ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፲


ምዕራፍ ፲

ሌሂ አይሁዶች በባቢሎናውያን በምርኮ እንደሚወሰዱ ተነበየ—ከአይሁዶች መካከል መሲህ፣ አዳኝና፣ መድኃኒት እንደሚመጣ ተናገረ—እንዲሁም ሌሂ የእግዚአብሔርን በግ የሚያጠምቀው እንደሚመጣ ተናገረ—ሌሂ የመሲሁን ሞትና ትንሣኤ ተናገረ—እርሱም የእስራኤልን መበተንና መሰባሰብ ከወይራ ዛፍ ጋር አነፃፀረ—ኔፊ ስለእግዚአብሔር ልጅ፣ ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታና፣ ስለፅድቅ አስፈላጊነት ተናገረ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እና አሁን እኔ፣ ኔፊ፣ በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ የእኔን ድርጊትና ንግስና አገልግሎት ታሪኬን በመፃፍ እቀጥላለሁ፤ ስለዚህ፣ በእኔ ታሪክ ለመቀጠል፣ የአባቴን ደግሞም የወንድሞቼን ነገሮች በመጠኑ መናገር አለብኝ።

እነሆም፣ እንዲህ ሆነ አባቴ ስለህልሙ መናገሩን፣ እናም እነርሱን በሙሉ ትጋት መምከር ከጨረሰ በኋላ፣ አይሁዶችን በተመለከተ ተናገራቸው—

እነርሱም ከጠፉ በኋላ፣ እንዲሁም ያቺ ታላቂቷ ከተማ ኢየሩሳሌምና ብዙዎች ሕዝቦቿ በምርኮ ወደ ባቢሎን ከተወሰዱ በኋላ፣ ጌታ በጊዜው መሰረት እንደገና ይመለሳሉ፣ አዎን፣ ከምርኮ ወጥተው ይመለሳሉ፤ እናም ከምርኮም ወጥተው ከተመለሱ በኋላ፣ እንደገናም የርስት ምድራቸው ባለቤት ይሆናሉ።

አዎን፣ አባቴ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ ከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ፣ ጌታ እግዚአብሔር ከአይሁዶች መካከል ነቢይን፣ እንዲሁም መሲሁን ወይም በሌላ አነጋገር የዓለምን መድኃኒት ያስነሳል።

እናም፣ ደግሞ እርሱ ነቢያትን በተመለከተ፣ እርሱ ስለተናገረበት መሲህን ወይም ይህ የአለም አዳኝን በሚመለከት ስለእነዚህ ነገሮች እንዴት ታላቅ ቁጥር ያላቸው እንደመሰከሩ ተናገረ።

ስለዚህ በዚህ መድሐኒት ካልታመኑ በስተቀር ሁሉም የሰው ዘር በመሳትና በውድቀት ላይ ነበሩ፣ እናም ለዘለአለምም ይሆናሉ።

እናም ደግሞ እርሱ ከመሲሁ፣ በፊት የጌታን መንገድ ለማቅናት ስለሚመጣው ነቢይ ተናገረ—

አዎን፣ ወደ ምድረበዳው ሄዶ እንዲህ በማለት ይጮሃል፥ የጌታን መንገድ አቅኑ፣ ጥርጊያውንም አዘጋጁ፣ እናንተ የማታውቁት አንዱ ከመካከላችሁ ቆሟልና፤ እናም እርሱም የጫማውን ጠፍር ለመፍታት ብቁ ያልሆንኩ ከእኔ የበረታ ነው። እናም ይህንን ነገር በተመለከተ አባቴ ብዙ ተናገረ።

እናም አባቴ ከዮርዳኖስ ባሻገር ቤተ ባራ ውስጥ እርሱ እንደሚያጠምቅ ተናገረ፣ ደግሞም እርሱ በውሃ እንደሚያጠምቅ ተናገረ፤ መሲሁንም ቢሆን በውሃ ያጠምቀዋል።

እናም እርሱ መሲሁን በውሃ ካጠመቀ በኋላ፣ የዓለምን ኃጢያት የሚያስወግደውን የእግዚአብሔርን በግ ማጥመቁን እርሱ እንዲሁም ይመሰክራል።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ አባቴ እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ በአይሁዶች መካከል ስለሚሰበከው ወንጌል፣ ደግሞም ስለአይሁዶች እምነት በማጣት መመንመን ለወንድሞቼ ነገራቸው። እናም ዳግም የሚመጣውን መሲሕ ከገደሉ በኋላና እርሱም ከተገደለ በኋላ፣ ከሞት ይነሳል፣ እናም እራሱን በመንፈስ ቅዱስ ለአህዛብ ይገልጣል።

