ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፲፩፥፩–፭። ከመዝሙር ፲፩፥፩–፭ ጋር አነጻፅሩ
በመጨረሻው ቀናት ጻድቃን ወደ ጌታ ተራራ ይሸሻሉ። ጌታ ሲመጣም፣ ክፉውን ያጠፋል እናም ጻድቁን ያቤዛል።
፩ አንተ በምትመጣበት በዚያ ቀን፣ አቤቱ ጌታ፤ እናም እምነቴን በአንተ ላይ እጥላለሁ። ለህዝብህም ትላለህ፣ ጆሮዬ ድምጽህን ሰምቷልና፤ ለእያንዳንዱም ነፍስ ትላለህ፣ ወደ ተራራዬ ሽሹ፤ እናም ጻድቃን ከወፍ ወጥመድ እንደተለቀቀች ወፍ ይሸሻሉ።
፪ ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ፣ መሰረታቸውን ይደመስሱ ዘንድ።
፫ ነገር ግን የክፉ መስረት ይደመሰሳልና፣ እናም ምን ለማድረግ ይችላሉ?
፬ ጌታ ወደተቀደሰው መቅደሱ ሲመጣ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ በሰማይ ተቀምጦ፣ ዓይኖቹ ክፉዎችን ይመረምራሉ።
፭ እነሆ አይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ፣ እናም ጻድቃንን ያድናል፣ እናም እነርሱም ይመረመራሉ። ጌታ ጻድቅን ይወዳል፣ ዓመፃን የወደዳት ኅጥእን ግን ነፍሱን ጠልቶአል።