ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፴፮


የአልማ ለልጁ ለሔለማን የሰጠው ትዕዛዛት

ምዕራፍ ፴፮ እስከ ፴፯ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፴፮

አልማ ለሔለማን መላዕክቱን ከተመለከተ በኋላ ስለመለወጡ መሰከረ—ለተኮነነ ነፍስ ስቃይን ተሰቃየ፤ የኢየሱስን ስም ጠራ፣ እናም ከእግዚአብሔር ተወለደ—ጣፋጩ ደስታ ነፍሱን ሞላው—እግዚአብሔርን የሚያወድሱ ብዛት ያላቸው መላዕክትን ተመለከተ—ብዙ የተለወጡ ቀምሰውታል እናም እርሱ እንደተመለከተው መንፈሳዊውን ነገር ተመልክተውታል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ልጄ ሆይ፣ ቃሌን አድምጥ፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስከጠበቅህ ድረስ በምድሪቱ ላይ እንደምትበለፅግ ለአንተ እምላለሁ።

የአባቶቻችንን ምርኮ በማስታወስ እኔ እንዳደረግሁት እንድታደርግ እፈልጋለሁ፤ በምርኮ ስለነበሩ ከአብርሃም አምላክና፣ ከይስሀቅ አምላክ፣ እናም ከያዕቆብ አምላክ በስተቀር ማንም ሊያስለቅቃቸው አይችልም፤ እርሱ በእርግጥ ከስቃያቸው አስለቅቋቸዋል።

እናም አሁን፣ ልጄ ሔለማን ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ወጣት ነህ፣ እናም ስለዚህ፣ ቃሌን እንድትሰማና ከእኔም እንድትማር እለምንሃለሁ፤ እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረጉ ሁሉ፣ በፈተናቸውና፣ በችግራቸው፣ እናም በስቃያቸው እንደሚደገፉና፣ በመጨረሻው ቀን ከፍ እንደሚደረጉ አውቃለሁ።

እናም በራሴ እንደማውቀው እንድታስብ አልፈልግም—በጊዜያዊው ሳይሆን ነገር ግን በመንፈሳዊው፣ በስጋዊ አዕምሮዬ ሳይሆን በእግዚአብሔር ነው።

እንግዲህ፣ እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፥ ከእግዚአብሔር ባልወለድ ኖሮ እነዚህን ነገሮች ባላወቅሁ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር፤ በቅዱስ መልአኩ አንደበት፣ እኔ ብቃት ያለኝ በመሆኔ ሳይሆን፣ እነዚህን ነገሮች እንዳውቅ አድርጎኛል፤

ከሞዛያ ልጆች ጋር የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት በመፈለግ እሄድ ነበርና፤ ነገር ግን እነሆ እግዚአብሔር በመንገዳችን እኛን እንዲያቆመን ቅዱስ መልአኩን ላከ።

እናም እነሆ፣ የነጎድጓድ ድምፅ በሚመስልና፣ ምድር ሁሉ በስራችን እስክትንቀጠቀጥ ተናገረን፤ እናም የጌታ ፍርሃት ስለመጣብን በመሬት ላይ ወደቅን።

ነገር ግን እነሆ፣ ድምፁ እንዲህ አለኝ፥ ተነስ። እናም ተነሳሁና ቆምኩ፣ መልአኩንም ተመለከትኩ።

እናም እርሱ እንዲህ አለኝ፥ ራስህን ለማጥፋት ከፈለግህም፣ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ለማጥፋት አትፈልግ።

እናም እንዲህ ሆነ በመሬት ላይ ወደቅሁ፤ እናም ለሶስት ቀንና ሌሊት አፌን ለመክፈትም፣ ሆነ ክንዶቼን ለመጠቀም አልቻልኩም።

፲፩ እናም መልአኩ ወንድሞቼ ያዳመጡትን፣ ነገር ግን እኔ ላዳምጠው ያልቻልኩትን ከዚህ የበለጡ ነገሮች ተናገረኝ፤ ራስህን ለማጥፋት ከፈለግህም፣ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ከእንግዲህ ለማጥፋት አትፈልግ የሚለውን ቃሉን ስሰማ፣ በታላቁ ፍርሃትና መገረም እጠፋለሁ ብዬ በመፍራቴ፣ በመሬት ላይ ወደቅሁ፣ እናም ሌላ ምንም አልሰማሁም።

