ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፪፥፳፪። ከራዕይ ፪፥፳፪ ጋር አነጻፅሩ
ክፉዎች ወደገሀነም ይጣላሉ።
፳፪ እነሆ፣ በገሀነም ላይ እጥላታለሁ፣ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤
ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፪፥፳፮–፳፯። ከራዕይ ፪፥፳፮–፳፯ ጋር አነጻፅሩ
የክርስቶስ ትእዛዛትን በማክበር አለምን የሚያሸንፉ በሚመጣው አለም መንግስቶችን በእምነት፣ በእኩልነት፣ በፍትህ ይገዛሉ።
፳፮ ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ትእዛዛቴን ለጠበቀው፣ በብዙ መንግስትቶች ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥
፳፯ እርሱም በእግዚአብሔር ቃል ይገዛቸዋል፤ እናም እነርሱም በእጁ ውስጥ ጭቃወ እቃ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ይሆናሉ፤ እናም በእምነት፣ በእኩልነት፣ እና በፍትህ፣ እንዲሁም እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ ይገዛቸዋል።