15. የናቩ ቤተመቅደስ
ቀዳሚው የናቩ ቤተመቅደስ ግራጫ ነጭ በሆነ በእዚያ አካባቢ በሚገኝ ድንጋይ የተሰራ ነበር። ህንጻው ፴፱ ሜትር ረጅም እና ፳፯ ሜትር ስፋት ያለው ነበር። ማማው ከመሬት ፵፰ ሜትር በላይ ነበር። የቤተክርስቲያኗ አባላት ይህን አስደናቂ ቤተመቅደስ ለመገንባት ታላቅ መስዋእት አደረጉ፣ ስራው የተጀመረውም በ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.) ነበር። አንዳንዶች ለብዙ ወሮች ህንጻውን ለመገንባት ሰሩ፤ ሌሎች ገንዘብን በመስዋዕት ሰጡ። ምንም እንኳን በሙሉ ባይፈጸምም፣ ወደ ምዕራብ ከመሸሻቸው ወሮች በፊት ለስርዓቶች በሚመጡ አባላት እስከሚችለው ድረስ ተሞልቶ ነበር። በአመጽ በተነሳሱ ሰዎች ማስፈራራት ምክንያት ብዙ ቅዱሳን ከናቩ ወጥተው ቢሄዱም፣ ቤተመቅደሱን ለመፈጸም ልዩ ሰራተኞች ወደኋላ ቀርተው ነበር። በሚያዝያ ፴፣ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.)፣ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባላት ሽማግሌዎች ኦርሰን ሀይድ እና ዊልፈርድ ዉድረፍ እና ፳ ሌሎች ይህን የጌታ ቤት ቀደሱ። በመስከረም የቀሩት የቤተክርስቲያኗ አባላት ከናቩ በግድ ሲወጡ ቤተመቅደሱን ትተው ሄዱ፤ ከእዚያም አመጸኛ ሰዎች የተቀደሰ ህንጻውን አረከሱ። ውስጡ የነበረውም በጥቅምት ፲፰፻፵፰ (እ.አ.አ.) በእሳት ተደምስሶ ነበር። እንደገና የተገነባው ቀዳማዊውን የሚመስለው ቤተመቅደስ (በዚህ የሚታየው ፎቶ) ከሰኔ ፳፯–፴፣ ፳፻፪ በፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ ተቀድሶ ነበር።
ታላቅ ድርጊቶች፥ በጥቅምት ፭፣ ፲፰፻፵፭ (እ.አ.አ.) በመሰብሰቢያው ክፍል አጠቃላይ ጉባኤ ነበር። የመንፈስ ስጦታው በታህሳስ ፲ ቀን ፲፰፻፵፭ ተጀምሮ እስከ የካቲት ፯፣ ፲፰፻፵፮ (እ.አ.አ.) ድረስ ቀጠለ። ከ፭ ሺህ ፭፻ የኋለውኛው ቀን ቅዱሳን የመንፈስ ስጦታቸውን ተቀበሉ፣ እናም ብዙ ለሙታን በወኪል መጠመቅ እና መተሳሰርም ተፈጽሞ ነበር።