2010–2019 (እ.አ.አ)
የቅዱስነት ወብት
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


12:12

የቅዱስነት ወብት

የሰማይ አባታችን እርሱ ቅዱስ እንደሆነው እኛም ቅዱስ እንሆን ዘንድ የሚያስፈልገውን በሙሉ ሰጥቶናል።

ለዚህ ስብሰባ ስዘጋጅ፣ ልቤ በቅርብም ይሁን በሩቅ ወደተገናኘኋቸው ብዙ ታማኝ እህቶች ይዞራል። ለእኔ፣ እነዚህ በንጉድ ዳዊት የምስጋና መዝሙር ውስጥ፡በደንብ ተገልጸዋል፥ “ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።”1

መልካም ወደሆነው ላይ ልባቸው በሚጓተተው፣ እንደ አዳኝ ለመሆን በሚፈልጉት እህቶች ውስጥ የቅድስና ወብት አይቻለሁ። ነፍሳቸውን፣ ልባቸውን፣ ሀይላቸውን፣ አዕምሮአቸውን፣ እና ጥንካሬአቸውን በሙሉ በየቀኑ በሚኖሩበት መንገድ ለጌታ አቅርበዋል።2 ቅድስና የሚገኘው ትእዛዛትን ለማክበር እና ከእግዚአብሔር ጋረ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ለማክበር በመጣር እና በመታገል ውስጥ ነው። ቅድስና መንፈስ ቅዱስን እንደ መሪያች እንዲሆን ምርጫዎችን ማድረግ ነው።3 የፍጥረት ጸባያችንን መተው እና በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ቅዱሳን መሆን ቅድስና ነው።4 “[የህይወታችን] ጉዳዮች በሙሉ ለጌታ ቅዱስ መሆን አለበት።”5

Tየሰማይ አምላክ የእስራኤል ልጆችን እንዳዘዘው፣ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታርክሱ።”6

ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንደዳስተማሩትሩት፥ “የሰማይ አባታችን ታላቅ ነገሮችን የሚጠብቅ እግዚአብሔር ነው። … እኛ ‘በሰለስቲያል ክብር’ ለመኖር (ት. እና ቃ. 88፥22) እና ‘በፊቱ ለመኖር’ (ሙሴ 6፥57) እንችል ዘንድ ቅዱስ እኛን ቅዱስ የማድረግ እቅድ አለው።”7 የእምነት ስብከት እንደሚገልጸው, “ማንም ሰው የእርሱ ፍጹምነት እና ቅድስና ሳይኖረው የእርሱን ክብር ለመደሰት አይችልም።”8 የሰማይ አባታችን ያውቀናል። ይወደናል፣ እናም እርሱ ቅዱስ እንደሆነው እኛም ቅዱስ እንሆን ዘንድ የሚያስፈልገውን በሙሉ ሰጥቶናል።

የሰማይ አባት ሴቶች ልጆች ነን፣ እናም እያንዳንዳችን መለኮታዊ የቅድስና ውርስ አለን። የሰማይ አባታችን እንዳወጀው፣ “እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም የቅድስና ሰው ነው።”9 በቅድመ ምድር ህይወት አለም ውስጥ፣ የሰማይ አባታችንን አፈቀርን እናም አመለክነው። እንደ እርሱ ለመሆን ፍላጎት አለን። ፍጹም በሆነ የአባት ፍቅር፣ ውድ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ የእኛ አዳኝና ቤዛ እንዲሆን ሰጠ። የቅድስና ሰው ልጅ ነው።10 ስሙ ቅዱስ ነው፣11 “የእዝራኤል ቅዱስ ነው።”12

ለቅድስና ያለን ተስፋ በክርስቶስ ላይ፣ በምህረቱ እና በጸጋው የሚያተኩር ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው እምነት ጋር፣ ኃጢአተኝነትን በሙሉ ለእራሳችን ከካድን13 እና በቅንነት ንስሀ ከገባን፣ ንጹህ፣ እንከን የሌለን ለመሆን እንችላለን። በውሀ ለኃጢያቶች ስርየት እንጠመቃለን። መንፈስ ቅዱስን በክፍት ልብ ስንቀበል ነፍሳችን የተቀደሱ ናቸው። በየሳምንቱ፣ የቅዱስ ቁርባን ስርዓትን እንቀበላለን። ጻድቅ ለመሆን የልብ ፍላጎት ባለው የንስሀ መንፈስ ጋር፣ የክርስቶስ ስምን በራሳችን ላይ ለመውሰድ፣ እርሱን ለማስታወስ፣ እና የእርሱ መንፈስ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር እንዲገኝ ዘንድ የእርሱን ትእዛዛት ለመጠበቅ ፈቃደኛ እንደምንሆን ቃል ገብተናል። ከጊዜ በኋላ፣ ከአብ፣ ከወልድ፣ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ለመሆን ስንጥር፣ የእነርሱ መለኮታዊ ፍጥረት ተካፋዮች እንሆናለን።14

