9. የከርትላንድ ቤተመቅደስ
የከርትላንድ ቤተመቅደስ የሚገኘው በከርትላንድ፣ ኦሀዮ ውስጥ ነው።
ታላቅ ድርጊቶች፥ የከርትላንድ ቤተመቅደስ በዚህ ዘመን በመጀመሪያ የተገነባ ቤተመቅደስ ነው (ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፲፱፤ ፺፭)። በዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ፣ ጆሴፍ የሰለስቲያል መንግስት ራዕይን አየ (ት. እና ቃ. ፻፴፯)። ይህም በመጋቢት ፳፯፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) ተቀደሰ (ት. እና ቃ. ፻፱)። በሚያዝያ ፫፣ ፲፰፻፴፮፣ ጌታ ታየ እና ለህዝቡ ቃሉን እንደሚገልጽበት ቦታም ቤተመቅደሱን ተቀበለ (ት. እና ቃ. ፻፲፥፩–፲)። በእዚህ ከታየ በኋላ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውደሪ በሙሴ፣ በኤልያ፣ እና በኤልያስ ተጎበኙ፣ ሁሉም አንዳንድ የክህነት ስልጣን ቁልፎችን እና አስፈላጊ መረጃዎችን ሰጧቸው (ት. እና ቃ. ፻፲፥፲፩–፲፮)። በስደት ምክንያት ቅዱሳን ከከርትላንድ በመሸሽ ከመውጣታቸው በፊት ለሁለት አመት ቤተመቅደሱ አገለገላቸው።