2010–2019 (እ.አ.አ)
ደስታና መንፈስ ደህንነት
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


17:1

ደስታና መንፈስ ደህንነት

የህይወታችን ትኩረት ከኢየሱስ ክርስቶስና ከወንጌሉ ጋር ሲሆን፣ በህይወታችን በተከሰተውም ወይም ባልተከሰተውም ሁኔታ ባሻገር ደስታ ሊሰማን ይችላል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ዛሬ ለመንፈሳዊ ደህናነታችን ቁልፍ ስለሆነ መርህ መናገር እፈልጋለሁ። ይህም መርህ በዙሪያችን ከበውን ያሉ ሃዘኖችና ስህተቶች በሚጨምሩበት ጊዜ በጣም ጠቃሚ ይሆናል።

እነኚህም የኋላኛው ቀናቶች ናቸው፣ ስለዚህም ትንቢቶች ሲፈጸሙ ስንመለከት ማንኛችንም መገረም የለብንም። ብዙ የነቢያት፣ ኢሳያስን፣ ጳውሎስን፣ ኔፊን፣ እናም ሞርሞንንም ጨምሮ፣ አስከፊው ጊዜ እንደሚመጣ፣1 እናም በዘመናችን አለም በጠቅላላ በሁከት ውስጥ እንደምትሆን፣2 ሰዎች “እራሳቸውን የሚወዱ፣ ... ያለምንም ተፈጥሯዊ ፍቅር፣ ... ከእግዚአብሄር ይልቅ ተድላን የሚወዱ” እንደሚሆኑ፣3 እናም አብዛኞቹ የጠላት ስራን የሚያካሂደውን ለሰይጣን አግልጋዮች እንድሚሆኑ አስቀድመው ተመልክተዋል።4 በእርግጥ፣ እኔና እናንተ “መጋደላችን ከዚህም ከጨለማ አለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነው።”5

በሃገራት መሃል አለመግባባት ሲባባስ፣ ፈሪ አሸባሪዎች የዋሆችን ሲያድኑ፣ እናም ሙስናም በሁሉም ከመንግስት እስከ ጉዳዮች ድረስ ውስጥ አብዝቶ የተለመደ ሲሆን፣ እኛን ምን ይረዳናል? በግል ችግሮቻችንና በአስከፊነት አስቸጋሪ በሆኑ በነዚህ የኋለኛው ቀናት ውስጥ ለመኖር እያንዳንዳችንን ምን ሊረዳን ይችላል?

ነቢዩ ሌሂ ለመንፈሳዊ ደህንነት አንድ መርህን አስተማረ። መጀመሪያ የሱን ሁኔታ አስቡ፥ እውነትን በኢየሩሳሌም በመስበኩ እሱ ተሰደደ እናም ንብረቱን ትቶ እንዲሁም ቤተሰቡን ይዞ ወደ ምድረበዳ እንዲሄድ ጌታም አዘዘው። በድንኳንም ውስጥ ኖረ እናም ወዳልታወቀውም መድረሻ በጉዞ ሳለ ባገኘው ምግብ ህይወቱን አቆየ፣ እናም ሁለቱ ልጆቹ፣ ላማንና ልሙኤልን በጌታ ትምህርት ላይ ሲያምጹ እናም ወንድሞቻቸውን ኔፊንና ሳምን ሲያጠቋቸው ተመለከተ።

በግልጽ፣ ሌሂ ተቃርኖን፣ ስጋትን፣ መከፋትን፣ ህመምን፣ ብስጭትን እናም ሃዘንን ጠንቅቆ ያውቃል። ሆኖም፣ በድፍረትና ባለማመንታት ከጌታ የተገለጸውን መርህ አወጀ። “ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው።”6 አስቡት! በዚህ የሟች ህይወት ውስጥ ያለውን የህይወታችንን ተፈጥሮና አላማ ለመግለጽ ለመጠቀም ከሚችላቸው ከሞሉ ሌሎች ቃላቶች ፣ እሱ ግን የመረጠው ቃል ደስታ ነው!

