2010–2019 (እ.አ.አ)
መለኮታዊ እርካታ የለሽነት
ጥቅምት 2018 (እ.አ.አ)


መለኮታዊ እርካታ የለሽነት

መለኮታዊ እርካታ ማጣት በእምነት እንድንተገብር ይገፋናል፣ የክርስቶስ መልካም አድርጉ ግብዣን እንከተላለን እንዲሁም ህይወታችንን ለእርሱ በትህትና እንሰጠዋለን።

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ በኮረብታው ጎን በተነጠፈ መንገድ ላይ ወደ ቤት እንሄድ ነበር። ሌላ መንገድ ነበር ያልተነጠፈ፣ ይህ መንገድ የወንዶቹ መንገድ ተብሎ ይጠራ ነበር። የወንዶቹ መንገድ ጭቃ እና ውደ ኮረብታው ቀጥ ብሎ ወደ ላይ የሚሄድ ነው። አጭር ነበር ግን የበለጠ ዳገታማ ነበር። እንደ ወጣት ሴትነቴ ወንዶቹ የሄዱበትን መንገድ ሁሉ መሄድ እንደምችል አውቅ ነበር። ከዚህም በበለጠ በመጨረሻው ዘመን እንደምኖር እናም ፈርቀዳዶቹ እንዳደረጉት እኔም ከባድ ነገር ማረግ እንዳልብኝ አውቅ ነበር - እናም መዘጋጀት ፈልጌ ነበር። አንዳንዴ በምንሄድበት መንገድ ላይ ከቡድኔ ጓደኞች ወደኋላ በመቅረት ጫማዬን አውልቄ በወንዶቹ መንግድ ላይ እጓዝ ነበር። እግሬን ለማጠንከር ነበር ሙከራዬ።

እንድ ፕራይመሪ ሴት ልጅ ይሄንን ማድረግ ያዘጋጀኛል ብዬ አስቤ ነበር። አሁን ግን ማውቀው የተለየነው። በተራራ መንገድ ላይ በባዶ እግር ከመሄድ ይልቅ፤ የመንፈስ ቅዱስን ግብዣ መልስ በመስጠት በቃልኪዳን መንግድ ላይ በመጓዝ እግሬን ማዘጋጀት እንደምችል አውቃለሁ። ጌታ በነብያቱ አማካኝነት እያንዳንዳችንን “በከፍታ እና በተቀደሰ” መንገድ እንድንኖር እና “አንድ እርምጃ ወደላይ” እንድንወጣ ጠርቶናል። 1

እነዚህ ትንቢታዊ ጥሪዎች ለድርጊት፣ ከውስጥ ከመነጨ ስሜት ጋር የበለጠ ማድረግ እና መሆን እንችላለን በማለት ኤልደር ኔል ኤ. ማክስዌል ብለው እንደጠሩት “መለኮታዊ አለመርካት” አንዳንዴ ሊፈጥርብን ይችላል።2 መለኮታዊ አለመርካት የሚመጣው “ያሁን ማንነታችንን መሆን ከምንችለው ማንነት ጋር ስናነጻጽር ነው።3 እያንዳንዳችን እውነተኞች ከሆንን አሁን ባለንበት እና ያሁን ማንነታችን መሆን ከሚግባን ቦታ እና ማንነት ጋር ያለውን ክፍተት ይሰማናል። ለበለጠ ግለሰባዊ አቅም እንሻለን። ይሄን አይነት ስሜት የሚኖረን የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች ስለሆንን እና ከክርስቶስ ብርሀን ጋር ተወልደን በወደቀው ዓለም ውስጥ ስለምንኖር ነው። እነዚህ ስሜቶች ከእግዚአብሔር የተሰጡ እና ለመተግበር ፍላጎትን የሚፈጥሩብን ናቸው።

የሴጣንን አጸፋዊ ምላሽን እና የሚያዳክሙንን ነግሮች በማወቅ እና በማስወገድ ወደ ከፍታ መንገድ የሚጠራንን መለኮታዊ ያለመርካት ስሜቶችን ልንቀበል ይገባል። ይሄ ድንቅ ቦታ ላይ ነው ሴጣን ዘሎ መግባት የሚፈልገው። እግዚአብሔርን እና ሰላሙን እና ጸጋውን እንድንሻ ወደ ሚመራን ከፍታ መንገድ መምረጥ እንችላለን፤ ወይንም ደግሞ በሀብት፣ በጥበብ፣በቁንጅና እና በምንም ነገር ፈጽሞ ብቁ አይደላችሁም በምል መልክቶች የምደበድበንን ሴጣንን ምስማት እንችላለን። የእኛ አለመርካት መሎኮታዊ ወይም አጥፊያችን ሊሆን ይችላል።