፲፪ አዎን፣ አባቴ አህዛቦችን በሚመለከትና የእስራኤልን ቤት በሚመለከት፣ እነርሱንም ልክ ቅርንጫፎቹ እንደወደበቁት ወይራ ዛፍ በመነፃፀረና በምድር ላይ ሁሉ መበታተን እንደሚገባቸው ብዙ ተናገረ።

፲፫ የጌታ ቃል ይፈፀም ዘንድ፣ በምድር ላይ ሁሉ መበተን አለብን፣ ስለዚህ እኛ ወደ ቃልኪዳኑ ምድር በአንድነት ሆነን መሔድ እንደሚያስፈልገን ተናገረ።

፲፬ እናም የእስራኤል ቤቶች ከተበተኑ በኋላ እንደገና በአንድ ላይ መሰብሰብ አለባቸው፤ ወይም አህዛብ የወንጌልን ሙሉነት ከተቀበሉ በኋላ፣ የወይራው ዛፍ ተፈጥሮአዊ ቅርንጫፎች፣ ወይም በአጠቃላይ የእስራኤል ቤት ቅሪት ይጣበቃሉ፣ ወይም የእነርሱ መድሐኒትና ጌታ ወደሆነው እውነተኛ መሲሕ እውቀት ይመጣሉ።

፲፭ እናም አባቴ በዚህ አይነት አነጋገር ተነበየ፣ እንዲሁም ለወንድሞቼና በዚህ መፅሐፍ ላይ ያልጻፍኳቸውን ሌሎች ብዙ ነገሮች ተናገረ፣ እኔ ግን ለእኔ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች በሌላኛው የራሴ መፅሐፍ ፅፌአለሁ።

፲፮ እናም እነዚህ ሁሉ እኔ የተናገርኳቸው ነገሮች የተደረጉት አባቴ በልሙኤል ሸለቆ በድንኳን ተቀምጦ ሳለ ነበር።

፲፯ እናም እንዲህ ሆነ እኔ፣ ኔፊ የአባቴን ቃላት ሁሉ ከሰማሁ በኋላ፣ እርሱ በራዕይ ስላያቸው ነገሮችና ደግሞ በእግዚአብሔር ልጅ ባለው እምነት በተቀበለው መንፈስ ቅዱስ ኃይል ስለተናገራቸው ነገሮች፤ እናም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጅ መሲሁ ነው፤ እኔም፣ ኔፊ ደግሞ በትጋት እርሱን ለፈለጉት ሁሉ እንደ ጥንት ጊዜው አሁንም ቢሆን እራሱን ለሰው ልጆች በሚገልጥበት በእግዚአብሔር ስጦታ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እነዚህን ነገሮች እመለከት እንዲሁም እሰማና አውቅ ዘንድ ፈለግሁ።

፲፰ እርሱ ትናንትም ዛሬም እስከዘለዓለም ያው ነውና፤ ንስሀ የሚገቡና ወደ እርሱ የሚመጡ ከሆነ፣ መንገዱ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ለሰዎች ሁሉ ተዘጋጅቷል።

፲፱ በትጋት የሚፈልግ ያገኛልና፣ የእግዚአብሔር ሚስጥሮች ለእነርሱ እንደጥንቱም ጊዜ ቢሆን በሚመጡትም ጊዜያት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይገለጥላቸዋል፣ ስለዚህ፣ የጌታ መንገድ አንድ ዘለዓለማዊ ዙሪያ ነው።

ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ አስታውስ፣ ለሥራህ ሁሉ ወደፍርድ ትቀርባለህና።

፳፩ ስለዚህ በሙከራ ዘመንህ መጥፎ ነገሮችን ማድረግ ከፈለግህ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት ሳትፀዳ ትገኛለህ፣ እናም ምንም እርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖር አይቻለውም፣ ስለዚህ ለዘለዓለም ትጣላለህ።

፳፪ እናም መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ነገሮች እናገርና እንዳልደብቃቸው ዘንድ ስልጣን ሰጥቶኛል።