፲፪ ነገር ግን በስቃይ ለዘለዓለም ተጨንቄ ነበር፣ ነፍሴ በታላቅ ደረጃ ተጨንቃ፣ እናም በኃጢአቶቼ ሁሉ ተሰቃይታ ነበርና።

፲፫ አዎን፣ በሲኦል ህመም የተሰቃየሁባቸውን፣ ኃጢአቶቼን እናም ክፋቶቼን ሁሉ አስታውሳለሁ፤ አዎን፣ በአምላኬ ላይ ማመፄን፣ እናም ቅዱሳን ትዕዛዛቱን አለመጠበቄን ተመልክቻለሁ።

፲፬ አዎን፣ እናም ብዙዎቹን ልጆቹን ገድያለሁ፣ ይልቁንም ወደጥፋትም እንዲመሩ አድርጌአለሁ፤ አዎን፣ እናም በአጠቃላይ ክፋቶቼ ታላቅ ስለነበሩ፤ ወደ አምላኬ በፊቱ ለመቅረብ ያለኝ ሀሳብ በሚያስቸግር ስቃይ ነፍሴን እንድትሰቃይ አደረጋት።

፲፭ በስራዬም ሊፈረድብኝ በአምላኬ ፊት እንዳልቆ ም ዘንድ፣ ተወግጄ እና በነፍስና በስጋዬ ለመጥፋት እንደምችል አስብበት ነበር።

፲፮ እናም አሁን፣ ለሶስት ቀንና ለሶስት ሌሊት በተኮነነች ነፍስ ህመምም እንኳን ተሰቃየሁ።

፲፯ እናም እንዲህ ሆነ በጭንቀት በተሰቃየሁ ጊዜ፣ በኃጢአቶቼ ብዛትም በትውስታ በተሰቃየሁ ጊዜ፣ እነሆ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተባለው፣ የዓለምን ኃጢያት ለመክፈል ስለሚመጣው፣ የአባቴን ትንቢት መስማቴን አስታወስኩኝ።

፲፰ እንግዲህ፣ አዕምሮዬ በዚህ ሀሳብ ላይ በተያዘበት ጊዜ፣ በልቤ እንዲህ በማለት አለቀስኩ፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሆንከው ኢየሱስ ሆይ፣ ለተማረርኩት፣ እና በዘለዓለማዊው የሞት ሰንሰለት ለተከበብኩት፣ ምህረትህ በእኔ ላይ አድርግልኝ።

፲፱ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ይህንን ባሰብኩ ጊዜ፣ ህመሜን ደግሞ ለማስታወስ አልቻልኩም፤ አዎን፣ ከእንግዲህም ወዲያ በኃጢአቴ ትውስታ አልተሰቃየሁም

እናም አቤቱ፣ እንዴት ያለ ደስታ ተሰማኝ፤ እናም ምን ዓይነት አስደናቂ ብርሃንን አይቻለሁ፤ አዎን፣ ነፍሴ በህመም እንደተሰቃየች ሁሉ ታላቅ በሆነም ደስታ ተሞላች!