በእምነት መተግበር

የሰይጣን ሐሰትን ከመለኮታዊ አለመርካት መግለጫ አንደኛው መንገድ መለኮታዊ አለመርካት ወደ ታማኝ እርምጃ እንደሚመራን ነው። መለኮታዊ እርካታን ማጣት በተመቻችንበት ቦታ ላይ እንድንቆይ አይጋብዝም ወይንም ወደ ተስፋ ማጣት አይመራንም። እኔ ሰላልሆንኳቸው ነገሮች በማሰብበት ጊዜ፣ እንደማልሻሻል ተምሪያለሁ፣ እናም ንፈስን ለማዳመጥ ሆነ ለመከተል ከባድ ይሆናል።4

በወጣት እድሜው ጆሴፍ ስሚዝ ያለባቸውን ድክመቶች ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበር እና “ስለዘላለማዊ ነፍሱ ነፍሱ ደኅንነት” ተጨነቀ። በራሱም ቃላትም፣ “የራሴ ሀጥያት በማወቅ አይምሮዬ እጅጉን ተጨነቀ ለራሴ እና ለአለም ሀጥያት ማዘንን ፈለኩ።”5 ይህም ወደ አመረረ ማሰላሰል እና ትልቅ አለመረጋጋት መራው።6 ይህ ነገር ታውቁታላችሁ? በድክመታችሁ ምክንያት ትረበሻላችሁ ወይም ትጨነቃላችሁ?

እንግዲህ ጆሴፍ የሆነ ነገር አድርጓል። እንዲህም ተካፈለ፣ “ምን መደረግ አለበት? ስል ለራሴ አብዝቼ እላለሁ።”7 ጆሴፍ በእምነት ተገበረ። ወደ ቅዱስ መፅሀፉ ተመልሶ ከያዕቆብ 1፥5 ያለውን ግብዣ አነበበ እናም ወደ እግዛብሔር እርዳታ ሄደ። የራዕዩም ውጤት ለወንጌል መመለስ ምክንያት ሆነ። የጆሴፍ ስሚዝ መለኮታዊ እርካታን ማጣት፣ አለመረጋጋትና ግራ መጋባት፣ እምነት ወደተሞላው ድርጊቱ ስለመራው አመስጋኝ ነኝ።

ጥሩን ለማድረግ የመንፈስን መነሳሳት ተከተ።

ብዙውን ጊዜ አለም አስተሳሰባችንን ወደ ውስጥ እና ወደ ኋላ እኔ ማን ነኝ፣ እኔ ምንስ አይደለሁም፣ እናም እኔ የምፈልገው በሚሉ ሀሳቦች በማዞር እና በግል በማኖር የአለመካታን ስሜት ራስን ለመደድ እንደ ምክንያት ይጠቀማል። መለኮታዊ አለመርካት “መልካም ስራ ሁሉ አርጎ ያለፈውን” የእየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ እንድንከተል ይገፋፋናል።8 የደቀመዝሙርነትን መንገድ ስንጓዝ፣ ሌሎችን እንድንደርስላቸው መንፈሳዊ ግፊት እናገኛለን።

ከአመታት በፊት የሰማሁት ታሪከ የመንፈስ ቀዱስን ግፊት እንዳውቅ እና እንድተገብር እረድቶኛል። እህት ቧኒ ዲ. ፓርኪን የቀድሞው የሴቶች መረዳጃ ክፍል ጠቅላይ ፕሬዝዳንት የሚከተለውን አካፍላ ነበር፥

