ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፫


ምዕራፍ ፫

የያሬድ ወንድም የጌታን ጣት አስራ ስድስቱን ድንጋዮች ሲነካ ተመለከተ—ክርስቶስ የመንፈስ አካሉን ለያሬድ ወንድም አሳየው—ፍፁም እውቀት ያላቸው በመጋረጃው ሊታገዱ አይችሉም—ተርጓሚዎች የያሬዳውያንን መዝገብ ወደ ብርሃኑ ለማምጣት ተዘጋጅተዋል።

እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም ተራራውም እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ሼለም ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ሔደ (እንግዲህ የተዘጋጀው ጀልባ ብዛት ስምንት ነበር) እናም ከአለት አስራ ስድስት ትናንሽ ድንጋዮች አቅልጦ አወጣ፤ እናም እነርሱም የነጡ፣ እናም እንደመስታወት ብሩህ ነበሩ፤ እናም እርሱም ተሸክሞ ወደ ተራራው ጫፍ ወሰዳቸው፣ እናም ወደ ጌታ በድጋሚ እንዲህ ሲል ጮኸ፥

አቤቱ ጌታዬ በጥፋት ውሀ መከበብ አለባችሁ ብለሃል። እንግዲህ እነሆ ጌታ ሆይ፣ አገልጋይህ በፊትህ ደካማ በመሆኑ አትቆጣው፤ ምክንያቱም አንተ ቅዱስ እንደሆንክ እናም በሰማይ እንደምትኖር፤ እናም እኛ ባንተ ፊት ከንቱዎች እንደሆንን እናውቃለን፤ በውድቀትም የተነሳ ተፈጥሮአችን ያለማቋረጥ ክፉ ሆኗል፤ ይሁን እንጂ፣ ጌታ ሆይ፣ እንደፈለግነውም ከአንተ እንቀበል ዘንድ አንተን እንድንጠራ ትዕዛዝ ሰጥተኸናል።

እነሆ፣ ጌታ ሆይ፣ በክፋታችን ቀጥተኸናል፣ እናም አባረኸናል፣ እናም ለእነዚህ ብዙ ዓመታትም በምድረበዳው ነበርን፤ ይሁን እንጂ፣ አንተ ለእኛ መሃሪ ነህ። አቤቱ ጌታ፣ በአዘኔታም ተመልከተኝ፣ እናም ከህዝብህም ቁጣህን መልስ፣ እናም በዚህ ማዕበላዊ ባህር በጨለማ እንዲጓዙ አትፍቀድ፤ ነገር ግን ከድንጋይ ያቀለጥኳቸው እነዚህ ነገሮች ተመልከት።

እናም ጌታ ሆይ፣ ስልጣን ሁሉ እንዳለህ፣ እናም ለሰዎች ጥቅምም ማንኛውንም ማድረግ እንደምትችል አውቃለሁ፤ ስለዚህ አቤቱ ጌታ፣ እነዚህን ድንጋዮች በጣትህ ንካቸው፣ እናም በጨለማም እንዲያበሩ አዘጋጃቸው፤ እናም ባዘጋጀነው ጀልባ ላይም ባህሩን በምናቋርጥበት ጊዜ ብርሃን ይሰጡን ዘንድ ያበሩልናል።

እነሆ፣ ጌታ ሆይ፣ ይህንን ማድረግ ትችላለህ። ሰዎች በአስተሳሰባቸው አነስተኛ አድርገው የሚያዩትን ታላቅ ኃይል ለማሳየት እንደምትችል እናውቃለን።

እናም እንዲህ ሆነ የያሬድ ወንድም እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ እነሆ፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ ድንጋዮቹን አንድ በአንድ በጣቱ ነካቸው። እናም መጋረጃው ከያሬድ ወንድም ዐይን ላይ ተወገደ፣ እናም የጌታን ጣት ተመለከተ፤ እናም ይህ ሥጋና ደም እንደለበሰ እንደ ሰው ጣት ነበር፤ እናም የያሬድ ወንድም በፍርሃት በመዋጡ በጌታ ፊት ወደቀ።

እናም ጌታ የያሬድ ወንድም በመሬት ላይ መውደቁን ተመለከተ፤ እናም ጌታ እንዲህ ሲል ተናገረ፥ ተነሳ ለምን ትወድቃለህ?

እናም ለጌታ እንዲህ አለው፥ የጌታን ጣት ተመለከትኩ፣ እናም ይመታኛል ብዬ ፈራሁኝ፤ ምክንያቱም ጌታ ሥጋና ደም እንዳለውም አላውቅም ነበርና።

እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ በእምነትህ የተነሳ ሥጋና ደም እንደምለብስ ተመለከትህ፤ እናም ከዚህ በፊት ማንም ሰው እንደአንተ ያለ ታላቅ እምነት ያለው በጭራሽ በፊቴ አልመጣም፤ ይህ ባይሆን ኖሮ ጣቴን ለማየት አትችልም ነበር። ከዚህ የበለጠን ነገር አይተሃልን?

እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ አላየሁም፤ ጌታ ሆይ፣ ራስህን አሳየኝ።

፲፩ እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ የምናገርህን ቃላት ታምናለህን?

