ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፳፮


ምዕራፍ ፳፮

አሞን በጌታ ተመካ—ታማኞች በጌታ ይጠነክራሉ፣ እናም እውቀት ይሰጣቸዋል—ሰዎች በእምነት ሺህ ነፍሳትን ወደንስሃ ያመጣሉ—እግዚአብሔር ሁሉም ዓይነት ስልጣን አለው እናም ሁሉንም ያውቃል። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን፣ አሞን ለወንድሞቹ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፣ እንዲህም ይላሉ፥ ወንድሞቼ፣ እነሆ እንዲህ ብዬ እናገራችኋለሁ፣ ለደስታችን እንዴት ታላቅ ምክንያት አለን፤ ከዛራሔምላ ምድር በጀመርን ጊዜ እግዚአብሔር ታላቅ በረከትን ሊሰጠን እንደሚችል መገመት እንችላለን?

እናም አሁን፣ እርሱ ምን ዓይነት ታላቅ በረከት በእኛ ላይ አድርጓል? ብዬ እጠይቃችኋለሁ፣ ይህንን ለመናገርስ ትችላላችሁን?

እነሆ፣ እኔ እመልስላችኋለሁ፤ ወንድሞቻችን፣ ላማናውያን በጨለማ ነበሩ፤ አዎን፣ እንዲያውም በጨለማው ገደል፤ ነገር ግን እነሆ፣ ስንቶቹ ናቸው ድንቁን የእግዚአብሔር ብርሃን የተመለከቱት! እናም ይህንን ታላቅ ስራም ለመፈፀም በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ መሆናችን፣ ይህ በእኛ ላይ የወረደው በረከት ነው።

እነሆ፣ ሺዎቹም ተደሰቱ፣ እናም ወደ እግዚአብሔር በረትም መጡ።

እነሆ፣ እርሻው ተዘጋጅቶ ነበር፣ እናም እናንተ ስላጨዳችሁና፣ በጉልበታችሁ ስለሰበሰባችሁ፣ አዎን፣ ቀኑን ሁሉ ስለሰራችሁ የተባረካችሁ ናችሁ፤ እናም የነዶዎቻችሁን ቁጥር ተመልከቱ! እናም እንዳይባከኑ በየጎተራዎቹ ይሰበሰባሉ።

አዎን፣ እነርሱም በመጨረሻው ቀን በውሽንፍሩ አይመቱም፤ አዎን፣ በአውሎ ንፋሱም አይበታተኑም፤ ነገር ግን ውሽንፍሩ ሲመጣ ሁሉም በቦታቸው በአንድ ላይ ይሰበሰባሉ፣ ውሽንፍሩም ዘልቆ ሊገባ አይቻለውም፤ አዎን፣ በሃያሉ ነፋስ ጠላታቸው ሊወስዳቸው ወደሚፈልግበትም የትኛውም ቦታ ቢሆን አይገፉም።

ነገር ግን እነሆ፣ እነርሱ በአውድማው ጌታ እጅ ናቸው፣ እናም የእርሱ ናቸው፤ እርሱም በመጨረሻው ቀን ያስነሳቸዋል

የአምላካችን ስም የተባረከ ይሁን፤ በመዝሙር እናወድሰው፤ አዎን ለቅዱስ ስሙ ምስጋና እናቅርብ፤ ምክንያቱም እርሱ ለዘለዓለም ፅድቅን አድርጓልና።

ከዛራሔምላ ምድር ባንመጣ ኖሮ፣ እነዚህ የተወደዱ ወንድሞቻችን፣ እኛንም እጅግ የሚወዱን፣ ለእኛ ያላቸው ጥላቻ የከፋ ይሆን ነበር፣ አዎን እናም ደግሞ እነርሱ ለእግዚአብሔር ባዕዳን በሆኑ ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ አሞን እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ ወንድሙ አሮን እንዲህ በማለት ወቀሰው፥ አሞን ደስታህ ወደኩራት ይወስድሃል ብዬ እፈራለሁ።

፲፩ ነገር ግን አሞን እርሱን እንዲህ አለው፥ በራሴ ጉልበት እንዲሁም በጥበቤ አልኮራም፤ ነገር ግን እነሆ፣ ደስታዬ ሙሉ ነው፣ አዎን፣ ልቤ በደስታ ይሞላል፣ እናም በአምላኬ ሐሴት አደርጋለሁ።