ቅድስና ቃል ኪዳኖቻችንን መጠበቅ ነው።

በእግዚአብሔር ፊት ምግባረ መልካም እና ምስጋና የሚገባው ከሆኑት የሚስቡን የበዙ ፈተናዎች እና ችግሮች እንዳሉ እናውቃለን። ነገር ግን ስጋዊ ህይወታችን ቅድስናን የመምረጥ እድል ይሰጠናል። በአብዛኛው ጊዜ ቃል ኪዳኖቻችንን ለመጠበቅ የምናደርገው መስዋዕቶች ናቸው ቅዱስ የሚያደርጉን።

ኢቫንጀሊን፣ በጋና የምትኖር ወጣት ሴት

በጋና ውስጥ 13 አመቷ በሆነችው ኢቫንጀሊን ፊት ላይ ያየሁት ቅድስና ነው። ቃል ኪዳኗን የምትጠብቅበት አንድ መንገድ እንደ ቢሀይቭ ክፍል ፕሬዘደንት ነበረራትን ጥሪ በማጉላት ነው። ወደ ጓደኞቿ፣ ተሳታፊ ወዳልሆኑት ወጣት ሴቶች ቤት ወላጆቻቸው ወደ ቤተክርስቲያን እንዲመጡ ፈቃድ እንዲሰጧቸው ለመጠየቅ በትሁት ትገልጽ ነበር። ወላጆችም እሁድ ልጆች የቤት ስራቸውን የሚፈጽሙበት ቀን ስለሆነ ይህ አስቸጋሪ እንደሆነ ይነግሯታል። ስለዚህ ኢቫንጀሊን ትሄድና በስራቸው ትረዳቸዋለች፣ እና በጥረቷም ጓደኞቿ በብዛት ወደ ቤተክርስቲያን ለመምጣት ፈቃድ ያገኛሉ።

ከዚህ ጋር የተያያዙትን ቃል ኪዳኖች ከጠበቅን፣ የቅዱስ ክህነት ስርዓቶች ይቀይሩናል፣ ይቀድሱናል፣ እናም ወደ ጌታ ፊት ለመግባት ያዘጋጀናል።15 የእርስ በራስ ሸከምን እንሸከማለን፤ እርስ በራስ እንጠናከራለን። ለደሀዎች፣ ለተራቡት፣ እራቁት የሆኑት፣ እና ለታመሙት መንፈሳዊ እና ጊዜአዊ እርዳታ ስንሰጥ ለኃጢያቶቻችን ስርየት እናገኛለን።16 የሰንበት ቀንን ስናከብር እና የጌታ ቅዱስ ቀን ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል፣ ራሳችንን ያለእንከን እናደርጋለን።17

ቤተሰባችንን እንባርካለን እናም ቤታችንን የቅዱስ ቦታዎችን እናደርጋለን። በንጹህ እና መጨረሻ በሌለው ፍቅር እንድንሞላ ዘንድ ስሜታችንን እንቆጣጠራለን።18 ሌሎችን በደግነት፣ በርህራሄ፣ እና የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን እንረዳለን። የፅዮን ህዝብ፣ የአንድ ልብና አዕምሮ፣ በአንድነት እና በጻድቅነት አብረው ይሚኖሩ ንጹህ ህዝብ እንሆናለን።19 “ፅዮን በወብት፣ እና በቅድስና፣ ልትልቅ ይገባልና።”20

እህቶች፣ ወደ ቤተመቅደስ ኑ። አዳኝ በሚመለስበት ጊዜ ለመቀበል የተዘጋጀን ቅዱስ ህዝብ ከሆንን፣ መነሳት እና ቆንጆ ልብሳሽንን መልበስ አለብን።21 በጥንካሬና በክብር፣ የአለም መንገድን እናስወግዳለን እና “በንፅህና ተሸፍነን፣ አዎን፣ እንዲሁም በጽድቅ በመጎናፀፊያ”22 ቃል ኪዳኖቻችንን እንጠብቃለን።

ቅድስና የመንፈስ ቅዱስን እንደ መሪያችን መቀበል ነው

ቅድስና የመንፈስ ስጦታ ነው። ይህን ስጦታ የምንቀበለው የሚቀድሰውንየመንፈ ቅዱስ ስጦታ የሚጨምሩትን እነዚያን ነገሮች በህይወታችን ውስጥ ስንቀበል ይህን ስጦታ እንቀበላለን።

ማርያም የአዳኝን ቃላት ሰማች

ማርታ ኢየሱስ ክርስቶስን በቤቷ ስትቀበል፣ በችሎታዋ ያህል ጌታን ለማገልገል ታላቅ ፍላጎት ተሰማት። እህቷ፣ ማርያም፣ “በኢየሱስ እግር ስር” ለመቀመጥ፡እኛ፡ቃሉኝ፡ለማዳመጥ መረጠች። ማርታ ያለእርዳታ ማገልገሉ ሲከብዳት፣ እንዲህ በማለት ቅሬታዋን ተናገረች፣ “ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን?”

