16. የካርቴጅ እስር ቤት
በካርቴጅ ከተማ፣ ኢለኖይ ውስጥ የነበረ እስር ቤት።
ታላቅ ድርጊቶች፥ በሰኔ ፳፬፣ ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ ስሚዝ እና ወንድሙ ሀይረም ስሚዝ ወደ ካርቴጅ በፈረስ ሄዱ። በሰኔ ፳፭ በሀሰት የአገር መክዳት ክስ ወደ እስር ቤት ተጣሉ። በሰኔ ፳፯ ፊታቸውን ጥቁር ቀለም የቀቡ አመጸኛ ሰዎች እስር ቤቱን ሰብረው ገቡ። ጆሴፍ እና ሀይረም በጥይት ተገደሉ፣ እናም ጆን ቴይለርም ቆሰሉ። በሚያስደንቅ ሁኔታም፣ ዊለርድ ሪቻርድ ግን ምንም አልተጎዱም።