ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፳፫


ምዕራፍ ፳፫

የባቢሎን ጥፋት በዳግም ምፅአት የሚኖረው ጥፋት ምልክት ነው—የቁጣና የበቀል ቀን ይሆናል—ባቢሎን (አለም) ለዘለዓለም ትወድቃለች—ኢሳይያስ ፲፫ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

የአሞፅ ልጅ ኢሳይያስ የተመለከተው የባቢሎን ሸክም

ከፍ ባሉ ተራራ ላይ አርማን አቁሙ፣ ድምፃችሁንም ወደ እነርሱ ከፍ አድርጉ፣ ወደ ልዑላት ደጃፍ ይሄዱ ዘንድ ጠቁሙአቸው

ቅዱሳኖቼን አዝዤአለሁ፣ ኃያላኖችንም ጠርቻቸዋለሁ፣ ቁጣዬ በእኔ ታላቅነት በሚደሰቱት ላይ አይደለችምና።

በተራሮቹ ያሉት ህዝቦች ጩኸት እንደ በርካታ ሰዎች ነው፣ ከመጠን በላይ የሚንጫጩ ሀገሮች መንግስታት ተከማችተዋል፣ የሰራዊት ጌታ የጦር ሰራዊቱን ይሰበስባል

እነርሱ፣ አዎን፣ ጌታ እና የእርሱ የቁጣው መሳሪያ ምድርን ሊያጠፋት ከሩቅ ሀገር፣ ከሰማይ ዳርቻም መጥተዋል።

የጌታ ቀን ቀርባለችና አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚገዛ እንደጥፋት ትመጣለች።

ስለዚህ ሁሉም እጆች ይዝላሉ፣ የሁሉም ሰዎች ልብ ትቀልጣለች።

እናም እነርሱ ይፈራሉ፣ ኃይለኛ ህመምና ሀዘንም ይይዛቸዋል፤ አንዱም በሌላው ይደነቃል፤ ፊቶቻቸው በእፍረት እንደነበልባል ይሆናሉ።

እነሆ፣ ጨካኝ በሆነ ቁጣና ከኃይለኛ ንዴት ጋር ምድርን ባድማ ሊያደርጋት የጌታ ቀን ይመጣል፤ ኃጢአተኞችንም ከውስጧ ያጠፋል

የሰማይ ከዋክብትና ህብር ከዋክብቶች ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።

፲፩ እናም ዓለምን በመጥፎ ስራዋ፣ ክፉዎችንም ለግፍ ስራቸው እቀጣለሁየትዕቢተኞችንም ኩራት አስቆማለሁ፣ የጨካኞችንም ኩራት አዋርዳለሁ።

፲፪ ሰውንም ከነጠረ ወርቅ የበለጠ የከበረ አደርገዋለሁ፤ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።

፲፫ ስለዚህ፣ በሰራዊት ጌታ መዐት እናም በታላቁ ቁጣው ቀን እኔ ሰማያትን አናውጣለሁ ምድርንም ከቦታዋ ፈቀቅ አደርጋታለሁ።

፲፬ እናም እንደሚሳደድ ድብ፣ ማንም ሰው እንደማይሰበስባቸው በጎች ይሆናሉ፤ እናም ሁሉም ሰው ወደ ራሱ ህዝብ ይዞራል፣ እናም ሁሉም ወደ ራሱ ምድር ይሸሻል።

፲፭ የሚኮራ ሰው ሁሉ ይወጋል፣ አዎን፣ ከኃጢአተኞች የተቀላቀለ ሰው ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።

፲፮ ልጆቻቸውም በዐይኖቻቸው ፊት ይከሰከሳሉ፤ ቤቶቻቸው ይበዘበዛል፣ ሚስቶቻቸውም ይደፈራሉ።

፲፯ እነሆ፣ ብር እና ወርቅ የማይሹትንና በዚህም የማይደሰቱትን ሜዶናውያንን በላያቸው አስነሳለሁ።

፲፰ ፍላፃዎቻቸውም ወጣቶቻቸውን ይጨፈጭፏቸዋል፤ ለማህፀኑም ፍሬ ምህረት አይኖራቸውም፤ ዐይኖቻቸውም ህፃናትን በህይወት አይተዉም።

፲፱ እናም የመንግስታት ክብር፣ የከለዳውያን ቆንጆ ክቡር የሆነችው ባቢሎን እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደነበረ ትሆናለች።

ለዘለዓለም የሚቀመጥባት አይገኝም፣ ከትውልድ እስከትውልድም የሚኖርባት አይኖርም—አረባውያንም ቢሆኑ ድንኳኑን በዚያ አይተክልም፤ እረኞችም ቢሆኑ እንኳ መንጋቸውን በዚያ አያሰማሩም።

፳፩ ነገር ግን የበረሃ የዱር አራዊት በዚያ ያርፋሉ፤ ሰጎኖችም ቤቶቻቸውን ይሞሉታል፣ ጉጉቶችም በዚያ ይኖራሉ፤ አጋንንትም በዚያ ይጨፍራሉ።

፳፪ እናም የደሴቶቹ አውሬዎች በባዶ ቤቶቻቸውቀበሮዎችም በአስደሳች ስፍራዎቻቸው ይጮሃሉ፤ እናም ጊዜዋ ቀርቧል፣ ቀኗም አይራዘምም። እኔ በፍጥነት አጠፋታለሁና፤ አዎን፣ እኔ ለህዝቦቼ መሃሪ እሆናለሁና፣ ነገር ግን ኃጢአተኞች ይጠፋሉ።