“ሱዛን … ድንቅ ልብስ ሰፊ ነበረች። ፕሬዝዳንት [ስፔንሰር ደብሊው.] ኪምቦል በእሷ ዋርድ ይኖር ነበር። አንድ እሁድ ሱዛን አዲስ ሱፍ እንደለበሰ አስተዋለች። አባቷ በቀርቡ አንድ ድንቅ የሐር ጨርቅ አምጥቶላት ነበር። ሱዛን ጨርቁ ፕሬዝዳንት ኪምቦል ከለበሱት ሱፍ ጋር የሚሄድ አንድ ቆንጆ ከረባት እንደሚወጣው አሰበች። ስለዚሀ ሰኞለት ከረባቱን ሰፋችው። በሶፍት ጠቅልላው ወደ ፕሬዝዳንት ኪምቦል ቤት አመራች።

“እየሄደች እያል እኔ ለነብዩ ከረባት ለመስራት እኔ ማን ነኝ” ስትል ቆም ብላ አሰበች። በጣም ብዙ ሊኖረው ይችላል። ስህተት እንደሠራች በመወሰን ለመመለስ መንገድ ጀመረቸ።

“ሲስተር ኪምቦል የፊት ለፊቱን በር ከፍታ ኦ ሱዛን አለች!”

“በመደናበር “ፕሬዝዳንት ኪምቦልን አዲሱን ሱፋቸውን ለብሰው እሁድለት አይቻቸው ነበር አለች ሱዛን። አባቴ ከኒዎርክ የሐር ጨርቅ አምጥቶልኝ ነበር እናም ከረባት ሰራሁላቸውም።’

“ሱዛን ማውራቷን ከመቀጠሏ በፊት፣ እህት ኪምቦል አስቆመቻት እና ትክሻዋን በመያዝ፡ “መቼም ቢሆን የደግነትን ሀሳብን አትከላከይ” አለቻት።9

ያንን ትምህርት እወደዋለው! “መቼም ቢሆን የደግነትን ሀሳብን አትከላከይ።” አንዳንዴ ለሰዋች የሆነ ነገር ማድረግ መነሳሳት ሲኖረኝ ይሄ ሀሳብ ከኔ ነው ወይስ ከመንፈስ ነው ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን እንዲህ እንዳስታውስ ተደርጌአለሁ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ያለማቋረጥ መልካምን እንዲሰሩ ይጋብዛል እናም ይገፋፋል፤ ስለዚህ፣ ማንኛውም ነገር መልካምን ለመስራት የሚጋብዝ እናም የሚገፋፋ፣ እናም እግዚአብሔርን እንድናፈቅር፣ እናም እንድናገለግለው የሚያደርግ ከእግዚአብሔር የሆነ ነው።”10

ነገርግን ይህን አስታወሰኝ፣ የእግዚአብሔር የሆነ ያለማቋረጥ መልካምን እንዲሰሩ ይጋብዛል እናም ይገፋፋል፤ ስለዚህ፣ ማንኛውም ነገር መልካምን ለመስራት የሚጋብዝ እናም የሚገፋፋ፣ እናም እግዚአብሔርን እንድናፈቅር፣11 እናም እንድናገለግለው የሚያደርግ ከእግዚአብሔር የሆነ ነው።

ብዙውን ጊዜ ሰአቱ አመቺ አይደለም፣ እናም የኛ ትንሽዬ አገልግሎት ያላትን አስተዋጻኦ በትንሹ ሊሆን ይችላል ምናውቀው። ነገር ግን አንዳንዴ በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ መሳሪያ እንደሆንን ይሰማናል እናም የመንፈስ ቅዱስ በኛውስጥ መስራት የእግዚአብሔር ፍቃድ መገለጫ መሆኑን በማወቃችን አመስጋኝ እንሆናለን።

እህቶች፣ ልናደርግ ያሰብ ነው ብዙ ቢሆን እንኳ እኔ እና እናንተ “ማድረግ ምንችለውን ሁሉ”12 እንዲያሳየን ለመንፈስ ቅዱስ መጸለይ አለብን። መንፈስ ሲያነሳሳን ሲንኩን የሞላውን ያልታጠበ እቃ ትተን፣ ለልጅ እናምብብ ፤ ጓደኛችንን እንጎብኝ፣ የጎረቤትን ልጅ እንያዝ ወይም ቤተመቅደስ ሄደን እናገልግል። አትሳሳቱብኝ፣ እኔ መረጃን ሰሪ ነኝ፤ ነገሮችን አንድ በአንድ ማጣራትን እወዳለሁ። ነገር ግን ሰላም የሚመጣው ብዙ መሆን ብዙ ከማድረግ ጋር አንድ እንደማይሆን በመረዳት ነው። ለእርካታ ማጣቴ መፍትሄው መንፈስን በመከተል “ስለ እራሴ ጊዜ” ያለኝን አስተሳሰብ ቀይሮታል እናም ሰዎችን እንደ ጊዜ ፈጂ ሳይሆን በህይወቴ ውስጥ አላማ እንዳላቸው ማየት ጀመርኩ።

