የጥናት እርዳታዎች
8. የጆን ጆንሰን ቤት


8. የጆን ጆንሰን ቤት

ፎቶ ፰

የጆን እና የአሊስ ጆንሰን ቤት የነበረው በሀይረም፣ ኦሀዮ ውስጥ ነበር። ይህም ክፍል በሁለተኛው ደረጃ ላይ የሚገኝ ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ባለቤቱ ኤማ በእዚህ ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር። ጆሴፍ እና ስድኒ ሪግደን በየካቲት ፲፮፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) የክብር ደረጃዎችን አስደናቂ ራዕይ ሌሎች ተሰብስበው በተገኙበት ተቀበሉ (ት. እና ቃ. ፸፮)። ነቢዩ ጆሴፍ ደግሞም በመፅሐፍ ቅዱስ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆስት) ላይ በዚህ ቤት ውስጥ ይሰራ ነበር። በመጋቢት ፳፬ ቀን ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) ምሽት፣ ጆሴፍ እና ኤማ በእዚህ እየኖሩ እያሉ፣ በአመጽ የተነሳሱ ከሀጂዎች እና ጸረ-ሞርሞኖች ጆሴፍንና ስድኒን ደበደቡ እናም በሬንጅ እና በላባ ቀብተው ሸፈኗቸው።