፲፪ አዎን፣ እኔ ምንም እንዳልሆንኩ አውቃለሁ፤ ጉልበቴን በተመለከተ ደካማ ነኝ፤ ስለዚህ በራሴ አልኮራም፣ ነገር ግን በአምላኬ እኮራለሁ፣ ምክንያቱም በእርሱ ኃይል ሁሉንም ነገር ማድረግ እችላለሁና፤ አዎን፣ እነሆ፣ በዚህ ምድር ብዙ አስደናቂ ተዓምራትን አድርገናል፣ ለዚህም ስሙን ለዘለዓለም እናወድሳለን።

፲፫ እነሆ፣ ስንት ሺህ ወንድሞቻችንን ነው እግዚአብሔር ከሲኦል እስራት የፈታው፣ እናም የቤዛነትን ፍቅር እንዲዘምሩ ተደረጉ፣ እናም ለዚህም ምክንያቱ በውስጣችን ባለው በቃሉ ኃይል የተነሳ ነበር፣ ስለዚህ ለመደሰትስ ታላቅ ምክንያት አይኖረንምን?

፲፬ አዎን፣ ልዑል እግዚአብሔር በመሆኑ እርሱን ለዘለዓለም ለማወደስ ምክንያት አለን፣ እናም ወንድሞቻችንን ከሲኦል ሰንሰለት አስለቅቋልና።

፲፭ አዎን፣ እነርሱም በዘለአለማዊው ጨለማና ጥፋት ተከበው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ወደ ዘለአለማዊው ብርሃን፣ አዎን፣ ወደ ዘለአለማዊው ደህንነት አመጣቸው፤ እናም ወደር በሌለው ፍቅሩም ተከበዋል፤ አዎን እናም ይህን ታላቅና ድንቅ ስራ በመስራታችን በእጆቹ መሳሪያ ሆነን ነበር።

፲፮ ስለዚህ፣ እኛ እንደነቃለን፤ አዎን በጌታ እንደነቃለን፤ አዎን፣ ደስታችን ሙሉ በመሆኑ ሐሴት እናደርጋለን፤ አዎን አምላካችንን ለዘለዓለም እናወድሳለን። እነሆ፣ በጌታ ከመጠን በላይ ለመደነቅ የሚችል ማን ነው? አዎን፣ ስለታላቁ ኃይሉና፣ ስለምህረቱ፣ እናም ለሰው ልጆች ስላለው ፅናት አብዝቶ መናገር የሚችል ማን ነው? እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ ከተሰማኝ ጥቂቱን ለመናገር አልችልም።

፲፯ አምላካችን ከአሰቃቂው ከኃጢያትና ከተበላሸው ሁኔታችን ሲያስለቅቀን እንደዚህ መሃሪ እንደሚሆንልን ማን ለመገመት ይቻለዋል?

፲፰ እነሆ፣ በቁጣም ቢሆን ቤተክርስቲያኗን በኃይል በማስፈራራት ለማጥፋት ሄድን።

፲፱ አቤቱ እንግዲህ፣ ወደአሰቃቂው ጥፋት ለምን አልተወንም፣ አዎን፣ የፍርዱ ጎራዴስ በእኛ ላይ እንዲወድቅ፣ እናም ወደዘለዓለማዊው ጥፋት እንዲጥለን ለምን አላደረገም?

አቤቱ ይህም ሀሣብ ነፍሴን እንድትኮበልል አድርጓት ነበር፤ እነሆ፣ እግዚአብሔር ፍርዱን በእኛ ላይ አላደረገም፣ ነገር ግን በታላቁ ምህረቱ ከዘለዓለማዊው ሞትና ስቃይ አሳልፎን፣ እንዲሁም ወደ ነፍሳችን ደህንነት አምጥቶናል።

፳፩ እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ እነዚህን ነገሮች የሚያውቅ ተፈጥሯዊው ሰው ማን ነው? ንስሃ ከገባው በስተቀር እነዚህን ነገሮች የሚያውቅ ማንም የለም እላችኋለሁ።