ህይወት በተጠማዘዙና በተዘጉ መንገዶች፣ በፈተናዎችና በሙከራዎች የተሞላች ነች። እያንዳንዳችን መጨነቅና ሃዘን እናም ተስፋም መቁረጥ ሊውጡን ያሉበት ወቅቶች አሉን። ሆኖም እዚህ ያለነው ለደስታ ነውን?

አዎ! መልሱ ስህተት የሌለው አዎ ነው! ነገር ግን እንዴት ነው ያህ የሚቻለው? የሰማይ አባታችን ያስቀመጠልንን ደስታ ለመውሰድ ምን ማድረግ አለብን?

እላይዛ አር. ስኖው፣ ሁለተኛዋ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዝዳንት የነበረችው፣ ተያያዥ መልስን ሰጠች። ባሰቃቂው የ1838 (እ.አ.አ) ክረምት መጀመሪያ ላይ በመውጣቱ7 በምዙሪ አስከፊው የመደምሰስ ህግ ምክንያት፣ እሷና ሌሎች ቅዱሳን በዚያው ክረምት እንዲለቁ ተገደዱ። አንድ ምሽት፣ የእላይዛ ቤተሰብ ስደተኛ ቅዱሳን በሚጠቀሟት ትንሽ የእንጨት ጎጆ ውስጥ ምሽቱን አሳለፉ። ክፍት ቦታውን የሞሉት እንጨቶች አስቀድሞ በኖሩት ነዋሪያን ለእሳት ማንደጃ ተጠቅመውት ለበር፣ በዚህም ምክንያት ድመትን ማስሾለክ የሚችሉ ቀዳዳዎች በእንጨት ግንድ መካከል ነበሩ። በጣም መራራ ብርዳማ ነበር፣ እና ምግባቸውም የበረዶ ድንጋይ ሆነ።

በዛው ምሽት 80 የሚሆኑ ሰዎች 6.1 ሜትር ካሬ በምታህል ጎጆ ውስጥ ተኮራመቱ። አብዛኞቹ ለመሞቅ ሎሊቱን በሙሉ ተቀምጥው ወይም ቆመው አሳለፉ። ውጪ ደግሞ የተወሰኑ ወንዶች የሚልነበነብውን እሳት ከበው፣ አንዳንዶች መዝሙሮችን በመዘመር እና ሌሎች በረዶ የሆኑ ድንቾችን በመጥበስ አሳለፉ። እላይዛ እንደመዘገበችው፥ “አንዳች እንኳ ቅራኔ አልተሰማም—ሁሉም ደስተኞች ነበሩ፣ እናም ገጽታዎችን በማንበብ፣ ለእንግዳዎች ሁኔታችን የመዝናኛ ጉዞ እንጂ በአገረ ገዢ የተሰደድን አንመስልም።”

የዚያ አድካሚ፣ በጣም ቀዝቃዛ ምሽት የነበረው የእላይዛ ዘገባ በሚያስገርም ሁኔታ የተስፋ አመለካከት ያለው ነበር። እሷም እንዳወጀችው፥ “ያ ምሽት የደስታ ምሽት ነበር። ማንም ሳሆን ቅዱሳን ብቻ በማንኛውም ሁኔታ መደሰት ይችላሉ።”8

ይሄ ነው! ቅዱሳን በማንኛውም ሁኔታ መደሰት ይችላሉ። መጥፎ ቀን፣ መጥፎ ሳምንት፣ ወይም መጥፎ አመት እንኳ ቢያጋጥመን ደስታ ሊሰማን እንችላለን።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የሚሰማን ደስታ ካሉን የህይወታችን ሁኔታዎች ጋር የተያያዙበት የቀነሰ ነው እናም የህይወታችን ትኩረት ጋር ያላቸው ዘመዴታ ታላቅ ነው።

