14. የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ የቀይ ሸክላ ሱቅ
በናቩ፣ ኢለኖይ ውስጥ የሚገኘው እንደገና የተገነባው የጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ የንግድ ቤትና ቢሮ። በናቩ ዘመን ይህ ህንጻ ከሌሎች በሙሉ በላይ አስፈላጊ የሆነ የቤተክርስቲያኗ ህንጻ ነበር። ይህ እንደ አጠቃላይ ሱቅ ያገለግል ብቻ ሳይሆን፣ ይህም የማህብረሰብ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ እና የሀይማኖት ማእከል ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ በሁለተኛው ደረጃ ክፍል ውስጥ ቢሮ ነበረው።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ቤተመቅደሱ ከመፈጸሙ በፊት፣ የንግድ ቤቱ ታላቅ አዳራሽ የመጀመሪያው ሙሉ የመንፈስ ስጦታዎች እንደተሰጡበት የስነስርዓት ክፍል ይጠቀሙበት ነበር። በመጋቢት ፲፯፣ ፲፰፻፵፪ (እ.አ.አ.)፣ ነቢዩ የቤተክርስቲያኗን ሴቶች እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር አደራጃቸው።