፳፪ አዎን፣ ንስሃ ለሚገቡ፣ እምነትን ለሚለማመደውና፣ መልካምን ለሚሰራው፣ እንዲሁም ሳያቋርጡ ለሚፀልየው፣ ለእንደእነዚህ ዓይነቶቹ የእግዚአብሔርን ሚስጥር እንዲያውቁ ይሰጣቸዋል፤ አዎን፣ ለእንደነዚህ አይነቶቹ ተገልፀው የማያውቁት ነገሮች እንዲገለፁላቸው ይሰጣቸዋል፤ አዎን እናም ለእነዚህ በሺህ የሚቆጠሩትን ነፍሳት ለንስሃ እንዲያመጡ ይሰጣቸዋል፣ እኛም ወንድሞቻችንን ለንስሃ እንድናመጣቸው እንደተሠጠን እንዲሁ ይሆናል።

፳፫ እናም ወንድሞቼ በዛራሔምላ ምድር ላሉት ወንድሞቻችን ወደኔፊ ምድር ለወንድሞቻችን ለላማናውያን ለማስተማር እንሄዳለን እንዳልናቸው፣ እናም በማሾፍ እንደሳቁብን ታስታውሳላችሁን?

፳፬ እንዲህ ብለውናልና፥ ላማናውያንን እውነትን ወደማወቅ ማምጣት እንደሚቻላችሁ ትገምታላችሁን? እንደ አንገተ ደንዳና ህዝቦች እንደነበሩት፤ በደም መፍሰስ ልባቸው እንደተደሰተው፤ ጊዜያቸውንም በክፋት እንዳሳለፉት፣ አቅጣጫቸውም ከመጀመሪያው ጀምሮ ሕጉን እንደሚተላለፉት የሆነውን ላማናውያንን የአባቶቻቸው ወግ ትክክል እንዳልነበር ለማሳመን ይቻለናል ብላችሁ ትገምታላችሁን? አሁን ወንድሞቼ ይህ የእነርሱ አነጋገር እንደሆነ አስታውሱ።

፳፭ እናም በተጨማሪ እንዲህ አሉ፥ እነርሱንና ክፋታቸውን ከምድሪቱ እንድናጠፋ፣ እኛንም እንዳይወሩን እናም እንዳያጠፉን መሳሪያዎቻችንን በእነርሱ ላይ እንታጠቅ።

፳፮ ነገር ግን እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ወደ ምድረበዳው የመጣነው ወንድሞቻችንን ለማጥፋት ባለ ዓላማ አይደለም፣ ነገር ግን ጥቂት ነፍሳትን ለማዳን ባለ ዓላማ ነው።

፳፯ እናም ልባችን በተጨነቀ ጊዜና፣ ወደኋላችን ለመመለስ በተዘጋጀን ጊዜ፣ እነሆ፣ ጌታ አፅናናን፣ እናም እንዲህ አለን፥ በወንድሞቻችሁ በላማናውያን መካከል ሂዱና፣ ስቃያችሁን በትዕግስት ያዙት፣ እናም መልካም ውጤትን እንድታገኙ አደርጋችኋለሁ።

፳፰ እናም አሁን እነሆ፣ እኛ መጥተናልና፣ ከእነርሱ መካከል ሆነናል፤ እናም በስቃያችን ትዕግስተኞች ነበርንም፣ በማንኛውም የህይወት ውጣውረዶች ተሰቃይተናልም፤ አዎን፣ የዓለምን ምህረት ላይ ተስፋ በማድረግ ከቤት ወደቤት ተጉዘናል—በዓለም ምህረት ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔርም ምህረት ተስፋ አድርገናል።

፳፱ እናም በየቤቶቻቸው ገባንና፣ አስተማርናቸውም፣ በጎዳናዎቻቸው ላይ አስተማርናቸውም፤ አዎን፣ በኮረብታዎቻቸውም ላይ አስተማርናቸው፤ እናም፣ በቤተመቅደሶቻቸውና በምኩራባቸው ገባንም፣ አስተማርናቸውም፤ ተባረርንና፣ ተሳለቁብንም፣ ተፉብንም፣ ፊታችንንም መቱት፤ እናም በድንጋይ ተወገርንና ተወስደን በጠንካራ ገምዶች ታሰርን፣ ወደ ወህኒ ቤት ተጣልንም፤ እናም በእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ በድጋሚ ተለቀቅን።

