ቅዱሳት መጻህፍት
ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ፩


ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ

በ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተገለጠለት የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ልዩ እትም፥ ማቴዎስ ፳፫፥፴፱ እና ምዕራፍ ፳፬

ምእራፍ ፩

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት አስቀድሞ ነገራቸው—ስለሰው ልጅ ስለክፉው መጥፊያ ዳግም ምፅዓት፣ እና ስለክፉዎች ጥፋት አስተማረ።

እላችኋለሁና፣ በጌታ ስም በሰማይ ደመናዎች ውስጥ፣ እና ሁሉም ቅዱስ መላእክት ከእርሱም ጋር የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም እና በነቢያት ስለእርሱ ነው የተጻፈው ብላችሁ ልታውቁኝ አትችሉም። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል በክብር ዘውድ ተጭኖለት ዳግም ተመልሶ እንደሚመጣ ገባቸው።

ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ እና ደቀ መዛሙርቱም የሚለውን ለመስማት ወደእርሱ መጥተው እንዲህ አሉ፥ መምህር፣ ስለቤተመቅደሱ ህንጻ አሳየን፣ አንተ እንዳልከው—እነርሱም ይፈርሳሉ፣ እና የተፈታ ሆኖ ትቀርላቸዋለች።

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አታዩም፣ እና አይገቧችሁምን? እውነት እላችኋለሁ፣ ከዚህ ቤተመቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የሚቀር አይኖርም።

እና ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፣ እና ወደ ደብረ ዘይት ተራራም ሄደ። በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፣ ስለ ቤተመቅደሱ መፍረስና ስለ አይሁድ በተመለከተ ያልካቸው እነዚህ ነገሮች መቼ እንደሚሆኑ ንገረን፤ እና የአንተ ደግሞ መመለሻና የአለም መጨረሻ፣ ወይም የአለም መጨረሻ የሆነው የክፉዎቹ መጥፊያ ምልክትስ ምንድን ነው? አሉት።

እና ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤

ብዙዎች በስሜ—እኔ ክርስቶስ ነኝ—በማለት ይመጣሉና፣ እና ብዙዎችንም ያስታሉ፤

ከዚያም በስሜ ምክንያትም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፣ እናም ይገድሏችኋል፣ እናም በህዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤

እና ብዙዎችም ይቀየማሉ፣ እና እርስ በራስ ይክዳሉ፣ እርስ በራስም ይጣላሉ፤

እና ብዙ ሐሰተኛ ነቢያትም ይነሳሉ፣ እና ብዙዎችንም ያስታሉ፤

እና ክፋት በብዛት ስለሚገኝ፣ የብዙዎችም ፍቅር ትቀዘቅዛለች፤

፲፩ በፅናት የሚቋቋመውና የማይሸነፈው ግን፣ እርሱ ይድናል።

፲፪ ኢየሩሳሌምን በሚመለከት በጥፋት ነቢዩ ዳንኤል የተናገረውን የጥፋት ርኩሰት ስታዩ፣ ከዚያም በተቀደሰ ስፍራም ቁሙ፤ ይህን የሚያነብ ይግባው።

፲፫ ከዚያም በይሁዳ የሚገኙ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤

፲፬ በቤቱ ጣራ ላይ የሚገኝ ማንም ሰው እቃውን ከቤቱ ለማውጣት አይውረድ፤

፲፭ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

፲፮ በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤

፲፯ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤

፲፰ በዚያን ጊዜ ከመንግስታቸው መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከእግዚአብሔር ወደ እስራኤል ተልኮ ያልነበረ ታላቅ ስቃይ በአይሁዶች፣ እና በኢየሩሳሌም ኗሪዎች ላይ ይደርሳል፤ ከዚህም በኋላ በእስራኤል ላይ እንደገና አይላክም።

፲፱ እነርሱ ላይ የደረሱባቸው ገና ከሚመጡባቸው ሀዘን የመጀመሪያዎቹ ናቸው።

እና እነዚያ ቀናትስ ካላጠሩ በስተቀር፣ ሥጋ ከለበሰ የሚድን ማንም አይኖርም፤ ነገር ግን እነዚያ ቀናት ለተመረጡ ሰዎች፣ በቃል ኪዳን መሰረት፣ ያጥራሉ።

፳፩ አይሁዶችን በሚመለከት የነገረኳችሁ እነዚህን ነገሮች ተመልከቱ፤ ደግሞም በኢየሩሳሌም ላይ ከሚመጡት ከእነዚያ ቀናት በኋላ፣ ማናችሁም አስተውሉ ክርስቶስ በዚህ አለ ወይም በዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤

፳፪ በእነዚያ ቀናት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉና፣ ቢቻላቸውም፣ በቃል ኪዳን መሰረት ምርጥ የነበሩትን፣ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅን ያሳያሉ።

፳፫ እነሆ፣ እነዚህን ነገሮች የምነግራችሁ ለተመረጡት ጥቅም ነው፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰማላችሁ፤ አትጨነቁም፣ የነገርኳችሁ ሁሉ መፈጸም አለባቸውና፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።

፳፬ እነሆ፣ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፤

፳፭ ስለዚህ፣ እነሆ፣ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፣ አትውጡ፥ እነሆ፣ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፣ አትመኑ፤

፳፮ የጠዋት ብርሀን ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚያበራ፣ እና ምድርን በሙሉ እንደሚሸፍን፣ የሰው ልጅ ምፅዓትም እንዲሁ ይሆናልና።

፳፯ አሁንም ምሳሌ አሳያችኋለሁ። እነሆ፤ ቅሪቶች ባሉበት፣ አሞራም አብረው ይሰበሰባሉ፣ እንደዚህም የእኔ ምርጦች ከአራቱ የምድር ማዕዘናት ይሰበሰባሉ።

፳፰ እና ጦርንም የጦርንም ወሬ ይሰማሉ።

፳፱ እነሆ፣ የምናገረው ለምርጦቼ ጥቅም ነው፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፣ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤

ደግሞም ከዓመፃ ብዛት የተነሣ የሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች፤ እስከ ፍጻሜው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

፴፩ ደግሞም፣ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፣ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ወይም የክፋተኞቹ ጥፋት ይመጣል።

፴፪ ደግሞም በነቢዩ በዳንኤል የተነገረው የጥፋት ርኩሰትም ይፈጸማል።

፴፫ ከዚያች መከራ ቀናት በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፣ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፣ እና የሰማይ ሀይላትም ይናወጣሉ።

፴፬ በእውነት እላችኋለሁ፣ የነገርኳችሁ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ፣ እነዚህ ነገሮች የሚታዩባቸው ይህ ትውልድ አያልፍም።

፴፭ ምንም እንኳን ሰማይና ምድር የሚያልፉበት ቀን ቢመጣም፣ ቃሌ ግን አያልፍም፣ ነገር ግን ሁሉም ይፈጸማሉ።

፴፮ አስቀድሜ እንዳልኳችሁ፣ ከዚያች የመከራ ቀናት በኋላ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ፣ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፣ ከዚያም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤

፴፯ እና ቃላቶቼን እንደ ሀብት የሚያከማቸው ማንም አይታለልም፣ የሰው ልጅም ይመጣልና፣ እና መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፣ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ

፴፰ አሁን የበለስ ዛፍን ምሳሌ ተማሩ—ቅርንጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤

፴፱ እንደዚሁም እነዚህን ሁሉ ምርጦቼ ሲያዩ፣ እርሱ በደጅ እንደቀረበ፣ እንዲሁም በበር ላይ እንዳለ ያውቃሉ፤

ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ከአባቴ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ማንም የሚያውቅ የለም።

፵፩ በኖህ ዘመን እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፤

፵፪ ከጥፋት ውሃ በፊት እንደነበረም ይሆንላቸዋል፤ ኖህ ወደ መርከቡ እስከገባበት ቀናት ድረስም ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ ነበሩና፤

፵፫ እና የጥፋት ውኃም መጥቶ፣ ሁሉን እስከ ወሰዳቸው ድረስ አላወቁም፤ የሰው ልጅ መምጣትም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

፵፬ ከዚያም የተጻፈው ይፈጸማል፣ በመጨረሻዎቹም ቀናት ሁለት ሰዎች በዕርሻ ላይ ይሆናሉ፣ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል

፵፭ ሁለቱ በወፍጮ ይፈጫሉ፣ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች።

፵፮ እና እኔ ለአንዱ የምለውን፣ ለሁሉም ሰዎች እላለሁ፤ ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ

፵፯ ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ ይነቃ ነበር፣ እና ቤቱም እንዲፈርስ አይፈቅድም ነበር፣ ነገር ግን ይዘጋጅም ነበር።

፵፰ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጁ፣ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

፵፱ በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ባለቤቱ በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ብልህ አገልጋይ ያደረገው እንግዲህ ማን ነው?

ባለቤቱ ተመልሶ ሲመጣ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ የተባረከ ነው፤ እና እውነት እላችኋለሁ፣ በእቃዎቹ ሁሉ ላይ ገዢ እንዲሆን ይሾመዋል።

፶፩ ነገር ግን ያ ክፉ ባርያ በልቡ እንዲህ ቢል፥ ጌታዬ መመለሻው ይዘገያል

፶፪ እና የባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ፣ እና ከሰካሮችም ጋር ሊበላና ሊጠጣ ጀመረ፣

፶፫ የዚያ ባርያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን፣ እና ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፣

፶፬ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፣ እና እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

፶፭ በሙሴ ትንቢት መሰረት፣ እንደዚህም የክፉዎች መጨረሻ ይመጣል፣ ብሏል፥ ከሰዎች መካከል ይቆረጣሉ፤ ነገር ግን የምድር መጨረሻው ገና አይደለም፣ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነው።