ቅዱሳት መጻህፍት
አብርሐም ፪


ምዕራፍ ፪

አብርሐም ከዑር ወጥቶ ወደ ከነዓን ሄደ—ሀራን ውስጥም ያህዌህ ተገለጠለት—የወንጌል በረከቶችም ሁሉ ለዘሮቹና በዘሩም በኩል ለሁሉም ቃል ተገብተዋል—ወደከነዓንና ወደ ግብፅ ሄደ።

አሁን በዑር ውስጥ ጌታ አምላክ ረሀቡ በጣም ፅኑ እንዲሆን አደረገ፣ በዚህም ምክንያት ወንድሜ ሀራንም ሞተ፤ አባቴ ታራን ግን በከለዳ ሃገር ዑር ውስጥ መኖር ቀጠለ።

እና እንዲህ ሆነ እኔ አብርሐም ሦራን አገባሁ፣ እናም ወንድሜ ናኮር የሃራን ሴት ልጅ ሚልካን አገባ።

አሁን ጌታ እንዲህ አለኝ፥ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።

ስለዚህ ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ የከለዳውያን ዑር ምድር ትቼ ሄድኩኝ፤ እና የወንድሜን ልጅ ሎጥንና ሚስቱን እናም ሚስቴን ሦራን ይዤ ሄድኩኝ፤ እና አባቴም ሃራን ብለን ወደጠራነው ምድርም ተከተለኝ።

ረሀቡም ቀነሰ፤ እናም ብዙ መንጋዎች በሀራን ስለነበሩ አባቴም በዚያ ቆየ፤ እና አባቴ ጣኦቶችን ወደማምለክ ተመለሰ፣ ስለዚህ በሀራን ውስጥ መኖር ቀጠለ።

ነገር ግን እኔ አብርሐምና የወንድሜ ልጅ ሎጥ ወደ ጌታ ጸለይን፣ እና ጌታም ለእኔ ተገልጦ እንዲህ አለኝ፥ ተነሳ፣ እና ሎጥን ከአንተ ጋር ውሰድ፤ አንተን ከሄራን ለማውጣት እና ለዘርህ፣ ድምጼን ሲያደምጡ፣ ለዘለአለም እንዲወስዱ ለምሰጠው እንግዳ ምድር ውስጥ ስሜን የምትሸከም አገልጋይ አደርግህ ዘንድ እንድትሄድ አላማ አለኝ።

እኔ ጌታ አምላክ ነኝና፤ በሰማይም እኖራለሁ፤ ምድርም የእግሬ ማረፊያ ነች፤ እጄን በባህር ላይ እዘረጋለሁ፣ እና በድምጼም ይታዘዛል፤ ንፋሱን እሰራለሁ እና እሳትን ሰረገላዬ አድርጌአለሁ፤ ለተራሮች—ከዚህ ሂዱ—እላለሁ እና እነሆ፣ በታላቅ አውሎንፋስ ወዲያውም ይወሰዳሉ።

ስሜ ያህዌህ ነው፣ እና መጨረሻውን ከመጀመሪያው አውቀዋለሁ፤ ስለዚህ እጄም በአንተ ላይ ይሆናል።

ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፣ እና አብዝቼም እባርክሀለሁ፣ እና ስምህንም ከህዝቦች መካከል ታላቅ አደርገዋለሁ፣ እና ከአንተ በኋላ ለሚመጡ ዘሮች በረከት ሆነህ፣ እጆቻቸው ይህን አገልግሎትና ክህነትን ለሁሉም ህዝቦች ይዘው ይሄዳሉ፤

እና በስምህ በኩልም እባርካቸዋለሁ፤ ይህን ወንጌል የተቀበሉት ሁሉ በአንተ ስም ይጠራሉ፣ እና እንደ አንተ ዘር ይቆጠራሉ፣ እና እንደ አባታቸው ተነስተው ይባርኩሀል፤

፲፩ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ በአንተ (ይህም ማለት በክህነትህ በኩል) እናም በዘርህ (ይህም ማለት በክህነትህ)፣ እና ከአንተም በኋላ በዘርህ (ይህም ማለት የራስህ ዘር ወይም የሰውነትህ ፍሬዎች) በኩል ይህ መብት ይቀጥላል፣ ሁሉም የምድር ቤተሰቦች በደህንነት በረከቶች፣ እንዲሁም የዘለአለም ህይወት በሆኑት የወንጌል በረከቶች ይባረካሉ ብዬ ቃል ኪዳን ሰጥቼሀለሁ።