እናም በሁሉም ዓይነት ስቃይ ተሰቃይተናል፣ እናም ይህ ሁሉ የሆነውም ምናልባት ጥቂት ነፍሳትን የምናድንበት መንገድ እንድንሆን ነበር፤ እናም ምናልባት ጥቂቶችን ለማዳን ምክንያት ለመሆን ከቻልን ደስታችን ሙሉ ይሆናል ብለን ገምተን ነበር።

፴፩ እናም እነሆ፣ የስራችንን ፍሬ መመልከት እንችላለን፤ እናም እነርሱ ጥቂት ናቸውን? እኔ ግን አይደሉም እላችኋለሁ፤ እነርሱ ብዙ ናቸው፤ አዎን ለወንድሞቻቸውና ደግሞ ለእኛ ባላቸው ፍቅር የተነሳ ከልባቸው መሆኑን እንመሰክራለን።

፴፪ እነሆም የጠላቶቻቸውን ነፍስ እንኳን ከማጥፋት ህይወታቸውን መስዋዕት ማድረጉ ይሻላቸዋል፤ እናም ለወንድሞቻቸው ባላቸው ፍቅር የተነሳ የጦር መሳሪያዎቻቸውን በምድር ውስጥ በጥልቅ ቀበሩት

፴፫ እናም አሁን እንዲህ እላችኋለሁ፣ በምድሪቱ ሁሉ እንደዚህ ያለ ታላቅ ፍቅር አለን? እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በኔፋውያን መካከልም እንኳን የለም።

፴፬ እነሆም በወንድሞቻቸው ላይ መሣሪያዎቻቸውን ያነሳሉ፤ ነገር ግን እንዲገድሉአቸው አይፈቅዱም። ነገር ግን እነሆ ከእነዚህ ስንቶቹ ናቸው ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት፤ እናም በፍቅራቸውና ለኃጢያት ባላቸው ጥላቻ ምክንያት ወደ አምላካቸው መሄዳቸውን እናውቃለን።

፴፭ አሁን ለመደሰት ምክንያት የለንምን? አዎን፣ እንዲህ እላችኋለሁ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ እንደእኛ ለመደሰት ታላቅ ምክንያት ያላቸው ሰዎች በጭራሽ የሉም፤ አዎን፣ እናም ደስታዬ በአምላኬ እስከምኮራም እንኳን ደርሷል፤ ምክንያቱም እርሱ ሁሉም ስልጣን፣ ሁሉም ጥበብ፣ እናም ሁሉም ግንዛቤ አለውና፤ ሁሉንም ነገር ያውቃልና፣ እርሱ እስከ ደህንነትም እንኳን ንስሃ ለሚገቡትና በስሙ ለሚያምኑት መሀሪ ነውና።

፴፮ እናም ይህ ኩራት ከሆነ፣ እኔም እንደዛው እኮራለሁ፤ ምክንያቱም ይህ የእኔ ህይወትና ብርሃን ነው፤ ደስታዬና ደህንነቴ፣ እናም ከዘለዓለማዊው ጥፋት የእኔ ቤዛ ነውና። አዎን የእስራኤል ዛፍ ቅርንጫፍ ለሆኑት እናም በእንግዳው ምድር ለጠፉት ለዚህ ህዝብ የሚያስበው አምላክ ስሙ የተባረከ ይሁን፤ አዎን፣ እኛ በባዕድ ምድር ለምንከራተተው የሚያስበው የአምላኬ ስም የተባረከ ይሁን እላለሁ።

፴፯ እንግዲህ ወንድሞቼ፣ እግዚአብሔር በየትኛውም ምድር ለሚገኙት ህዝቦቹ እንደሚያስብ እንመለከታለን፤ አዎን፣ ህዝቡን ያስባል፣ እናም የአንጀት ምህረቱም በምድር ላይ ሁሉ ናቸው። እንግዲህ ይህ የእኔ ደስታና ታላቁ ምስጋናዬ ነው፤ አዎን፣ እናም ለአምላኬ ምስጋናዬን ለዘለአለም አቀርባለሁ። አሜን።