2010–2019 (እ.አ.አ)
ሁለት ታላላቅ ትዕዛዛት
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ሁለት ታላላቅ ተዕዛዛት

ሁለቱንም ታላቅ ትዕዛዛት ለመጠበቅ መሞከር አለብን። እንደዚህ ለማድረግ በህግ እና በፍቅር መሃል ያለውን ቀጭን መንገድ እንራመዳለን።

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውድ እህቶቼ ፤ በመለኮት እንደተመረጡ የዘላለም ቤተሰብ ጠባቂዎች ሰላም እላችኋለሁ። ፕሬዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ይህ ቤተክርስትያን የተመለሰው ቤተሰቦች እንዲመሰረቱ፣ እንዲታተሙ እና ለዘላለም ከፍ እንዲሉ ነው”ብለው አስተምረውናል።1 ይህ ትምህርት ራሳቸውን ሴት እና ወንድ ግብረሰዶማውያን፣ ሁለቱንም ጾታ አፍቃርያን ወይም ጾታ የቀየሩትን በተለምዶ ኤልጂቢቲ ነን ብለው ራሳቸውን ለሚለዩ አስፈላጊ መልዕክት አለው።2 ፕሬዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በተጨማሪም “እርስ በራስ ለመዋደድ የግድ ሁልጊዜ መስማማት አይጠበቅብንም” ብለው አስታውሰውናል።3 እነዚህ ትንቢታዊ ትምህርቶች ለቤተሰብ ውይይት የህጻናትንና የወጣቶችን ጥያቄዎች ለመመለስ አስፈላጊ ናቸው። ለዚህ ታዳሚ ለመናገር በጸሎት መነሳሳትን ፈልጌያለሁ ምክንያቱም በልዪ ሁኔታ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሁሉም በቤተክርስትያን ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በነዚህ ጥያቄዎች ይጋፈጣሉ።

1.

ክርስቶስ ሁለቱ ታላቅ ትዕዛዛት ብሎ ባስተማረው እጀምራለሁ።

“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

“ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

“ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም። ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የምትለው ናት።”4

ይህ እኛ ሁሉንም ሰው እንድንወድ ታዘናል ማለት ነው፤ የኢየሱስ የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ ሁሉም ሰው ባልንጀራችን እንደሆነ ስለሚያስተምር። 5 ነገር ግን ሁለተኛን ትዕዛዝ የመጠበቅ ከፍተኛ ፍላጎታችን የመጀመርያውን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ የሚለውን እንድንረሳ ማድረግ የለበትም፡፡ ያንን ፍቅር የምናሳየው “ትዕዛዛቱን በመጠበቅ“ ነው።6 እግዚአብሔር ትዕዛዛቱን እንድንጠብቅ የሚፈልገው በዚያ ታዛዥነት ብቻ ንስሃን ጨምሮ እሱ ወደሚገኝበት ተመልሰን መኖር እና እንደሱ ፍጹም መሆን ስለምንችል ነው።

በቅርቡ በቢ.ዋይ.ይው ባደረገው ንግግር ፕረዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “በእግዚአብሔር ፍቅር እና በህጎቹ መሃል ያለው ግንኙነት“7 ብሎ ስለጠራው አውርቶ ነበር። የእግዚአብሔር የጋብቻ ህግ እና አብሮት ያለው የንጽህና ህግ ራሳቸውን ኤል.ጂ.ቢ.ቲ ብለው ከሚለዩ ጋር በደንብ የሚያያዘው ነው። ሁለቱም በሰማይ አባት የማዳን እቅድ ውስጥ ለልጆቹ አስፈላጊ ናቸው። ፕረዝደንት ኔልሰን “ የእግዚአብሔር ህግ መነሻው ለኛ ያለው ገደብ የለሽ ፍቅሩ እና መሆን ምንችለውን ሁሉ መሆን እንድንችል መፈለጉ ነው“ ብለው አስተምረዋል።8

ፕረዝደንት ኔልሰን “ብዙ ሃገሮች … የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ህጋዊ አድርገዋል። እንደ ቤተክርስቲያኗ አባላት የሃገርን ህግ እናከብራለን … ህጋዊ ጋብቻን ጨምሮ። ነገር ግን እውነታው በመጀመርያ … ጋብቻ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው። አሁንም ድረስ በአንድ ሴትና በአንድ ወንድ መካከል እንደሆነ በርሱ ተደንግጓል። እግዚአብሔር ስለጋብቻ ያለውን የእርሱን ፍቺ አልቀየረም።” ብለው አስተምረዋል።

ፕረዝደንት ኔልሰን በመቀጠል “እግዚአብሔር የንጽህናን ህግ አልቀየረም። የቤተመቅደስ መግብያ መስፈርቶች አልተቀየሩም” ብለዋል።9

ፕረዝደንት ኔልሰን ሁላችንንም “እንደ ሃዋርያነት ስልጣናችን እውነትን ብቻ ማስተማር ነው” ብለው አስታውሰውናል። ያ ሃላፊነት መለኮታዊ ህግን እንድንቀይር [ሃዋርያት] ስልጣን አይሰጠንም ። 10 ስለዚህ እህቶቼ የቤትክርስትያን መሪዎች በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል የጋብቻን ልዩ አስፈላጊነት እና የንጽህና ህግ ሁል ጊዜ ማስተማር አለባቸው።

2.

የኋላኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ስራ የእግዚአብሔርን ልጆች ለሴሌስቻል መንግስት በተለይም ለከፍተኛው ክብር ለከፍታ ወይም ለዘላለም ህይወት ማዘጋጀት ነው። ያ ትልቁ እጣ የሚቻለው በዘላለማዊ ጋብቻ ብቻ ነው።11 ዘላለማዊ ህይወት በሴትና በወንድ ጥምረት የመፍጠር — የዘመናችን መገለጥ12”ለዘላለም ዘርን የመቀጠል” የሚለውን 13ሃይልን ያካትታል።

በንግግሩ ፕረዝደንት ኔልሰን “የእግዚአብሔርን ህግ መጠበቅ ወደ መጨረሻው ከፍታ ስትሄዱ ደህንነታችሁን ይጠብቃል” ብለው አስተምረዋል። 14—ያም ከፍ ባለ ህይወት እና በሰማይ ወላጆቻችን መለኮታዊ ሃይል እንደእግዝአብሄር መሆን ነው። ለምንወዳቸው ሁሉ የምንሻው መጨረሻ ያ ነው። በመውደዳችን ምክንያት ለምንወዳቸው ሁሉ ታላቅ ደስታ እንዲያመጣ የምናውቀውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትን እና ስራ እና እቅድ ያ ፍቅር እንዲተካ አንፈቅድም።

ነገር ግን ብዙ የምንወዳቸው አንዳንዶቹ የተመለሰው ወንጌል ያላቸው ፣ አማኝ ያልሆኑ ወይም የእግዚአብሔርን የጋብቻና የንጽህና ህግ ላለመከተል የመረጡ አሉ። እነሱስ?

የእግዚአብሔር ትምህርት ሁላችንም የሱ ልጆች እንደሆንን እና የፈጠረን ደስታን እንድናገኝ እንደሆነ ያሳያል።15 የዘመናችን መገለጥ እግዚአብሔር እሱን ለመታዘዝ በመምረጥ የሱን ታላቅ በረከት የመሻት ወይም ያነሰ ክብር ወዳላቸው መንግስታት የሚመሩ ምርጫዎችን የመምረጥ ምድራዊ ልምምድ አዘጋጅቷል። 16 እግዚአብሔር ለልጆቹ ሁሉ ካለው ታላቅ ፍቅር የተነሳ እነዚያ ያነሱ መንግስታት እንኳን ከምናስበው በላይ አስደናቂ ናቸው።17 የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ ይሄ ሁሉ እንዲቻል አድርጓል ።“አብን የሚያከብር እናምየእጆቹን ስራዎች ሁሉ የሚያድን”ስለሆነ።18

3.

ስለመጀመርያው ትዕዛዝ አውርቻለሁ ነገር ግን ሁለተኛውስ? እንዴት ነው ባለንጀሮቻችንን የመውደድን ህግ የምንጠብቀው? ሴትና ወንድ ግብረሰዶማውያን፣ ሁለቱንም ጾታ አፍቃርያን ወይም የጾታ ለውጥ ትምህርቶችና ተግባሮችን የሚከተሉትን አባሎች ፤ አዳኛችን ሁሉንም ባልንጀሮቻችንን በፍቅር እንድንይዝ እንደሚያዘን አባላቶቻችንን ለማሳመን እንሻለን። ስለዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ህጋዊ ሲደረግ የቀዳሚ አመራር እና የአስራሁለቱ ሸንጎ አባላት እንዲህ አሉ “የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምንም ባንስማማ እንኳን ሁሉንም ሰው እንድንወድ እና በርህራሄ እና በትህትና እንድናይ ያስተምረናል። የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ህጎች ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ተጠቃሚዎች ክብር በጎደለው መልኩ መታየት እንደሌለባቸው እናስረግጣለን። 19

በተጨማሪም እምነታችንን እና ቃልኪዳናችንን የማይከተሉትን በፍጹም መጨቆን የለብንም።20 በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህን ነገሮች የሚጋፈጡ ሰዎች በአንዳንድ አባላትና በቤተሰቦች፣ በቅርንጫፍ እና ካስማ መሪዎች መገለል እና ተቀባይነት ማጣት ይገጥማቸዋል። ሁላችንም ደጎች እና የበለጠ ትሁቶች ለመሆን መጣር አለብን።

4.