፲፪ አሁን ጌታ ከእኔ ጋር መናገሩን ከጨረሰ በኋላና ፊቱንም ከእኔ ከወሰደም በኋላ፣ በልቤ እንዲህ አልኩ፥ አገልጋይህ በትኩረት ፈልጎህ ነበር፤ አሁን አገኘሁህ፤

፲፫ ከኤልከናኽ አማልክቶችም እኔን ለማዳን መላእክትህን ላክ፣ እና ድምፅህን ባደምጥ ለእኔ ጥቅም ይሆናል፣ ስለዚህ አሁን ባሪያህም ይነሳ እና በሰላም አሰናብተው።

፲፬ ስለዚህ እኔ አብርሐም ጌታ እንዳለኝ ተነስቼ ሄድኩ፣ ሎጥም ከእኔ ጋር፤ እና እኔ አብርሐምም ከካራን ስሄድ ስልሳ ሁለት አመቴ ነበር።

፲፭ እና በከላውዴዎ በዑር ውስጥ እያለሁ ያገባኋት ሦራን እና የወንድሜ ልጅ ሎጥን፣ እና የሰበሰብናቸውን ነገሮች፣ እና በካራን ውስጥ ያገኘናቸውን ነፍሳት ወሰድኩ፣ እና ወደ ከነዓንም ምድር ገባን፣ እና ስንጓዝም በድንኳን ውስጥ ኖርን፤

፲፮ ስለዚህ፣ ከካራን ተጉዘን በጀርሸን በኩል ወደ ከነዓን ምድር ስንመጣም፣ ዘለአለምዊውም ከለላችን አለታችንና መድሀኒታችን ነበር።

፲፯ አሁን እኔ አብርሐም መሰዊያ በጀርሸን ምድር ውስጥ ሰራሁ፣ እና ለጌታም መስዋዕትን አቀረብኩ፣ እና እንዳይሞቱም ከአባቴ ቤት ረሀቡ ጋብ እንዲል ጸለይኩ።

፲፰ ከዚያም እስከ ሴኬም ድረስ ከጀርሸን ምድሪቱ ዘልቀን አልፈን ሄድን፤ ይህም በሞሬ ሜዳ ውስጥ የነበረ ነው፣ እና በከነዓናውያን ድንበርም ደርሰን ነበር፣ እናም በባእድ አምላኪዎች ምድር ውስጥ ስለገባን፣ በሞሬ ሜዳ አካባቢም መስዋዕትን አቀረብኩ፣ ጌታንም በመንፈሳዊ ነገር ተግቼ ጠራሁት።

፲፱ እናም ጌታ ጸሎቴን ለመመለስ ተገለጠልኝ፣ እና እንዲህም አለኝ፥ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።

እና እኔ አብርሐም ለጌታ ከሰራሁት መሰዊያ ተነሳሁ፣ በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራም ሄድኩ፣ እና ቤቴልን በምዕራብ፣ ጋይን በምስራቅ ሆኖ ድንኳኔን በዚያ ተከልኩ፤ እና በዚያም ለጌታ ሌላ መሰዊያን ሰራሁ፣ እና ደግሜም የጌታን ስም ጠራሁ

፳፩ እና እኔ አብርሐም ወደ ደቡብ መጓዝን ቀጠልኩ፤ በዚያም ምድር ውስጥ ረሀብ ይበረታ ነበር፤ እና እኔ አብርሐም ረሀቡ ፅኑ ስለነበር፣ ወደ ግብፅ ለመሄድ፣ እና ወደዚያም ለመጓዝ ወሰንኩ።

፳፪ ግብፅ ለመግባት እየቀረብኩ ስመጣም፣ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ እነሆ፣ ሚስትህ ሦራ ለመመልከት መልከ መልካም ሴት ነች፤

፳፫ ስለዚህ እንዲህ ሆነ ግብጻውያን እርሷን በሚያዩበት ጊዜ ይህች ሚስቱ ናት ይላሉ፤ እና ይገድሉሀል፣ እርሷን ግን በህይወት ይተውአታል፤ ስለዚህ እንዲህ አድርግ።

፳፬ ለግብጻውያኑ እህትህ እንደሆነች ትንገራቸው፣ ነፍስህም ትድናለች።

፳፭ እንዲህም ሆነ እኔ አብርሐም ጌታ የነገረኝን ሁሉ ለሚስቴ ሦራ ነገርኳት—ለአንቺም ደህንነት፣ እና በአንቺም ምክንያት ነፍሴ ትድን ዘንድ፣ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ እንግዲህ እህቴ እንደሆንሽ እንድትነግሪያቸው እለምንሻለሁ።