የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ኢሳይያስ ፳፱


ጆ.ስ.ት.፣ ኢሳይያስ ፳፱፥፩–፰።ኢሳይያስ ፳፱፥፩–፰ ጋር አነጻፅሩ

በኢየሩሳሌም ከበፊት በጥንት ነቢያት የተሰበከው መልእክት በበኋለኛው ቀናት “ከምድር ውስጥ” በሚመጣው በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ይሰበካል።

ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፤ በዓላትም ይመለሱ።

አርኤልንም አስጨንቃለሁ፥ ልቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ ጌታም እንዲህ ብሎኛል፣ እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።

በዙሪያዋም እሰፍራለሁ፥ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቃታለሁ፥ አምባም በላይዋ አቆማለሁ።

ትዋረዳለች፥ በመሬትም ላይ ሆና ትናገራለች፥ ቃሏም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምጿም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፥ ቃሏም ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል።

ነገር ግን የጠላቶቿ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል፤ አዎን፣ ድንገትም ፈጥኖ ይሆናል።

በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛሉና።

በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል።

አዎን፣ ለእነርሱም ተርቦም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፣ እነሆ፥ ይበላል፥ ነገር ግን ይነቃል ሰውነቱም ባዶ ነው፤ ወይም ተጠምቶም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይጠጣል፥ ነገር ግን ይነቃል፥ እነሆም፥ ይዝላል ሰውነቱም አምሮት አለው፤ አዎን፣ እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።