የህይወታችን ትኩረት፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን አሁን ባስተማሩን፣ ከእግዚአብሄር የመዳን እቅድ ጋር እና ከኢየሱስ ክርስቶስና ከወንጌሉ ጋር ሲሆን፣ በህይወታችን በተከሰተውም ወይም ባልተከሰተውም ሁኔታ ባሻገር ደስታ ሊሰማን ይችላል። ደስታ ከሱና በሱ ምክንያት ይመጣል። እሱ የደስታ ሁሉ ምንጭ ነው። በገና ”ደስታ ላለም፣ ጌታ መጥቷልና”9 የሚለውን መዝሙር ስንዘምር ይህም ይሰማናል። እናም አመቱን በሙሉ ሊሰማን ይችላል። ለኋለኛ ቀን ቅዱሳን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ ነው!

ለዛ ነው የኛ የወንጌል አገልጋዮች ቤታቸውን ትተው ወንጌሉን ለመስበክ የሚሄዱት። አላማቸውም የቤተ ክርስቲያን አባላትን ቁጥር መጨመር አይደለም። ይልቁንም፣ የወንጌል አገልጋዮቻችን የሚያስተምሩት እናም የሚያጠምቁት10 ለአለምም ህዝብ ደስታን ለማምጣት ነው።!11

አዳኝ እንዳበረከተው ”አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ”12 ሰላም፣ እሱም የሰውን መገንዘብ እና የምድርን መረዳት የሚቃረን የጋለ፣ ጥልቅ እናም የሰፋ ደስታን ይሰጣል። ለምሳሌ፣ ልጆቻችሁ ሊዳን በማይቻል ህመም ሲሰቃዩ፣ ወይም ስራችሁን ስታጡ ወይም ባለቤታችሁ ሲከዳችሁ ደስታ የሚሰማ አይመስልም። ሆኖም በእርግጠኝነት አዳኝ የሚሰጠው ደስታ ይሄ ነው። “ችግሮቻን ለተወሰነች ጊዜ እንደሆነ”13 እናም ይህም ለኛው በጎነት እንደሚውል14 እያረጋገጠልን፣ ደስታው የማይቋረጥ ነው።

እንዴት አርገን ነው ያንን ደስታ የምንቀበለው? እኛም “የእምነታችን ጸሀፊ እና ፈጻሚ ወደሆነው ኢየሱስ”15 “በሀሳቦች በሙሉ”16 በመመልከት ለመጀመር እንችላለን። በጸሎት እና ከእርሱና ከሰማይ አባታችን ጋር የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ ልናመሰግነው እንችላለን። አዳኛችን ለኛ አብዝቶ እውን ሲሆልን እናም የሱ ደስታ እንዲሰጠን ስንማጸን፣ ደስታችን ይጨምራል።

ደስታ ሃያል ነው፣ እናም በደስታ ላይ ማተኮር የእግዚአብሄርን ሃይል ወደ ህይወታችን ያመጣል። በሁሉም ነገሮች እንደሚሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻ አርያችን ነው፣ ”በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታገሰ።”17 ያን አስቡት! በምድር ላይ ካሉ የሚያሰቅቁ ተሞክሮዎችን ለመጽናት፣ አዳኛችን ያተኮረው በደስታ ላይ ነው።!

በፊቱ ያለው ደስታ ምንድን ነበር? በእርግጥም እኛን የማጽዳት፣የመፈወስ፣ እናም የማጠንከር ደስታ፤ ንስሃን ለሚገቡ የሚከፈለው የሃጢያት ክፍያ ደስታ፤ ለእኔና ለናንተ ወደቤታችን—በንጽህና እና በብቁነት—ከሰማያዊ ወላጆቻችን እና ቤተሰቦቻችን ለመኖር እንድንመለስ የማስችል ደስታ ነው።

ወደ እኛ፣ ወይም ወደምንወዳቸው፣ ስለሚመጡት ደስታዎች ትኩረት ካደረግን፣ በዚህ ጊዜ አጥለቅላቂ፣ አሰቃይ፣ አስፈሪ፣ ፍትሃዊ ያልሆነ፣ ወይም በቀላሉ የማይፈጸም የሆኑትን ምን መጽናት እንችላለን?

