የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፫


ጆ.ስ.ት.፣ ሮሜ ፫፥፭–፰።ሮሜ ፫፥፭–፰ ጋር አነጻፅሩ

ሰው መልካም ነገርን ለማምጣት ክፉ ማድረግ እንደማይችል ጳውሎስ አስተማረ።

ነገር ግን በዓመፃችን ቀርተን እና የእግዚአብሔርን ጽድቅ የምናሞግስ ከሆንን፣ ቍጣን የሚያመጣ እግዚአብሔር ዓመፀኛ ነው ለማለት እንዴት እንደፍራለን? (እግዚአብሔርን እንደሚፈራ ሰው እላለሁ፣)

እንዲህ አይሁን፤ እንዲህ ቢሆን እግዚአብሔር በዓለም እንዴት ይፈርዳል?

በእኔ ውሸት (ይህም በይሁዳዎች እንደዚህ ነው የሚጠራው) ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ፣ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኃጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል? እናም አንቀበልም? እንዲሁ ይሰድቡናልና።

አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና፣ (የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው) መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም። ግን ይህ ሀሰት ነው።