የጥናት እርዳታዎች
6. የፒተር ዊትመር ቀዳማዊ ቤት


6. የፒተር ዊትመር ቀዳማዊ ቤት

ፎቶ ፮

ይህ የፍልጥ እንጨት ቤት የፒተር ዊትመር ቀዳማዊን የመጀመሪያ ቤት የሚመስል ነው።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ጆሴፍ ስሚዝ በእዚህ ቦታ የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም ስራውን በሰኔ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) ፈጸመ። በዚህ ቤት አጠገብ ባለው ጫካ ውስጥ፣ ሶስቱ ምስክሮች መልአክ ሞሮኒን እና የወርቅ ሰሌዳዎችን ተመለከቱ። ምስክራቸውም በሚታተሙት የመፅሐፈ ሞርሞን መፅሐፎች ውስጥ በሙሉ ታትመዋል። በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ህጋዊ መደራጀትን ለመመልከቱ ፷ የሚሆኑ ሰዎች በፒተር ዊትመር ቤት ውስጥ ተሰበሰቡ (ት. እና ቃ. ፳)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚገኙት ሀያ ራዕዮች የተቀበሉት በየፒተር ዊትመር ቤት ውስጥ ነበር።