ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፲፱፥፲፭፣ ፳፩። ከራዕይ፲፱፥፲፭፣ ፳፩ ጋር አነጻፅሩ
እግዚአብሔር የክርስቶስን ቃል በመጠቀም ህዝቦችን ይመታል።
፲፭ ከአፉም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣል፣ በዚህም አሕዛብንም ይመታበታል፤ በአፉ ቃልም ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን በሚገዛ እግዚአብሔር የብርቱ ቁጣ ወይን መጭመቂያን ይረግጣል።
፳፩ የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ቃል ተገደሉ፣ ቃልም ከአፉ የሚወጣው ነበር፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።