የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፲፫


ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፲፫፥፰–፲።ዮሐንስ ፲፫፥፰–፲ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ የአይሁድ ህግን ለመፈጸም የሐዋሪያትን እግሮች አጠበ።

ጴጥሮስም የእኔን እግር ማጠብ አያስፈልግህም አለው። ኢየሱስም ካላጠብሁህ፣ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም ብሎ መለሰለት።

ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ ሆይ፣ እጆቼንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሮቼን ብቻ አይደለም አለው።

ኢየሱስም እጁንና ራሱን ያጠበ፣ የሚያስፈልገው እግሩን መታጠብ ብቻ ነው፣ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፣ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው። አሁን ይህ በህጋቸው ውስጥ የአይሁድ ባህል ነበር፤ ይህም ቢሆን ኢየሱስ ይህን ያደረገው ህግ እንዲሟላ ነበር።