የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯


ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯፥፩–፪፣ ፭፣ ፳፮፣ ፳፱–፴፫፣ ፴፰።፩ ቆሮንቶስ ፯፥፩–፪፣ ፭፣ ፳፮፣ ፳፱–፴፰ ጋር አነጻፅሩ

ጳውሎስ ጋብቻ የሚፈለግ እንደሆነ አስተማረ። በሚስዮን የተጠሩት፣ ግን፣ በአገልግሎታቸው ጊዜ ያላገቡ ቢሆኑ እግዚአብሔርን በተሻለ ለማገልገል ይችላሉ።

አሁን እናንተ እንዲህ ብላችሁ ስለ ጻፋችሁልኝ ነገሮች በሚመለከት፣ ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው።

ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት እላችኋለሁ።

ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።

፳፮ እንግዲህ ስለ አሁኑ ችግር ይህ መልካም ይመስለኛል፤ ሰው እንዲህ ሆኖ ቢኖር ታላቅ መልካም ያደርጋልና።

፳፱ ነገር ግን ወደአገልግሎት ለተጠራችሁት እናገራለሁ። ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፣ ዘመኑ አጭር ነው፣ ወደ አገልግሎት እንድትላኩ ዘንድ። እንዲሁም ሚስቶች ያሉአቸውም እንደሌላቸው ይሆናሉ፤ እናንተ ተጠርታችኋል እና የጌታን ስራ ለመስራት ተመርጣችኋልና።

የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ ይሆንብላቸዋል፤ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፣ እና የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው ይሆንላቸዋል፤

፴፩ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሆናሉ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና።

፴፪ ነገር ግን ወንድሞች ጥሪአችሁን እንድታጎሉ ፍላጎቴ ነው። ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባልና፤ ስለዚህ ያሸንፋል።

፴፫ ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፤ ስለዚህ ልዩነት አለ፣ ተደናቅፎአልና።

፴፰ እንዲሁም ያገባ እርሱም መልካም አደረገ፤ ያላገባም እርሱም የተሻለ አደረገ።