፲፪ እናም እርሱ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ እውነት እንደምትናገር አውቃለሁ፤ አንተ የእውነት አምላክ ነህና፣ ለመዋሸት አትችልም።

፲፫ እናም እርሱም እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ እነሆ፣ ጌታ ራሱን አሳየው፣ እናም እንዲህ አለው፥ እነዚህን ነገሮች በማወቅህ አንተ ከመውደቅ ድነሃል፤ ስለዚህ እኔ ባለሁበት ተመልሰሀል፣ ስለዚህም ራሴን አሳይቼሀለሁ

፲፬ እነሆ፣ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ህዝቤን ለማዳን የተዘጋጀሁ እኔ ነኝ። እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ። እኔ አብም ወልድም ነኝ። በእኔም የሰው ዘር በሙሉ፣ እንዲሁም በስሜም የሚያምኑትም፣ የዘለዓለም ህይወትን ያገኛሉ፤ እናም እነርሱም ወንድና ሴት ልጆቼም ይሆናሉ።

፲፭ እናም እኔ ለፈጠርኩት ሰው በጭራሽ ራሴን አላሳየሁም፤ ምክንያቱም ማንም አንተ እንዳደረግኸው በእኔ ያመነ አልነበረምና። አንተ በእኔ አምሳል መፈጠርህን ተመልክተሃልን? አዎን፣ ሰዎች ሁሉ እንኳ በመጀመሪያ የተፈጠሩት በእኔ አምሳል ነው።

፲፮ እነሆ፣ ይህ ሰውነት፣ አሁን የተመለከትከው፣ መንፈሳዊው ሰውነቴ ነው፤ እናም ሰውን የፈጠርኩት በመንፈስ አካሌ አምሳል ነው፤ እናም በመንፈስ ለአንተ እንደታየሁት ለህዝቤም በሥጋ እታያለሁ።

፲፯ እናም እንግዲህ እንዳልኩት እኔ ሞሮኒ ስለተፃፉት ስለነዚህ ነገሮች ሙሉ ታሪክን መፃፍ አልችልም፤ ስለዚህ ኢየሱስ ለኔፋውያን እራሱን እንዳሳየው በዚሁ መልክ ለዚህ ሰው ራሱን በመንፈስ አሳይቷል ማለቱ ይበቃኛል።

፲፰ እናም እርሱም ለኔፋውያን እንዳስተማራቸው አስተምሮታል፤ እናም ይህን ሁሉ ያደረገው ጌታ ብዙ ታላላቅ ስራዎችን ባሳየው ምክንያት ይህ ሰው አምላክ መሆኑን ያውቅ ዘንድ ነው።

፲፱ እናም ይህ ሰው ከነበረው እውቀትም የተነሳ በመጋረጃው ውስጥ ከመመልከት ሊጠበቅ አልቻለም፤ እናም የኢየሱስን ጣት ተመለከተ፤ በተመለከተም ጊዜ በፍርሃት ወደቀ፤ ምክንያቱም የጌታ ጣት መሆኑን አውቋልና፤ እናም እንግዲህ እምነት የለውም፣ ምክንያቱም ምንም ባለመጠራጠር ያውቃለና።

ስለዚህ፣ ይህን የእግዚአብሔር ፍፁም የሆነ እውቀት ስላለው፣ በመጋረጃው ውስጥ ሊጠበቅ አልተቻለውም፤ ስለዚህ ኢየሱስን ተመለከተው፤ እናም እርሱም አስተማረው።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ ጌታ የያሬድን ወንድም እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ ስሜን በሥጋ ሆኜ ለማስከበር እስከምመጣበት ጊዜ ድረስ እነዚህ ያየሃቸውን እናም የሰማሃቸውን ነገሮች ወደዓለም እንዲሄዱ አትፍቀድ፤ ስለዚህ፣ ያየሃቸውን እናም የሰማሃቸውን ነገሮች አስቀምጥ፣ እናም ለማንም አታሳይ።

፳፪ እናም እነሆ፣ ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜም ፃፈው፣ እናም ማንም ሊተረጉማቸው እንዳይችልም አሽገው፤ ምክንያቱም ለማንበብ በማይቻል ቋንቋ ትጽፋቸዋለህና።

፳፫ እናም እነሆ፣ እነዚህን ሁለት ድንጋዮች እሰጥሃለሁ፣ እናም ደግሞ ከምትጽፋቸው ነገሮች ጋር ትቀብራቸዋለህ።

፳፬ እነሆም የምትጽፈው ቋንቋ አምታትቼዋለሁ፤ ስለዚህ አንተ የምትፅፋቸውን ነገሮች በራሴ ጊዜም እነዚህ ድንጋዮች ለሰዎች አይኖች እንዲያደምቋቸው አደርጋለሁ።

፳፭ እናም ጌታም እነዚህን ቃላት በተናገረ ጊዜ፣ ለያሬድ ወንድም የምድር ፍጡር የሆኑትን ሁሉ፣ እናም ደግሞ ሊሆኑ የሚችሉትን በሙሉ አሳየው፤ እናም እስከምድር ዳርቻም ከያሬድ ወንድም ፊት አልደበቀውም።

፳፮ ከዚህ በፊትም በእርሱ የሚያምን ከሆነ ሁሉንም ነገሮች ሊያሳየው እንደሚችል ተናግሮታልና—ለእርሱም ያሳየዋል፤ ስለዚህ ጌታ ከእርሱ ሊደብቅ የሚቻለው ምንም ነገር የለም፤ ምክንያቱም ጌታ ሁሉንም ነገሮች ሊያሳየው እንደሚችል ያውቃልና።

፳፯ እናም ጌታ እንዲህ አለው፥ እነዚህን ነገሮች ፃፍ፣ እናም አትማቸው፣ እናም የራሴ ጊዜ ሲደርስ ለሰው ልጆች አሳያቸዋለሁ።

፳፰ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም የተቀበላቸውን ሁለት ድንጋዮች እንዲያሽጋቸው እናም ጌታም ለሰው ልጆች እስከሚያሳያቸው እርሱ ለማንም እንዳያሳያቸው አዘዘው።