ጆ.ስ.ት.፣ ኢሳይያስ ፵፪፥፲፱–፳፫። ከኢሳይያስ ፵፪፥፲፱–፳፪ ጋር አነጻፅሩ
ጌታ እውነትን ለማየት ወይም ለመስማት ያልመረጡትን ለማስተማር አገልጋዩን ይልካል፤ የሚያዳምጡና የሚታዘዙም ፍጹም ይሆናሉ።
፲፱ ዕውር ወደሆናችሁት፤ አዎን፣ የዕውሩን አይን ለመክፈት፣ እና የደንቆሮውን ጆሮዎች ለመክፈት አገልጋዬን እልክልሀለሁ፤
፳ እና አይነ ስውር ቢሆኑም፣ መልእክተኛውን፣ የጌታን አገልጋይ፣ ካዳመጡ ፍጹም ይሆናሉ።
፳፩ እናንተ ህዝቦች ናችሁ፣ ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትጠባበቁትም፤ ጆሮአችሁም ለመስማት ተከፍተዋል፣ ነገር ግን አትሰሙም።
፳፪ እግዚአብሔር በእንደዚህ አይነት ሰዎች አልተደሰተም፣ ነገር ግን ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርጋል እና የከበር ያደርገዋል።
፳፫ እናንተ የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ናችሁ፤ ጠላቶቻችሁ፣ ሁሉም፣ በዋሻዎች ውስጥ ጠምደዋችኋል፣ እና በእስር ቤትም ሸሽገዋችኋል፤ እንደ አደን አስበዋችኋል፣ እና ማንም አያድንም፤ እንደ ምርኮም፣ እና ማንም ደግሞ ይመለስ አላለም።