17. ወደ ምዕራብ መሰደድ
ከናቩ፣ ኢለኖይ ለቅቆ መውጣት የሚጀመርበት ጊዜ አላማ የነበረው በመጋቢት እና በሚያዝያ መካከል ነበር፣ ነገር ግን ባመጹት ህዝቡ ፍርሀት ምክንያት ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ ቅዱሳን የምስስፒ ወንዝን በመሻገር ስደታቸውን በየካቲት ፬፣ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) እንዲጀምሩ መመሪያ ሰጡ። ፕሬዘደንት ያንግ ለቅዱሳን የሀይማኖት ስጦታዎችን ለማከናወን ወደኋላ ቀሩ እናም እስከ የካቲት መሀከል ድረስ ከናቩ አልወጡም ነበር።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ከመሞቱ በፊት እንዲህ ተነበየ፣ “አንዳንዶቻችሁ ከዚህ ሄዳችሁ መኖሪያን በመመስረት፣ ከተማዎችን በመገንባት እና ቅዱሳን በሮኪ ተራራዎች መካከል ሀይለኛ ህዝቦች እንዲሆኑ ለማድረግ ትረዳላችሁ።” ፲፪ ሺህ የሚሆኑ ቅዱሳን ከየካቲት እስከ መስከረም ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ድረስ ከናቩ ወጡ። ቅዱሳን ከዊንተር ኮርተር ከወጡ በኋላ፣ በአስር፣ ሀምሳ፣ እና መቶ ቡድኖች ተደራጁ፣ እያንዳንዱም በሻምበል ስር ነበሩ (ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፫)። በመስከረም ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ስድስት መድፎች የነበሯቸው ፰፻ የሚሆኑ ሰዎች ናቩን ከበቡ። ከብዙ ቀናት ጦርነት በኋላ፣ የቀሩት ቅዱሳን ህይወታቸውን ለማዳን እና ወንዙን የመሻገር እድል ለማግኘት እራሳቸውን በምርኮነት አሳልፈው ሰጡ። ከአምስት እስከ ስድስት መቶ ወንዶች፣ ሴቶች፣ እና ልጆች ወንዙን ተሻገሩ እናም በወንዙ ዳርም ሰፈሩ። ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ እነዚህን “ደሀ ቅዱሳን” ለማዳን የሚያድኑ ቡድኖችን ከመደገፊያዎች ጋር ላኩላቸው።