ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፮፥፩–፲። ከዕብራውያን ፮፥፩–፲ ጋር አነጻፅሩ
የክርስቶስ ትምህርት መሰረታዊ መርሆች ወደ ፍጹምነት ይመራሉ።
፩ ስለዚህ የክርስቶስ መሰረታዊ መርሆችን ሳንተው ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ ከሞተ ሥራ ንስሐ፣ እና በእግዚአብሔር እምነት መሠረትን ደግመን አንመሥርት።
፪ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርትም።
፫ እግዚአብሔርም ቢፈቅድ ወደ ፍጻሜም እንሄዳለን።
፬ አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን፣
፭ መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን፣
፮ በኋላም የካዱትን በንስሐ እንደገና እንዲታደሱም የማይቻል አድርጓል፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታል፣ እናም ያዋርዱትማልና።
፯ ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ ለሚኖሩባትም የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፣ በእሳትም የምትጸዳበት ቀን ይመጣል።
፰ እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፤ ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያመጡ፣ ወደ እሳት ይጣላሉ፤ መጨረሻቸውም መቃጠል ነው።
፱ ስለ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ምንም እንኳ እንዲሁ ብንናገር፥ አብልጦ የሚሻለውና ለመዳን የሚሆነው እንዲሆንላችሁ ተረድተናል።
፲ ስለዚህ እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።