ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፯፥፫። ከዕብራውያን ፯፥፫ ጋር አነጻፅሩ
መልከ ጼዴቅ በእግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ቅዱሱ ካህን ነበር። ይህን ክህነት የሚቀበሉ ኁሉ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ይችላሉ።
፫ ይህ የመልከ ጼዴቅ አባትና እናት የትውልድም ቍጥር እንደሌለው፣ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ እንደሌለውም፣ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ወደካህንነት ተሾመ። እና ወደ ክህነት የተሾሙት ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ ተመስለው ለዘላለም ካህን ሆነው ይኖራሉ።
ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፯፥፲፱–፳፩። ከዕብራውያን ፯፥፲፱–፳፩ ጋር አነጻፅሩ
ህግ “ለሚሻል ኪዳን ዋስ” ለሆነው ለኢየሱስ ህዝብን አዘጋጀ።
፲፱ ሕጉ ያለ መሀላ ይፈጸማል እናም ምንም ፍጹም አላደረገምና፣ ግን ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።
፳ ይህ ሊቀ ካህን ያለ መሐላ እንደማይሆን፤ በዚህም ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
፳፩ (እርሱ ግን፣ ጌታ፣ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሐላ ካህን እንዳልሆነ መጠን፤)
ጆ.ስ.ት.፣ ዕብራውያን ፯፥፳፭–፳፮። ከዕብራውያን ፯፥፳፮–፳፯ ጋር አነጻፅሩ
ክርስቶስ ለኃጢያቶቻችን እራሱን ኃጢያት እንደሌለው መስዋዕት አቀረበ።
፳፭ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ገዢ የሆነ፣ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህን እንድንሆን ይገባልና፤
፳፮ እርሱም አስቀድሞ ለራሳቸው ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን እንደሚያቀርቡት እንደነዚያ ሊቀ ካህናት አይደለም፤ ከህዝቦች ኀጥያቶች በስተቀር፣ ለራሱ ኃጢያቶች መስዋዕት ማቅረብ የለበትም፣ ምንም ኀጥያት አያውቅምና። ራሱንም ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።