3. በፍልጥ እንጨት የተሰራ የጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ ቤት
በፓልማይራ፣ ኒው ዮርክ ውስጥ የፍልጥ እንጨት ቤት በመጀመሪያ ተገንብቶበት በነበረው ቦታ ላይ በአምሳያነት የተሰራ የጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ ቤት። የመጀመሪያውን የስሚዝ ቤተሰብ ፩ ተኩል ቤት የሚሆን ከፍልጥ እንጨት ቤት የተሰራው ወደ ፓልማይራ ከገቡ ከአጭር ጊዜ በኋላ ነበር። ቤተሰብ ከ፲፰፻፲፱ እስከ ፲፰፻፳፭ (እ.አ.አ.) ድረስ በዚህ ይኖሩ ነበር።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የትኛው ቤተክርስቲያን ትክክለኛ እንደሆነ ለማወቅ በሚታገልበት ጊዜ በዚህ ቤት ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስን ያጠና ነበር (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፲፩–፲፫)። ሞሮኒ በጆሴፍ ስሚዝ ታየ እናም ስለመፅሐፈ ሞርሞን ሰሌዳዎች ነገርው (ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴–፵፯)።