እርግጠኛ ባልሆነ የመንፈሳዊ ሁኔታ ያለ አንድ አባት በመጨረሻ በጌታ ፊት ንጹህ እና ትክክለኛ በመሆን በጣው ደስታ—ከጥፋተኝነት ስሜት እና እፍረት ነጻ የመውጣት—እና የአምሮ ሰላምም ደስታ ላይ ትኩረት አደረገ። ያም ትኩረት ንስሀ ለመግባት ድፍረትን ሰጠው፥ ለሚስቱና ለኤጲስ ቆጶሱ የራቁት ምስሎችን የማየት ያለበትን ችግር፣ አስከትሎም በጋብቻ አለመታመኑን በሙሉ ለመናዘዝም። እሱ አሁን ኤጲስ ቆጶሱ እንዲያደርግ የሚመክረውን ሁሉ ያደርጋል እናም የሚስቱን እምነት ደግሞ ለማግኘት በሙሉ ልቡ ይጥራል።

አንድ ወጣት ሴት፣ ታዋቂ እና ፍላጎትን የሚያነሳሳ ነገር ግን ለመንፈስ አደገኛ የሆኑን ሁኔታዎችን ትታ ስትሄድ የጋደኞችን ማፌዝ ለመጽናት፣ ከፍትወተ ስጋ ግንኙነት ንጹህ የመሆን ደስታ ላይ ትኩረትን አደረገች።

ባለቤቱን ደጋግሞ ዝቅ የሚያደርግ እናም እንደፈለገው በልጆቹ ላይ በንዴት የሚደነፋ አንድ ወንድ፣ መንፈስ ቅዱስን ቋሚ ጓደኛው ለማድረግ ብቁ ለመሆን ላይ ትኩረትን አደረገ። ይህንንም ማተኮሩ፣ በአብዛኛው ጊዜ የተሸነፈበትን፣ ፍጥረታዊ ሰውነቱን ለማስወገድ አነሳሳው፣18 እና አስፈላጊውን ለውጥም አደረገ።

የቅርብ የስራ ጓደኛዬ ለሀያ አመታት ስለነበሩበት ከባድ ፈተናዎች ነገረኝ። እንዲህ አለ፣ “በደስታ መሰቃየትን ተምሬአለሁ። ስቃዬ በክርስቶስ ስቃይ ተውጦ ነበር።”19

እኔና እናንተ ከፊታችን “የተቀመጠውን” ደስታ ላይ በማተኮር መጽናት የምንችላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?20 ምን አይነት ንስሀስ ይቻላል? ምን አይነት ድክመት ጥንካሬ ሊሆን ይችላል?21 ምን አይነት ግሰጻስ በረከት ሊሆነን ይችላል?22 ምን አይነት ተስፋ መቁረጥ፣ እንዲሁም አሳዛኝ አደጋ፣ ወደ በጎነት መመለስ ይችላል?23 እናም ምን አይነት አስቸጋሪ አገልግሎት ለጌታ ለመስጠት እንችላለን?24

በትጋት ወደ ጌታ ስናተኩር እና የሱን ወደ ደስታ የማተኮርን መንገድ ስንከተል፣ በደስታችን ጣልቃ የሚያገቡ ነገሮችን ማስወገድ አለብን። ቆሪሆርን፣ ጸረ ክርስቶስ የሆነውን ታስታውሳላችሁ? ስለ አዳኝ ሀሰትን በማባዛት፣ ቆሪሆር ከቦታ ወደቦታ እየሄደ ሊቀ ካህን የሆነው ፊት መቶ እንዲህ እስኪጠይቀው ድረስ ቀጠለ፥ “የጌታን መንገድ ለማሳት ለምን ትሄዳለህ? ይህንንም ህዝብ ደስታውን ለማቋረጥ ለምን ክርስቶስ የለም ብለህ ታስተምራለህ?”25

