የጥናት እርዳታዎች
18. የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ


18. የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ

ፎቶ ፲፰

የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ከሰሜን ምስራቅ በኩል ሲታይ። የመጀመሪያዎቹ ፈር ቀዳጆ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ከገቡ በኋላ፣ ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ መሬትን በዱላቸው መትተው እንዲህ አወጁ፣ “በዚህ ቦታ ላይ የእግዚአብሔራችንን ቤተመቅደስ እንገነባለን።” ስራውም በየካቲት ፲፬፣ ፲፰፻፶፫ (እ.አ.አ.) ተጀመረ። በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፶፫ (እ.አ.አ.) የማዕዘን ድንጋዩ ተነጠፈ። ቤተመቅደሱም ከአርባ አመት በኋላ በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፺፫ (እ.አ.አ.) ተፈጸመ እናም ተቀደሰ። ቀዳሚ አመራር እና አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ለመወያየት እና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት እና ለማስተዳደር ከጌታ መመሪያን ለማግኘት በየሳምንቱ በእዚህ ይገናኛሉ።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ከአስተዳደሪያዊ አዋጅ ፪ በተጨማሪ፣ ጌታ የቤተክርስቲያኗን ፕሬዘደንቶች እና አጠቃላይ ባለስልጣኖችን በዚህ ቦታ ላይ የራዕይ መንፈስን አፍስሶላቸዋል። በቅርብም፣ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ በአንድ ድምፅ “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” ተቀብለው አሳትመዋል። ለህያዋን ይሁን ለሙታን የሚከናወነው የቤተመቅደስ ስነስርዓቶች የሚልዮኖችን ህይወቶች ባርከዋል።