፳፩ አዎን፣ ልጄ እንዲህ እልሃለሁኝ፥ እንደ እኔ ህመም ሀያልና መሪር የሆነ ምንም ሊኖር አይችልም። አዎን፣ እናም በድጋሚ ልጄ እንዲህ እልሃለሁ፥ በሌላ መልኩ፣ እንደ እኔ ደስታ ሀያልና ጣፋጭ ሊሆን የሚችል ምንም የለም።

፳፪ አዎን፣ አባታችን ሌሂ እንደተመለከተው እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ ለአምላካቸው በመዘመር እናም በማወደስ ላይ ባሉት ስፍር ቁጥር በሌላቸው መላዕክት ተከቦ የተመለከትኩ መሰለኝ፤ አዎን እናም ነፍሴ በእጅጉ በዚያ ስፍራ መሆንን ናፈቀች።

፳፫ ነገር ግን እነሆ፣ እጆቼና እግሮቼ ብርታትን በድጋሚ አገኙ፣ እናም በእግሬ ቆምኩና፣ ለህዝቡም ከእግዚአብሔር መወለዴን ገለፅኩ።

፳፬ አዎን፣ እናም ከዚያን ጊዜ እስከአሁን ድረስ እንኳን፣ ነፍሳትን ወደ ንስሃ አመጣ ዘንድ፣ እኔ ወደ ቀመስኩት ታላቅ ደስታ እነርሱንም እንዲቀምሱ አመጣቸው ዘንድ፣ እነርሱም ከእግዚአብሔር እንዲወለዱ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ይሞሉ ዘንድ ሳላቋርጥ ሠርቻለሁ።

፳፭ አዎን፣ እናም አሁን እነሆ ልጄ ሆይ፣ ጌታ በስራዬ ፍሬም እጅግ ታላቅ የሆነ ደስታን ይሰጠኛል።

፳፮ እኔ እንዳውቀው ባደረገው ቃል የተነሳ፣ እነሆ ብዙዎች ከእግዚአብሔር ተወልደዋልና፣ እኔ የቀመስኩትን ቀምሰዋል፤ እናም እኔ የተመለከትኩትን ተመልክተዋል፤ ስለዚህ የተናገርኳቸውን ነገሮች እኔ እንደማውቅ ያውቃሉ፤ እናም ያለኝ እውቀት ከእግዚአብሔር ነው።

፳፯ እናም በሁሉም ዓይነት ፈተናና፣ መከራ፣ አዎን፣ በሁሉም ዓይነት ስቃይ ተደግፌአለሁ፤ አዎን፣ እግዚአብሔር ከወህኒ፣ ከእስራትና፣ ከሞት አድኖኛል፤ አዎን፣ እናም እምነቴን በእርሱ አደርጋለሁ፣ አሁንም እኔን ያድነኛል

፳፰ እናም በክብር ከእርሱ ጋር እንድኖር በመጨረሻው ቀን እንደሚያስነሳኝ አውቃለሁ፤ አዎን አባቶቻችንን ከግብፅ ስላስወጣናግብፃውያን በቀይ ባህር እንዲሰምጡ ስላደረገ እርሱን ለዘለዓለም አወድሳለሁ፤ እናም በኃይሉ ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር መርቷቸዋል፤ አዎን፣ እናም በተለያዩ ጊዜያት ከባርነትና ከምርኮ አስለቅቋቸዋል።

፳፱ አዎን፣ እናም ደግሞ አባቶቻችንን ከኢየሩሳሌም ምድር አስወጥቷል፤ ደግሞም በዘለዓለማዊው ኃይሉ እነርሱን ከባርነትና ከምርኮ፣ በየጊዜው እስከ አሁን ድረስም እንኳን፣ አስለቅቋል፤ እናም እኔም ሁልጊዜ ምርኮአቸውን አስታውሳለሁ፤ አዎን፣ እናም ደግሞ አንተም ምርኮአቸውን እኔ እንደአደረግሁት ማስታወስ ይገባሀል።

ነገር ግን እነሆ፣ ልጄ፣ ይህ ብቻም አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስከጠበቅህ ድረስ በምድሪቱ እንደምትበለፅግ እኔ እንደማውቀው ማወቅ አለብህ፤ እናም ደግሞ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እስካልጠበቅህ ድረስ ከፊቱ እንደምትወገድ ማወቅ አለብህ። እንግዲህ ይህ በእርሱ ቃል መሰረት ነው።