ክርስቶስን ወይም የሱን ትምህርት የሚቃወም ማንኛውም ነገር ደስታችንን ያቋርጣል። ያም ጨምሮ፣ በድህረ ገጾች እና በብሎጎች ተስፋፍቶ ያሉ የሰዎችን ፍልስፍና ናቸው።26

አለምን ከተመልከትን እና ለደስታ የሚጠቀሙትን ቀመር ከተከተልን፣27 በፍጹም ደስታን አናውቅም። ጻድቃን ያልሆኑ የተለያዩ ስሜት ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን በፍጹም ደስታ አይኖራቸውም!28 ደስታ ለታማኞች የሆነ ስጦታ ነው።29 ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረው በፈቃደኝነት የጻድቅ ህይወትን ለመምራት በመጣር የሚመጣ ስጦታ ነው።30

እንዴት ደስታን እንደምናገኝ አስተማረን። የሰማይ አባታችንን አምላካችን አድርገን ስንመርጥ31 እናም ያዳኛችን የኃጢያት ክፍያ በህይወታችን ሲሰራ መሰማት ሲችለን፣ በደስታ እንሞላለን።32 ሁልጊዜ ባለቤቶቻችንን ስንንከባከብ እና ልጆቻችንን ስንመራ፣ ሁልጊዜ አንድን ሰው ይቅር ስንል ወይም ይቅርታን ስንጠይቅ፣ ደስታ ሊሰማን እንችላለን።

ሁልቀን እኔና እናንተ የሰለስቲያል ህግጋትን ለመኖር ስንመርጥ፣ ሁልጊዜ ቃል ኪዳኖቻችንን ስንጠብቅና ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ ስናግዝ፣ ደስታ የኛው ይሆናል።

የዘማሪውን ቃላቶች አስተውሉ፤ “ ሁልጊዜ እግዜአብሄርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም።” … በሱም ፊት የደስታ ጥጋብ አለ።”33 ይህ መርህ በልባችን ውስጥ ሲጣበቅ፣ እያንዳንዷ ቀን የደስታ እና የቡረቃ ጊዜ ትሆናለች።34 ይህንንም ተቀደሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. 2 ጢማቴዎስ 3፥1–5 ተመልከቱ።

  2. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥2688፥91 ተመልከቱ።

  3. 2 ጢማቴዎስ 3፥2–4

  4. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥5 ተመልከቱ።

  5. ኤፌሶን 6፥12

  6. 2 ኔፊ 2፥25

  7. የምዙሪ ክፍለ ሀገር ገዢው ሊልበርን ደብሊው. ቦግስ በጥቅምት 27፣ 1838 (እ.አ.አ) ሞርሞኖች የሚገደሉበትን ትእዛዝ ስጠ (Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 349 ተመልከቱ።

  8. እላይዛ አር. ስኖው፣ በኤድዋርድ ደብሊው. ቱለጀ፣ The Women of Mormondom (1877) ውስጥ፣ 145–46።

  9. “Joy to the World,” Hymns, no. 201.

  10. ሚስዮኖች ጌታ እንዲህ እንዳዘዘው ያደርጋሉ፥ ይሰብካሉ፣ ያስተምራሉ፣ እናም በስሙ ይጠምቃሉ (ማቴዎስ 28፥19ማርቆስ 16፥15ሞርሞን 9፥22ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥884፥62112፥28)። በምልድና ጸሎቱ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዝሙርቱ ጋር ስላለው ደስታ አወጀ። እንዲህም አለ፣ “ ይህን በአለም እናገራለሁ፣ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ ይሆን ዘንድ” (ዮሀንስ 17፥13፤ ማብራሪያ ተጨምሯል)።

  11. አልማ 13፥22 ተመልከቱ።

  12. ፊሊጵስዮስ 4፥7

  13. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥7

  14. 2 ኔፊ 2፥2 ተመልከቱ።

  15. ዕብራውያን 12፥2

  16. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 6፥36

  17. ዕብራውያን 12፥2

  18. ሞዛያ 3፥19ተመልከቱ። ማስታወሻ፥ “ተፈጥሯዊው ሰው” የእግዚአብሄር ጠላት ብቻ አይደለም፤ ደግሞም የሚስቱ እና የልጆቹ ጠላት ነው።

