ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፩፥፩–፴፬። ከዮሐንስ ፩፥፩–፴፬ ጋር አነጻፅሩ
የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ተሰብኳል። መጥመቁ ዮሐንስ የክርስቶስን መንገድ የሚያዘጋጀው ኤልያስ ነው፣ እና ኢየሱስ ክርስቶስም ሁሉንም ነገሮች ደግሞ የሚመልሰው ሌላው ኤልያስ ነው።
፩ በመጀመሪያው ወንጌሉ በወልድ በኩል ተሰብኮ ነበር። እና ወንጌሉም ቃል ነበረ፣ ቃልም በወልድ ዘንድ ነበረ፣ ወልድም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፣ ወልድም ከእግዚአብሔር ነበረ።
፪ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
፫ ሁሉም ነገሮች በእርሱ ተሰርተው ነበር፤ እና ከተሰራውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልተሰራም።
፬ በእርሱ ወንጌል ነበረች፣ እና ወንጌልም ሕይወት ነበረች፣ ሕይወትም የሰዎች ብርሃን ነበረች።
፭ ብርሃንም በአለም ይበራል፣ አለምም አላስተዋለውም።
፮ ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ።
፯ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ፣ በወልድ በኩል ስለወንጌሉ ለሁሉም ይመሰክር ዘንድ፣ በእርሱ በኩል ሰዎች ያምኑ ዘንድ፣ ይህ ለምስክር ወደ አለም መጣ።
፰ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፣ እርሱ ያ ብርሃን አልነበረም፣
፱ ወደ ዓለም ለሚመጣው ሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ነበር፤
፲ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ነው። በዓለም የነበረው፣ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፣ ዓለሙም አላወቀውም።
፲፩ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
፲፪ ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ብቻ፣ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።
፲፫ እርሱም ከእግዚአብሔር ተወለደ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
፲፬ ያም ቃል ሥጋ ሆነ፣ በእኛም አደረ፣ ክብሩንም እንደ አብ አንድያ ልጅ ክብር፣ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ፣ አየን።
፲፭ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፣ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ፣ ከእኔ በኋላ የሚመጣው፣ ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና።
፲፮ በመጀመሪያም ቃል ነበረ፣ እንዲሁም በስጋ የነበረውና በአብ ፈቃድ መሰረት የተላከልን ወልድ። እና በስሙ ያመኑት ሁሉ ሙሉነቱን ተቀበሉ። እና በጸጋው በኩልም፣ ከሙላቱም፣ እንዲሁም የማይጠፋ ህይወት እና የዘለአለማዊ ህይወት፣ ሁላችንም ተቀብለናል።
፲፯ ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፣ ህይወት እና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።
፲፰ ሞትን የሚያመጣ የሥጋ ትእዛዝ ሕግ አይነት ነበርና፤ ወንጌል ግን የአብ እቅፍ በሆነው በአንድያ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጨረሻ የሌለው ህይወት ሀይል እንዳለው አይነት ነው።
፲፱ እናም ስለወልድ ምስክርን ካልመሰከረ በስተቀር፣ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በእርሱ ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው አይድንም።
፳ ይህም የዮሐንስ ምስክር ነው፣ ከኢየሩሳሌም አይሁዶች ቄሶች እና ሌዊ ወደ እርሱ ልከው ጠየቁት፤ አንት ማን ነህ?
፳፩ ኤልያስ እንደሆነ መሰከረም አልካደምም፤ ነገር ግን እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።
፳፪ እነርሱም እንኪያስ ኤልያስ ነህ? ብለው ጠየቁት። እርሱም ሁሉንም ነገሮች ደግሞ የሚመልሰው ያ ኤልያስ አይደለሁም አለ። እነርሱም ነቢዩ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም ብሎ መለሰ።
፳፫ እንኪያስ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።
፳፬ እርሱም ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረበዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።
፳፭ የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩ።
፳፮ እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ሁሉን ነገሮች ደግሞ የሚመልሰው ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት፣ አሉትም።
፳፯ ዮሐንስ መልሶ፣ እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል አላቸው፤
፳፰ እርሱም የምመሰክርለት ነው። እርሱም እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፣ ወይም ቦታውን ለመሙላት የማልችል፣ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ነቢይ፣ እንዲሁም ኤልያስ፣ ይህ ነው፤ እርሱም በውሀ ብቻ ሳይሆን፣ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃል አላቸው።
፳፱ በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፤ እነሆ የዓለምን ኃጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!
፴ ዮሐንስም ለህዝቦች ስለእርሱ እንዲህ ሲል መሰከረ፣ አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፣ ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ከእኔም በፊት ነበርና፣ አውቀውም ነበር፣ እና እርሱም ለእስራኤል ይታያል፣ ስለዚህ በውሀ ለማጥመቅ መጣሁ ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።
፴፩ ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፤ በእኔ ሲጠመቅ፣ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።
፴፪ እኔም አውቀው ነበር፤ በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ ነውና፤ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።
፴፫ እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ።
፴፬ እነዚህም ነገሮች ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቤተ ራባ ሆነ።
ጆ.ስ.ት.፣ ዮሐንስ ፩፥፵፪። ከዮሐንስ ፩፥፵፪ ጋር አነጻፅሩ
ኬፋ “ባለራዕይ” ወይም “አለት” ማለት ነው
፵፪ ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ፣ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፣ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ባለራዕይ ወይም አለት ማለት ነው። እነርሱም አሳ አጥማጆች ነበሩ። እነርሱም ወዲያው ሁሉንም ተው፣ እና ኢየሱስን ተከተሉ።