7. የኒውል ኬ ዊትኒ እና ተዋንያን ሱቅ
የኒውል ኬ ዊትኒ የንግድ ቤት በከርትላንድ ውስጥ በደረሱት የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ክፍል ነበረው። ጆሴፍ እና ኤማ በዚህ ቦታ ለአጭር ጊዜ ኖሩ። ብዙ ዋና ራዕዮችም በእዚህ ቦታ ተቀብለው ነበር። ከጥር ፳፬፣ ፲፰፻፴፫ እስከ ሚያዝያ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) አካባቢ ድረስ የነቢያት ትምህርት ቤትም እዚህ ቦታ ውስጥ ነበር።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ነቢዩ ጆሴፍ የጥበብ ቃል (ት. እና ቃ. ፹፱) ራዕይን ተቀበለ። የመፅሐፍ ቅዱስ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ. ስ. ት) አብዛኛው ስራውን የፈጸመው በእዚህ ቦታ ነበር።