በማንረዳው ምክንያቶች ሁላችንም የተለያዩ ችግሮች በጊዜያዊ ህይወታችን ውስጥ ይገጥሙናል ። ነገር ግን በቅንነት የእግዚአብሔርን እርዳታ ከፈለግን እያንዳንዳችን እነዚህን ፈተናዎች እንድናልፍ እንደሚረዳን እናውቃለን። ከመከራና የተማርናቸውን ህጎች መተላለፍ በኋላ ንስሃ ከገባን ክብር ላለው መንግስት እንደምንበቃ ተምረናል። ታላቁ እና የመጨረሻው ፍርድ ብቻውን እኛን ለመዳኘት አስፈላጊው እውቀት፣ ጥበብ እና ጸጋ ባለው በጌታ ይሆናል።

ከዚያ በፊት ሁላችንም ሁለቱን ታላቅ ትዕዛዛት ለመጠበቅ መጣር አለብን። ይህንን ለማድረግ በህግ እና በፍቅር መካከል ባለ ቀጭን መስመር መራመድ አለብን—ትዕዛዛትን በመጠበቅ እና በቃልኪዳን መንገድ በመራመድ በዚያም መንገድ ባለንጀሮቻችንን በመውደድ ነው። ይህ እርምጃ ምን መደገፍ እንዳለብን እና ምን መውደድ እንዳለብን እናም በማክበር እንድናዳምጥ እና በሂደቱም እንድናስተምር ሰማያዊ መነሳሳትን እንድንሻ ይጠይቃል። እርምጃችን ትዕዛዛትን እንዳንጥስ ነገር ግን ሙሉ የሆነ መረዳትንና ፍቅርን እንድናሳይ ይሻል። እርምጃችን ተመሳሳይ ጾታ ፍላጎት አለን ብለው የሚያውጁ ህጻናትን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት። ነገር ግን ያለጊዜው መመደብን ይቃወማል ምክንያቱም በብዙ ልጆች እንደዚህ አይነት ግራ መጋባቶች በጊዜ ብዛት ይቀንሳሉ። 21 እርምጃችን ከቃልኪዳን መንገድ ውጪ መመልመልን ይቃወማል። እናም ከጌታ መንገድ ሰዎችን ለሚያርቅ ነገር ድጋፍ አይሰጥም። በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ትዕዛዛትን ለሚጠብቁ ሁሉ ተስፋን በመጨረሻም ደስታ እና በረከቶችን ቃል እንደገባልን እናስታውሳለን።

5.

እናቶች እና አባቶች እና ሁላችንም ሁለቱን ታላቅ ትዕዛዛት የማስተማር ሃላፊነት አለብን። ለቤተክርስትያኑ ሴቶች ፕረዝደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል በዚህ ታላቅ ትንቢት ዉስጥ ያለውን ሃላፊነት አብራርተዋል። “የመጨረሻ ጊዜያት በቤተክርስቲያን አብዛኛው ዋና እድገቶች የሚመጡት የአለም መልካም ሴቶች … በብዙ ቁጥር ወደ ቤተክርስቲያን ስለሚሳቡ ነው። ይህም የሚሆነው የቤተክርስቲያን ሴቶች በህይወታቸው በሚያንፀባርቁት የቅድስና እና ግልፅነት መጠን እና የቤተክርስቲያን ሴቶች፣ ጎልተው እና ተለይተው፣ …ከአለም ሴቶች ተለይተው እስኪታዩድረስ ነው።” ስለዚህ እነዚህ አርአያ የሆኑ የቤተክርስትያኑ ሴቶች ለቤተክርስትያኑ በኋለኛው ቀን ለቁጥርም ሆነ ለመንፈሳዊ እድገት አስፈላጊ ሃይሎች ይሆናሉ።” 22

ስለዚያ ትንቢት ስናወራ ፕረዝደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ፕሬዘዳንት ኪምቦል አስቀድመው የተመለከቱት ቀን ዛሬ ነው። እናንተ እሱ ቀድሞ የተመለከታቸው ሴቶች ናችሁ!” ብለዋል፡፡23 ከ40 አመት በፊት ይህን ትንቢት የሰማን እኛ የቤተክርስትያኑ ሴቶች በአሁን ሰአት አለምን በማስቀደም እና በሰይጣናዊ መዛባቶች የተጠቁ ጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ከሚያድኗቸው መሃል መሆናቸውን በጥቂቱ ነበር ያውቅነው። ጸሎቴ እና ባርኮቴ ያን ትንቢት ይፈጸም ዘንድ እንድታስተምሩ እና እንድትተገብሩ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፣ አሜን።

አትም