ጆ.ስ.ት.፣ መዝሙር ፳፬፥፯–፲። ከመዝሙር ፳፬፥፯–፲ ጋር አነጻፅሩ
የክብር ንጉስ በሚመጣበት ጊዜ ህዝቡን ይቤዣቸዋል።
፯ ራሶቻችሁን ከፍ አድርጉ፣ የያዕቆብ ትውልዶች ሆይ፤ እና ወደላይ ከፍ ተደረጉ፤ እና ክብር ንጉስ የሆነው ብርቱና ኃያል ጌታ፣ በሰልፍ ኃያል ጌታ ለዘለአለም ይመሰርታችኋል።
፰ እና ሰማይን ይጠቀልላል፤ እና ህዝቦቹን ለማዳን፣ የዘለአለም ስም ለመስራት፣ በዘለአለም ስለቱ ላይ እንዲመሰርታችሁ ይወርዳል።
፱ ራሶቻችሁን ከፍ አድርጉ፣ የያዕቆብ ትውልድ ሆይ፤ ራሶቻችሁን ከፍ አድርጉ፣ የዘለአለም ትውልዶች ሆይ፤ እና የሰራዊት ጌታ፣ የነገሥታት ንጉሥ፤
፲ እንዲሁም የክብር ንጉስ ወደ እናንተ ይመጣል፤ እና ህዝቦቹን ያድናል፣ እና በጻድቅነትም ይመሰርታቸዋል። ሰላህ