የጥናት እርዳታዎች
4. ግራንዲን የማተሚያ ሱቅ


4. ግራንዲን የማተሚያ ሱቅ

ፎቶ ፬

በ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) የመጀመሪያው የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂ የታተመበት በፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ የሚገኘው እንደገና የተገነባው የኤግበርት ቢ ግራንዲን የማተሚያ ሱቅ። የመፅሐፈ ሞርሞን ፭ ሺህ መፅሐፎች የሚታተሙበትን ገንዘብ ለመክፈል ማርቲን ሀሪስ የእርሻ ቦታውን በብድር አስያዘ እናም አንድ ክፍሉንም ሸጠ። ለማተም ዝግጅቱ የተጀመረው በነሐሴ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) ነበር፣ እናም ታትመው የተፈጸሙት መፅሀፎች ይገኙ የነበሩትም በመጋቢት ፳፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ማርቲን ሀሪስ የመፅሐፈ ሞርሞን ማተሚያ እዳን ለመክፈል ንብረቱን በፈቃደኝነት እንዲሰጥ ታዝዞ ነበር (ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፮–፴፭)።