የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፩


ጆ.ስ.ት.፣ ራዕይ ፩፥፩–፬።ራዕይ ፩፥፩–፰ ጋር አነጻፅሩ

ሐዋርያው ዮሐንስ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ትንቢቶች ተቀበለ። በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመልአክ ተጎበኘ።

ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ፣ በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ ያመለከተው፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠው የእግዚአብሔር አገልጋይ የዮሐንስ ራዕይ፣

እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ የመሰከረው።

የጌታ መምጫ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነቡት የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና የሚረዳቸው፣ በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።

አሁን ይህ ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ ቤተክርስቲያናት አገልጋዮች የሰጠው ምስክር ነው። ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፣ የሰባት ቤተክርስቲያናት ሰባት አገልጋሎች ለሆኑት እንደመሰክሩ በዙፋኑም ፊት መላእክቱን ከላከው፣ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ስለዚህ፣ እኔ፣ ዮሐንስ፣ ታማኝ ምስክር፣ ከመላእክ እና ከሙታንም በኵር እና የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ስለተሰጡኝ ነገሮች እመሰክራለሁ።

ለወደደን፣ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፣ ለእግዚአብሔር ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፣ ክብር ይሁን። ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።

እነሆ፥ በደመና በመንግስት ውስጥ ካሉት አስር ሺህ ቅዱሳን ጋር፣ በአባቱ ክብር ተለብሶ ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ ያዩታል፤ እና የወጉትም፣ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። እንዲሁም ይሁን፣ አሜን።

እንዲህም ብሏልና፣ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ።