ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፲፪


ምዕራፍ ፲፪

ነቢዩ ኤተር ህዝቡ በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አበረታታ—ሞሮኒ አስገራሚ የሆኑትን እናም በእምነት የተሰሩትን ድንቅ ነገሮች አስታወሰ—የያሬድ ወንድም እምነቱ ክርስቶስን ለማየት አስቻለው—ጌታ ሰዎች ትሁት ይሆኑ ዘንድ ድካምን ይሰጣቸዋል—የያሬድ ወንድም የዜሪንን ተራራ በእምነት አንቀሳቀሰ—እምነት፣ ተስፋ፣ እና ልግስና ለደህንነት አስፈላጊ ናቸው—ሞሮኒ ኢየሱስን ፊት ለፊት አየው።

እናም እንዲህ ሆነ የኤተር ዘመን በቆሪያንተመር ዘመን ነበር፤ እናም ቆሪያንተመር በምድሪቱ በሙሉ ላይ ንጉስ ነበር።

እናም ኤተርም የጌታ ነቢይ ነበር፤ ስለዚህ ኤተር በቆሪያንተመር ዘመን ተነሳ፤ እናም ለህዝቡ መተንበይ ጀመረ፣ በውስጡ በነበረው የጌታ መንፈስ መንስኤ ሊታገት አይቻልምና።

እርሱም ከማለዳ ጀምሮ ፀሐይ እስከምትጠልቅ ህዝቡም ንሰሃ በመግባት በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አለበለዚያ እንደሚጠፉ በመምከር፣ ለእነርሱም በእምነት ሁሉም ነገሮች ለመሟላት እንደሚችሉ በመንገር ጮኸ

ስለሆነም፣ በእግዚአብሔር የሚያምን በእርግጥ ለተሻለ ዓለም፣ አዎን፣ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ያለውን ስፍራ እንኳ ለማግኘት ተስፋ ይኖረዋል፤ ይኸውም ተስፋ በእምነት የሚመጣ ነው፤ ተስፋም ለሰዎች ነፍስ እንደመሃልቅ ነው፤ እነርሱንም ፅኑ እና የማይነቃነቁ እንዲሆኑ እናም ሁልጊዜም በርካታ መልካም ነገሮችን እንዲሰሩ፤ እግዚአብሔርንም እንዲያከብሩ ያደርጋቸዋል።

እናም እንዲህ ሆነ ኤተር ታላቅ እና አስገራሚ ነገሮችን ለህዝቡ ተነበየላቸው፤ እነርሱ ግን ስላላዩት አላመኑበትም።

እናም አሁን፣ እኔ ሞሮኒ፣ ስለነዚህ ነገሮች በመጠኑ እናገራለሁ፤ እምነት ተስፋ የምናደርጋቸው ነገሮች ነገር ግን የማናያቸው መሆኑን ለዓለምም አሳያለሁ፤ ስለዚህ፣ ስላላያችሁ አትከራከሩ፣ ምክንያቱም እምነታችሁ እስከሚፈተን ድረስ ምስክርነትን አትቀበሉምና።

ምክንያቱም ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በኋላ እራሱን ለአባቶቻችን ያሳየው በእምነት ነበር፤ እነርሱም በእርሱ እምነት እስከሚኖራቸው ድረስ እራሱን አልገለፀላቸውም፤ ስለሆነም፣ አንዳንዶቹ በእርሱ ላይ እምነት ሳይኖራቸው አልቀረም፣ ምክንያቱም እራሱን ለዓለም አላሳየምና።

ነገር ግን ሰዎች በማመናቸው እራሱን ለዓለም አሳይቷል፣ እናም የአብንም ስም አክብሯል፣ እና ሌሎች ከሰማያዊው ስጦታ ይካፈሉ ዘንድ፣ ባልተመለከቷቸውም ነገሮች ተስፋ ያደርጉ ዘንድ መንገዱን አዘጋጅቷል።

ስለዚህ፣ እናንተ ደግሞ ተስፋን ማድረግ፣ እናም እምነት ካላችሁ ከስጦታው ተካፋዮች ለመሆን ትችላላችሁ።

እነሆ የጥንቶቹም ቅዱስ ወደሆነው የእግዚአብሔር ስርዓት የሚጠሩት በእምነታቸው ነበር።

፲፩ ስለሆነም፣ በእምነት ነበር የሙሴ ህግ የተሰጠው። ነገር ግን እግዚአብሔርም በልጁ ስጦታም ይበልጥ የተመረጠውን መንገድ አዘጋጅቷል፤ እናም ይህም የተሟላው በእምነት ነው።

፲፪ በሰው ልጆች መካከል እምነት ከሌለ እግዚአብሔር በመካከላቸው ተአምር መስራት አይችልም፤ ስለሆነም እስከሚያምኑ ድረስ እራሱን አልገለፀላቸውም።

፲፫ እነሆ፣ የአልማ እና የአሙሌቅ እምነትም ነው ወህኒ ቤቱ ወደምድር እንዲወድቅ ያደረገው።

፲፬ እነሆ፣ የኔፊና የሌሂ እምነት ነበር ላማናውያንን እንዲለወጡ ያደረገው፣ ስለሆነም እነርሱም በእሳት እና በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቁ።

