ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፪፥፩። ከያዕቆብ ፪፥፩ ጋር አነጻፅሩ
አባላት አንድን ሰው ከሌላ በላይ ከፍ አድርገው አይመልከቱ።
፩ ወንድሞቼ ሆይ፥ ለሰው ፊት እያደላችሁ፣ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ሊኖራችሁ አትችሉም።
ጆ.ስ.ት.፣ ያዕቆብ ፪፥፲፬–፳፩። ከያዕቆብ ፪፥፲፬–፳፪ ጋር አነጻፅሩ
እምነት ያለስራ የሞተ ነው እናም አያድንም።
፲፬ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ይህ ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
፲፭ አዎን፣ አንድ ሰው፣ እምነት ያለሥራ እንዳለኝ አሳይሀለሁ ይል ይሆናል፣ ግን እኔም እምነትህን ያለስራዎችህ አሳየኝ፣ እና እምነቴን በሥራዎቼ አሳይሃለሁ እላለሁ።
፲፮ ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም፣ በደኅና ሂዱ፣ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው፤ ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባይሰጣቸው፤ ለዚህ አይነት እምነትህ ምን ይጠቅማል?
፲፯ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
፲፰ ስለዚህ፣ አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን እና ሊያድንህ እንደማይችል ልታውቅ ትወዳለህን?
፲፱ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፤ ራስህን እንደነርሱ አድርገሀል፣ ጻድቅ ባለመሆን።
፳ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
፳፩ እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፣ በሥራም እምነት ፍጹም እንደሆነ ትመለከታለህን?