፕሬዘደንት ኔልሰን ይህንን ጨምረዋል፦ “በዘለአለም ውስጥ ካሉት ሁሉ ታላላቅ በረከቶች ሳትካፈሉ እንዳትቀሩ፣ እግዚአብሔር ነጻነታችሁን ሳይጥስ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል።22
እንደ ወላጆች፣ በልጆቻችን እንክብካቤ ውስጥ የእግዚአብሔር ወኪሎች ነን።23 ልጆቻችን የእርሱን መለኮታዊ ተጽእኖ እንዲሰማቸው የሚያስችል አካባቢን ለመፍጠር የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን።
የሰማይ አባት እኛ እንደ ወላጆች የልጆቻችንን መንፈሳዊ ህይወት ሲገለጥ ለመመልከት በተመልካቾች መቀመጫ ላይ እንድንቀመጥ አልፈለገም። ይህንን ታስቦ የሚደረግን የወላጅነትን ሀሳብ በግል ልምድ ላብራራ። በጓቲማላ በሚገኝ ትንሽ ቅርንጫፍ ውስጥ የመጀመሪያ ክፍል ተሳታፌ ሆኜ ሳለሁ፣ ወላጆቼ ስለየፓትሪያርክ በረከቶች አስፈላጊነት ያስተምሩኝ ጀመር። እናቴ ጊዜ ወስዳ ውድ የሆነውን የፓትሪያርክ በረከትን ሰለየመቀበል ልምዷ አካፈለች። ከየፓትሪያርክ በረከት ጋር ስለሚዛመደው ትምህርት አስተማረችኝ እንዲሁም ቃል ስለተገቡ በረከቶች መሰከረችልኝ። የእርሷ አላማና ጥንቃቄ ባለው የወላጅነት አስተዳደግ የራሴን የፓትሪያርክ በረከት የመቀበል ፍላጎት እንዲኖረኝ አነሳሳኝ።
12 አመቴ እያለ፣ ወላጆቼ ፓትርያርክን ለማግኘት በፍለጋዬ ረዱኝ። እንኖርበት በነበረ አውራጃ ፓትርያርክ ስላንነበረ ይህን ማድረግ አስፈላጊ ነበር። 156 ኪሎ ሜትር (97 ማይል) ርቆ ባለ አውራጃ ውስጥ ወደሚገኝ ፓትርያርክ ተጓዝኩኝ። ፓትርያርኩ ሊባርኩኝ እጃቸውን በጭንቅላቴ ላይ የጫኑበትን በደንብ አስታውሳለሁ። በኃይለኛ የመንፈሳዊ ማረጋገጫ የሰማይ አባቴ እንደሚያውቀኝ ያለ ጥርጣሬ አውቄ ነበር።
ከትንሽ ከተማ ለመጣ ለየ12 አመት ወንድ ልጅ ይህ ለእኔ ሁሉም ነገር ነበር። በእናቴ እና በአባቴ አላማና ጥንቃቄ ባለው ወላጅነት ምክንያት ልቤ በዚያ ቀን ወደ የሰማይ አባቴ ዞረ፣ እናም ለእነርሱ ለዘለአለም አመስጋኝ እሆናለሁ።
የመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እህት ጆይ ዲ. ጆንስ እንዲህ አስተምረዋል፦ “በወንጌል መለወጥ ልጆቻችን ላይ በቀላሉ እስኪደርስ መጠበቅ አንችልም። በአጋጣሚ በወንጌል መለወጥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መርህ አይደለም።”24 የእኛ ፍቅር እና ተነሳሽነት ያላቸው ግብዣዎች፣ ልጆቻችን ነጻ ምርጫቸውን በሚጠቀሙበት መንገድ ላይ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ። ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዲህ ብለው አብራርተው ነበር፦ “ሌላ ምንም ስራ ጻድቃዊ፣ አላማ ያለው እና በጥንቃቄ ከሚደረግ ወላጅነት በላይ የሚበልጥ ስራ የለም።”25
መደምደሚያ
ወላጆች፣ ይህ ዓለም ለልጆቻችን ትኩረት በሚወዳደሩ ፍልስፍናዎች፣ ባህሎች እና ሀሳቦች የተሞላ ነው። በጣም ወቅታዊ የሆኑትን የሚዲያ ቻናሎችን በመጠቀም ታላቁ እና ሰፊው ህንፃ አባላቱ ማን እንደሆኑ በየቀኑ ያስተዋውቃል። “ነገር ግን እግዚአብሔርም በልጁ ስጦታም ይበልጥ የተመረጠውን መንገድ አዘጋጅቷል” ብሎ ነቢዩ ሞሮኒ አስተምሯል።26
በቃል ኪዳኖች አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ስንተባበር እና በልጆቻችን እንክብካቤ የእርሱ ወኪሎች ስንሆን፣ “እናም ልጆቻችን ለኃጢአታቸው ስርየት የትኛውን ምንጭ መመልከት እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ”27 ሀሳባችንን ይቀድሳል፣ ትምህርቶቻችንን ያነሳሳል እና ግብዣዎቻችንን ያስተካክላል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።