መለኮታዊ እርካታ ማጣት ወደ ክርስቶስ ይመራል

መለኮታዊ እርካታ ማጣት ወደ ትህትና ይምራል፣ ሁልጊዜ አይሞላልኝም ብለን በማነጻፀር ከሚመጣው ወደ ለራስ ማዘን ወይም ወደ ተነሳሳሽነት ማጣት አይመራንም። ቃል ኪዳን የሚጠብቁ ሴቶች በሁሉም መጠን እና ቅርፅ ይመጣሉ፤ ቤተሰቦቻቸው፣ አጋጣሚዎቻቸውም፣ እና ጉዳዮቻቸውም ይለያያሉ።

በእርግጥም፣ ሁላችንም ከመለኮታዊ እጣ ፈንታችን የቀነስን ነን፣ እናም በብቻችን ለሁሉም ብቁ እንደማይሆን በምንረዳበት እውነትም ይገኛል። ነገር ግን የወንጌል መልካም ዜናም በእግዚአብሔር ጸጋ በኩል እና የሚበቃ እንደሆንን ነው። በክርስቶስ ረዳታ፣ ሁሉንም ነገሮች ለማድረግ እንችላለን።13 ቅዱሳት መጻህፍት “ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እናገኛለን” ብለው ቃል ይገባሉ።14

የሚያስደንቀው እውነት ደካማነቶቻችን ትሁት ሲያደርጉን እና ወደ ክርስቶስ ሲያዞሩን በረከታችን መሆናቸው ነው።15 እርካታ ማጣት መለኮታዊ የሚሆነው ለራስ በማዘን ሳይሆን ምንፈልገውን በመያዝ ወደ ክርስቶስ መቅረብ ነው።

እንደውም የክርስቶስ ተአምራቶች የሚጀምሩት ከመፈለግ፣ ከመሻት ውይም ካለእውቀት በመሆን ነው። ስለ አሳዎቹ እና ስለ ዳቦው ታስታውሳላችሁ? እያንዳንዱ የወንጌል ጸሀፊዎች እየሱስ ሲከተሉት የነበሩትን ሺዎች እንዴት በተአምር እንደመገበ ይናገራሉ።16 ነገር ግን ታሪኩ የሚጀምረው ደቀመዛምርቱ እንዳጡ በማውቃቸው ነው፤ ያላቸው “አምስት የገብስ ዳቦ እና ሁለት ትንንሽ አሳዎች” እንደነበር ተገነዘቡ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል?17 ደቀመዛምርቱ ልክ ነበሩ በቂ ምግብ አልነበራቸውም፣ ነገር ግን ያላቸውን ለእየሱስ ሰጡት እናም እርሱ ተአምሩን ሰረ።

ወደፊት ላለው ስራ ያላችሁ ተሰእጦ እን ችሎታ ትንሽ ነው ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? እኔ አውቃለሁ። ነገር ግን እኔ እና እናንተ ያለንን ለክርስቶስ በመስጠት እሱ ያበዛልናል። ምትሰጡት ከበቂ በላይ ነው እንደ ሰውነታች አቅም ባይኖረንም እና ደካማ ብንሆን እንኳ በእግዚአብሔር ፀጋ ላይ መሞርኮዝ አለብን።

እውነታው እያንዳንዳችን ከመለኮታዊነት ከመሆን አንድ ትውልድ ብቻ ነው ወደኋላ ያለነው፣ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።18 በዘመናት ሁሉ ለተራ ወንድ እና ሴት እና ለነብያት በሙሉ እንዳደረገው፣ እግዚአብሔር እኛን ለመቀየር ፍላጎት አለው።