  19. አልማ 31፥38 ተመልከቱ።

  20. ዕብራውያን 12፥2

  21. ኤተር 12፥27 ተመልከቱ።

  22. ዕብራውያን 12፥6 ተመልከቱ።

  23. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7 ተመልከቱ።

  24. ማቴዎስ 19፥26ማርቆስ 10፥27 ተመልከቱ።

  25. አልማ 30፥22። መፅሐፈ ሞርሞን ኢየሱስን ለመከተል በመምረጥ ምክንያትደስታን ለማግኘት በቻሉ ወንዶስ እና ሴቶች ምሳሌ የተሞላ ነው። እንደ ኮሪሆር አይነት ምንም ሌላ ምርጫ ወደ መጨረሻ ጥፋት ይመራል።

  26. ስም ማጥፋት፣ ማለትም ያለአግባብ ማቅረብ፣ ትርጉሙ የአንድን ሰው ወይም ነገር ዝና ለማጥፋት የተጠነሰሰ ሃሰተኛ እና የተንኮል አረፍተ ነገር ማለት ነው። ስም ማጥፋት በቆሪሆር ጊዜ ይካሄድ ነበር እናም በዚህም ጊዜ አለ። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በስም ማጥፋት እንኳን ቢሆን ስለ ቤተ ክርስቲያኗ አይበገሬነት ተናግሯል። እንዲህ አለ፥ “የእውነት ሰንደቅ አላማ ተተክላለች፤ ያልተቀደሰ ማንም እጅ የስራውን እድገት ማቆም አይችልም፤ ስደትም ቢብስ፣ ወንበዴዎች ቢተባበሩ፣ የጦር ሰራዊቶች ቢሰበሰቡ፣ ሀሜተኞች ስም ቢያጠፉ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነት በድፍረት፣ በግርማ፣ በገለልተኝነት፣ በሁሉም አህጉራት ዘልቆ እስኪገባ፣ ሁሉንም ድንበር እስኪጎበኝ፣ ሁሉንም አገራት እስኪጠርግ፣ እናም እያንዳንዷ ጆሮ እስክትሰማ፣ የእግዚአብሔርም ዓላማ እስኪሳካ እናም ታላቁ ያህዌ ሥራው ተጠናቋል እስኪል ድረስ ይጓዛል” (Teachings: Joseph Smith, 444)።

  27. አለምነገሮችን መገብየት ደስታን ያመጣል ብላ ታስተምራለች። ያም ካልሰራ፣ ጨምራችሁ ግዙ! በሃጢያትም ደስታን ማግኘት እንደምትችሉ ታስተምራለች። ያም ካልሰራ፣ ጨምራችሁ ሃጢያትን ስሩ ትላለች! የምትገባውም ቃል በእያንዳንዱ የህይወት አላማ መደሰት ነው ለሚል ቀስተ ደመና መጨረሻ ላይ የደስታ ማሰሮ እንዳለ ነው። እውነት አይደለም!

  28. በዚህም አለም ወይም በሚመጣው አለም አይሆንም።

  29. ጻድቅ ቅዱሳን “የአለምን መከራዎች የተቋቋሙ... የእግዚአብሄርን መንግስት ይወርሳሉ፣ ... እናም ደስታቸው ለዘላለም ሙሉ ይሆናል” (2 ኔፊ 9፥18)።

  30. ለምሳሌ፣ 2 ኔፊ 27፥30አልማ 27፥16–18 ተመልከቱ።

  31. 1 ኔፊ 17፥40 ተመልከቱ።

  32. ሞዛያ 4፥2–3 ተመልከቱ።

  33. ምሳሌ 16፥8፤ 11

  34. ኢሳይያስ 35፥102 ኔፊ 8፥3