፲፭ እነሆ፣ የአሞን እና የወንድሙ እምነት ነበር ታላቅ የሆነ ተአምር በላማናውያን መካከል የሠራው

፲፮ አዎን፣ ከክርስቶስ በፊት የነበሩትም እንኳን እናም ደግሞ ከእርሱ በኋላ የነበሩት ተአምር የሚሰሩት ሁሉም የሰሯቸው በእምነት ነበር።

፲፯ እናም ሦስቱ ደቀመዛሙርት ሞትን እንዳይቀምሱ ቃል ኪዳን የተገባላቸው በእምነት ነበር፤ እናም እምነት እስከሚኖራቸው ድረስ ቃልኪዳኑን አላገኙም ነበር።

፲፰ እናም በማንኛውም ጊዜም እንኳን እምነት እስከሚኖራቸው ድረስ ተአምራትን ማንም አልሰራም፤ ስለዚህ እነርሱ አስቀድመው በእግዚአብሔር ልጅ አምነዋል።

፲፱ እናም ክርስቶስ ከመምጣቱም በፊት እንኳን በእምነታቸው እጅግ የበረቱ ብዙዎች ነበሩ፤ እነርሱም በመጋረጃው ስር ሊጠበቁ አልተቻሉም፤ ነገር ግን በእውነትም በእምነት አይን ያዩአቸውን ነገሮች በዐይኖቻቸው አይተዋል እናም ተደስተዋል።

እናም እነሆ፣ በዚህ መዝገብ ውስጥም ከእነዚህ አንዱ የያሬድን ወንድም መሆኑን አይተናል፤ እርሱም በእግዚአብሔር እምነቱ ታላቅ በመሆኑ እግዚአብሔርም በጣቶቹ ሲያመለክት፣ ለእርሱም በተናገራቸው ቃላት ምክንያት፣ ከያሬድ ወንድም እይታ ሊደብቀው አልቻለም፤ ቃላቱንም እርሱ በእምነቱ ያገኛቸው ነበሩ።

፳፩ እናም የያሬድ ወንድም የጌታን ጣት ከተመለከተ በኋላ፣ የያሬድ ወንድም በእምነቱ ቃል ኪዳን ስለተቀበለ፣ ጌታ ከእርሱ ምንም ነገር ከእይታው ሊሰውርበትም አልቻለም፤ ስለዚህ እርሱም ሁሉንም ነገሮች አሳየው ምክንያቱም ከመጋረጃው ውጪ ከእንግዲህ ሊያስቀምጠው አይቻለውምና።

፳፪ እናም እነዚህ ነገሮች በአህዛብ አማካኝነት ለወንድሞቻቸው እንዲመጡ አባቶቻችን ቃል ኪዳንን ያገኙት በእምነት ነው፤ ስለዚህ ጌታ፣ አዎን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን፣ እኔን አዞኛል።

፳፫ እናም እንዲህ ስል ተናገርኩት፥ ጌታ ሆይ፣ ስንፅፍ ደካሞች በመሆናችን አህዛብ ይሳለቁብናል፤ ጌታ በእምነታችን በሚገባ እንድንናገር አድርጎናል፣ ነገር ግን በጽሁፍ ኃያላን እንድንሆን አላደረገንምና፤ መንፈስ ቅዱስንም ስለሰጠሃቸው እነዚህን ሰዎች ሁሉ ብዙ ለመናገር እንዲችሉ አድርገኻቸዋልና።

፳፬ እናም በእጆቻችን አስቸጋሪነት ምክንያትም ትንሽ ብቻ እንድንፅፍ አድርገኸናል። እነሆ፣ እንደያሬድ ወንድም በይበልጥ መፃፍ እንድንችል አላደረግኽንም፣ ምክንያቱም ሰዎች እንዲያነቡት የሚገፋፉበት ኃያል እንዲሆኑ እርሱ የፃፋቸውን ነገሮች እንዳንተው ሁሉ ኃያል አድርገሃቸዋል።

፳፭ ቃላቶቻችንን ደግሞ መፃፍ እስከማንችል ድረስ ኃያል እና ታላቅ አደረክ፤ ስለዚህ በምንፅፍበት ጊዜም ደካማነታችንን እንመለከታለን፣ እናም ቃላቶቹን በምናስቀምጥበትም እንደናቀፋለን፤ እናም አህዛብ በቃላችን እንደሚሳለቁብን እፈራለሁ።

፳፮ እናም ይህን በምናገርበት ጊዜ፣ ጌታ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ ሞኞች ይሳለቃሉ ነገር ግን ያዝናሉ፤ እናም ፀጋዬ ለየዋሆች በቂ ነው፣ እነርሱም በድካማችሁ ብልጫ አይወስዱባችሁም።

