የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬


ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬፥፪–፭።ሮሜ ፬፥፪–፭ ጋር አነጻፅሩ

ሰው ለመዳን የሚችለው፣ የሙሴ ህግን ከመከተል ጋር ባለው ስራ ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ብቻ ነው።

አብርሃም በሥራ ህግ ጸድቆ ቢሆን፣ በራሱ ክብር አለው፤ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም።

ቅዱስ መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።

በሥራ ህግ ጸድቆ የሆነው ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤

ነገር ግን በሥራ ህግ ጽድቅ ለመሆን ለማይፈልገው፣ ግን ኃጢአተኛውንም በማያጸድቀው ለሚያምነው፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።

ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፬፥፲፮።ሮሜ ፬፥፲፮ ጋር አነጻፅሩ

እምነት እና ስራም፣ በጸጋ በኩል፣ ለደህንነት አስፈላጊ ነው።

፲፮ ስለዚህ እስከመጨረሻ ድረስ በእምነት እና በስራ፣ በጸጋ በኩል ቃል ኪዳን እንዲጸና ዘንድ ጸድቃችኋል፤ ይህም በህግ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን ደግሞ አባታችን ለሆነው ከአብርሃም እምነት ለሆኑት ለዘሩ ሁሉ ነው።