ረጋ ያለው የግሰጻ ቃላትን እወዳቸዋለሁ። በፍጹም ፍቅር እና መጨረሻ በሌለው ርህራሄ፣ አዳኝ እንዲህ ገሰጸ፥

“ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥

“የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም።”23

እህቶች፣ ቅዱስ ከሆንን፣ በእዝራኤል ቅዱስ እግር አጠገብ ለመቀመጥ እና ለቅድስና ጊዜ ለመስጠት መማር አለብን። ስልካችንን፣ ለማለቅ የማይችለው የድርጊት ዝርዝር፣ እና የአለማዊነት ሀሳብን በጎን እናደርጋለን? ጸልዩ፣ አጥኑ እና ወደ ነፍሳችሁ የሚያጸዳውን እና የሚፈውስውን ፍቅር የሚያመጣውን የእግዚአብሔርን ቃል አድምጡ። በእርሱ ቅዱስ፣ የሚቀድስ መንፈስ እንሞላ ዘንድ ቅዱስ ለመሆን ጊዜ እንውሰድ። መንፈስ ቅዱስ መሪያችን ሆኖ፣ ቅዳኝን በቅድስና ወብት ለመቀበ እንዘጋጃለን።24

ቅድስና በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ቅዱሳን እንሆናለን

በንጉስ ቢንያም ቃላት መሰረት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ቅዱሳን የሚሆኑት ታዛዥ፣የዋህ፣ ትሁት፣ ትእግዝተኛ፣ እና በፍቅር የተሞሉት ናቸው።25 ስለኢየሱስ ክርስቶስም እንዲህ ተነበየ፣ “በኃይል ሁሉንም የሚገዛው ጌታ የነገሰው፣ የነበረው፣ እናም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ሁሉ የሚኖረው፣ ከሰማይ በሰው ልጆች መካከል የሚመጣበት ጊዜ ይመጣል፣ ሩቅም አይደለም፣ በጭቃ ሰውነቱ ይኖራልም።” የመጣው በስተኞችን፣ ሽባዎችን፣ ደንቆሮዎችን፣ እውሮችን ለመባረክ እና የሞቱትን ለማስነሳት ነበር። ግን “ሰው ሊሰቃይበት ከሚችለው የበለጠም”26 ተሰቃየ። ደህንነት የሚመጣው በእርሱ በኩል ብቻ ቢሆንም፣ እርሱ ተሳልቆበታል፣ ተገርፏል፣ እና ተሰቅሏል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ ሁላችንም ሞትን እናዘንፍ ዘንድ ከመቃብር ተነሳ። አለምን በጻድቅነት የሚፈርደው እርሱ ነው። የሚያድነን እርሱን ነው። እርሱም የእዝራኤል ቅዱስ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የቅድስና ውበት ነው።

የንጉስ ቤንያም ህዝብ እነዚህን ቃላት ሲሰሙ፣ ለአምላካችን ጸጋ እና ክብር ያላቸው ትህትና እና አምልኮ ታላቅ ሆኖ ወደ ምድር ወደቁ። የስጋዊ ጉዳያቸውን አወቁ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ምህረት ላይ እንዴት በፍጹም የተመካን እንደሆንን ተመልክታችኋልን? እያንዳንዱ መልካም ስጦታ፣ ጊዜአዊ እና መንፈሳዊ በክርስቶስ በኩል እንደሚመጣ ትረዳላችሁን? በአብ የዘለአለም እቅድ መሰረት በዚህ ህይወት ሰላም እና በዘለአለም ግርማዎች በቅዱስ ልጁ በኩል የእኛ እንደሚሆኑ ታስታውሳላችሁን?

የንጉስ ቢንያም ህዝብ በታላቅና በአንድ ድምፅ እንዳሉት አብረን እንተባበር፣ “አቤቱ ምህረትን ስጠን፣ እናም ለኃጢአታችን ይቅርታን እናገኝ ዘንድና ልባችን ንፁህ ይሆን ዘንድ የክርስቶስን የደም ክፍያ በእኛ ላይ አድርግ፤ ሰማይና ምድርን እንዲሁም ሁሉንም ነገሮች በፈጠረው በሰው ልጆች መካከል በሚመጣው በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ ኢየሱስ እናምናለንና።”27

ወደ እዝራኤል ቅዱስ እንደምንመጣ፣ በደስታ እንድንሞላ፣ እና የኃጢያቶች ስርየት እና የሰላም ህሊና ዘንድ መንፈሱ በእኛ ላይ እንደሚያርፍ እመሰክራለሁ።

የሰማይ አባት እያንዳንዳችንን ቅዱስ የመሆን ችሎታ ሰጥቶናል። ትእዛዛትን ለማከበር እና መንፈስ ቅዱስን እንደ መሪያችን ለመቀበል የምንችለውን ያህል እናድርግ። በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ፣ በኃጢያት ክፍያው በኩል ቅዱሳን ስንሆን አለሟችነትን እና ዘለአለማዊነትን እንቀበላለን እናም እግዚአብሔር አባታችንን ለስሙ ተገቢ የሆነውን ግርማ እንሰጠዋለን። ህይወታችን ቅዱስ በኩራት የሚሆነው ጌታን በቅድስና ወብት ስናመልክ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።