የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፴፫


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፴፫፥፳፣ ፳፫።ዘፀአት ፴፫፥፳፣ ፳፫ ጋር አነጻፅሩ

ማንም ኀጥያተኛ ሰው የእግዚአብሔርን ፊት ማየት እና መኖር አይችልም።

እና ሙሴን እንዲህ አለው፣ ፊቴን በዚህ ጊዜ ልታየኝ አትችልም፣ አለበለዚያ ቁጣዬ በአንተ ላይ ደግማም ትቀጣጠላለች፣ እና አንተንና ህዝቦችህን አጠፋለሁ፤ በዚህ ጊዜ በመካከላቸው ማንም ሰው አይቶኝ አይኖርምና፣ በጣም ኀጥያተኞች ናቸውና። እና ማንም ኀጥያተኛ ሰው በምንም ጊዜ ፊቴን አይቶ፣ ወይም ማንም ኀጥያተኛ ሰው በምንም ጊዜ ፊቴን በማየት፣ እና ለመኖር አይችልም።

፳፫ እና እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፣ ጀርባዬንም ታያለህ፣ ፊቴን ግን እንደሌላው ጊዜ አይታይም፤ በህዝቦቼ እስራኤል ተናድጃለሁና።