፳፯ እናም ሰዎች ወደ እኔ የሚመጡ ከሆኑ ድክመታቸውን አሳያቸዋለሁ። ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን እሰጣቸዋለሁ፤ እናም ፀጋዬም እራሳቸውን በፊቴ ዝቅ ላደረጉ ሁሉ በቂ ነው፤ እነርሱም በፊቴ እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ፣ እናም በእኔም እምነት ካላቸው፣ ከዚያም ደካማ የሆኑትን ለእነርሱ ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ።

፳፰ እነሆ፣ ለአህዛብ ድካማቸውን አሳያቸዋለሁ፣ እናም እምነት፤ ተስፋ እና ልግስና ወደ እኔ—የፅድቅ ምንጭ ሁሉ ወደሆነው እንደሚያመጣቸው አሳያቸዋለሁ።

፳፱ እናም እኔ ሞሮኒ፣ እነዚህን ቃላት በመስማቴ ተፅናንቼ ነበር እናም እንዲህ አልኩኝ፥ አቤቱ ጌታ የፅድቅ ፈቃድህ ይከናወናል፤ ምክንያቱም አንተ ለሰው ልጆች እንደእምነታቸው እንደምታከናውን አውቃለሁና፤

የያሬድ ወንድም የዜሪንን ተራራ ተንቀሳቀስ ሲለው—እርሱም ተንቀሳቀሶ ነበር። እናም እምነት ባይኖረው አይንቀሳቀስም ነበር፣ ስለዚህ አንተም ለሰዎች እንደ እምነታቸው ትሰራለህ።

፴፩ ምክንያቱም ለደቀመዛሙርቱም ራስህን እንደዚህ አሳይተሃል፤ ባንተም ካመኑ እናም በስምህ ከተናገሩ በኋላ ራስህን በታላቅ ኃይል አሳይተሃቸዋልና።

፴፪ እናም ደግሞ ለሰዎች ቤት፣ አዎን፣ በአባትህም ቤት እንኳን ማዘጋጀትህን መናገርህን አስታውሳለሁ፤ በዚህም ሰው የላቀ ተስፋ ይኖረው ዘንድ ነው፤ ስለሆነም ሰው ተስፋ ማድረግ ይገባዋል፣ አለበለዚያ አንተ ያዘጋጀኸውን ሥፍራ በውርስ ሊቀበል አይችልም።

፴፫ እናም በድጋሚ፣ ለሰዎች ልጆች ስፍራቸውን ለማዘጋጀት እንደገና ታነሳው ዘንድ ህይወትህን አሳልፈህ ለአለም እስከመስጠት ድረስ ዓለምን መውደድህን መናገርህን አስታውሳለሁ።

፴፬ እናም አሁን ይህ ለሰዎች ልጆች የነበረህ ፍቅር ልግስና እንደሆነ አውቃለሁ፤ ስለዚህ ሰዎች ልግስና ከሌላቸው በአባትህ መኖሪያ ያዘጋጀኸውን ስፍራ ሊወርሱ አይችሉም።

፴፭ ስለዚህ፣ እኛ ደካሞች በመሆናችን አህዛብ ልግስና ከሌላቸው ትፈትናቸዋለህ እናም ተሰጦአቸውም ይወሰድባቸዋል፤ አዎን፣ ያንን የተቀበሉትንም እንኳን፣ እናም በብዛት ላላቸውም ይጨመርላቸዋል ያልከውን በዚህ ነገር አውቀዋለሁ።

፴፮ እናም እንዲህ ሆነ አህዛብ ልግስና ይኖራቸው ዘንድ ጸጋ እንዲሰጣቸው ወደ ጌታ ፀለይሁ።

፴፯ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ ልግስና ከሌላቸው አንተ ግድ የለህም፣ አንተ ታማኝ ነበርክ፤ ስለዚህ፣ ልብስህ ይነፃል። እናም ድካምህን በማየትህ በአባቴ ቤት ባዘጋጀሁልህ ቦታ እንድትቀመጥ ጠንካራ ትደረጋለህ።

፴፰ እናም አሁን እኔ ሞሮኒ፣ አህዛቦችን አዎን እናም ደግሞ የምወዳቸው ወንድሞቼን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እስካገኛቸው እሰናበታችኋለሁ፤ በዚያም ሰዎችም በሙሉ ልብሶቼ በእናንተ ደም እንዳልተበከሉ ያውቃሉ።

፴፱ እና ከዚያም ኢየሱስን ማየቴን ታውቃላችሁ፣ እናም እርሱም ፊት ለፊት ተናግሮኛል፣ እናም እነዚህን ነገሮች በተመለከተ አንድ ሰው ለሌላ እንደሚናገርም፣ በራሴ ቋንቋ በግልፅ በትህትና ነግሮኛል፤

እናም በፅሁፍ ደካማ በመሆኔም ጥቂቱን ብቻ ፅፌአለሁ።

፵፩ እናም እንግዲህ፣ ነቢያት እና ሐዋሪያት የፃፉለትን ይህንን ኢየሱስን እንድትፈልጉት እመክራችኋለሁ፤ በዚህም የእግዚአብሔር አብ ፀጋ፣ እናም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስና፣ ስለእነርሱ የሚመሰክረው መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥና፣ ከእናንተ ጋር ለዘለዓለም ይኑር። አሜን።