ሲ. ኤስ. ሊዊስ የእግዚአብሔርን የመቀየር ሀይልን እንዲህ ብሎ ተንትኖታል፤ እራሳችሁን መኖሪያ ቤት አርጋችሁ አስቡ። እግዚአብሔርም ያንን ቤት ዳግመኛ ሊገነባ መጣ። መጀመሪያ ምን እያረገ እንደሆነ ልትረዱ ትችሉ ይሆናል። በጣሪያው ላይ ያለውን ትቦ በመድፈን የሚያፈሰውን ክፍተት ያቆማል ከዛም እያለ ይቀጥላል፤ እነዚህ ነግሮች መጠገን እንዳለባቸው ታውቁ ነበር ስለዚህ አይገርማችሁም። ነገር ገን አሁን ቤቱን በሚጎዳ መልኩ መምታ ይጀምራል። አያችሁ እናንተ ካሰባችሁት የተለየ ሌላ ቤት ነው ሚሰራው። እናንት ወደ አንድ ጥሩ ትንሽ ጎጆ ምትገነቡ ነበር የመሰላችሁ እሱ ግን ቤተመንግስት ነው የሚገነባው። እራሱ መጥቶ ሊኖርበት ያስባል።19

በአዳኛችን የሀጥያት ክፍያ አማካኝነት ወደፊት ካለው ስራ ጋር እኩል መሆን እንችላለን። ነብያት የደቀመዝሙርነትን መንገድ ስንወጣ በክርስቶስ ፀጋ ልንነፃ እንችላለን ሲሉ አስተምረዋል። መለኮታዊ እርካታ ማጣት በእምነት እንድንተገብር ይገፋናል፣ የክርስቶስ መልካም አድርጉ ግብዣን እንከተላለን እንዲሁም ህይወታችንን ለእርሱ በትህትና እንሰጠዋለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Russell M. Nelson, in Tad Walch, “‘The Lord’s Message Is for Everyone’: President Nelson Talks about Global Tour,” Deseret News, Apr. 12, 2018, deseretnews.com.

  2. Neal A. Maxwell, “Becoming a Disciple,” Ensign, June 1996, 18.

  3. Neal A. Maxwell, “Becoming a Disciple,” 16; emphasis added.

  4. “ተስፋ መቁረጥ እምነትን ያዳክማል። ትንሽ ምትጠብቁ ከሆነ፣ ውጤታማነታችሁ ይቀንሳል፣ ፍላጎታችሁ ይደክማል እናም መንፈስ ቅዱስን መከተል በጣም ያዳግታችኋል።” (“What Is My Purpose as a Missionary?Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service, rev. ed. [2018], lds.org/manual/missionary).

  5. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 28.

  6. ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥8

  7. ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥10፤ አትኩሮት ተጨምሯል።

  8. የሐዋሪያት ስራ 10፥38

  9. Bonnie D. Parkin, “Personal Ministry: Sacred and Precious” (Brigham Young University devotional, Feb. 13, 2007), speeches.byu.edu.

  10. ሞሮኒ 7፥13

  11. 1 ቆሮንቶስ 13፥8

  12. 2 ኔፊ 32፥5

  13. “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊልጵስዮስ 4፥13)።

  14. ዕብራውያን 4፥16

  15. “ሰዎች ወደ እኔ ቢመጡ ድክመታቸውን አሳያቸዋለሁ። ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን እሰጣቸዋለሁ፤ እናም ፀጋዬም እራሳቸውን በፊቴ ዝቅ ላደረጉ ሁሉ በቂ ነው፤ እነርሱም በፊቴ እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ እናም በእኔም እምነት ካላቸው ደካማ የሆኑትን ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ (ኤተር 12፥27፤ ትኩረት ተጨምሯል)።

  16. ማቴዎስ 14፥13–21ማርቆስ 6፥31–44ሉቃስ 9፥10–17ዮሀንስ 6፥1–14.

  17. ዮሀንስ 6፥9

  18. ፕሬዘዳነት ቦይድ ኬ. ፓከር “የዘር ማንዘራችሁ ምንም ብዙ ቢሆን፣ ምንም አይነት ዘር ወይም ሰው ብትሆኑ የመንፈሳዊ ዘራችሁ በአንድ መስመር ይጻፋል ሲሉ አስተምረዋል። እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ናችሁ።” (“To Young Women and Men,” Ensign, May 1989, 54).

  19. C. S. Lewis, Mere Christianity (1960), 160.

አትም