አጠቃላይ ጉባኤ
የክርስቶስ አይነት እርጋታ
የሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


የክርስቶስ አይነት እርጋታ

“ነቅቶም ንፋሱን ገሰጸው ባህሩንም፣ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ንፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ”(ማርቆስ 4፥39)።

ለመጨረሻ ጊዜ በአጠቃላይ ጉባኤ የተናገርኩ ጊዜ አማች ልጄ ራያን ከትዊተር እንዲህ የሚል አሳየኝ፣ “እውነት? የሰውየው ስም ብራግ ነው—መኩራት ማለት ነው—እና ስለ ትህትና አይናገርም? እንዴት ያለ ኪሳራ ነው!” በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ብስጭቱ እንደቀጠለ ነው።

ምስል
ዶን ብራግ እንደ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች

የኔ ድንቅ አባት በታዋቂው አሰልጣኝ ጆን ውድን ስር ለዩሲኤልኤ የመላው አሜሪካ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነበር። በአባቴ ህይወት ውስጥ በሙሉ ይቀራረቡ ነበር፣ እና አልፎ አልፎ አሰልጣኝ እና ወይዘሮ ይሆናሉ። ውድን ለእራት ወደ ቤታችን ይመጡ ነበር። ስለ ቅርጫት ኳስ ወይም ሌላ በአእምሮዬ ስላለ ስለማንኛውም ነገር ማውራት ሁልጊዜ ያስደስተው ነበር። አንድ ጊዜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ሁለተኛ አመት ስገባ ምን ምክር እንደሚሰጠኝ ጠየኩት። ሁል ጊዜ አስተማሪው እንዲህ አለ፦ “አባትህ የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን እንደተቀላቀለህ ነግሮኛል፣ ስለዚህ በጌታ ላይ እምነት እንዳለህ አውቃለሁ። በዚህ እምነት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ መረጋጋት እንዲኖርህ እርግጠኛ ሁን። በማዕበል ውስጥ መልካም ሰው ሁን።”

በዓመታት ውስጥ ያ ውይይት ከእኔ ጋር ተጣብቆ ቀረ። ይህ ምክር በሁሉም ሁኔታዎች፣ በተለይም በመከራና በችግር ጊዜ እንድሰክን፣ እንድረጋጋ እና ሰብሰብ እንድል ረድቶኛል። የአሰልጣኝ ውድን ቡድኖች ተረጋግተው እንዴት እንደተጫወቱ እና 10 ብሄራዊ ሻምፒዮናዎችን በማሸነፍ ያገኙትን ታላቅ ስኬት ማየት ችያለሁ።

ነገር ግን በዚህ ዘመን ስለ መረጋጋት ብዙ አይነገርም እናም በሁከትና ብጥብጥ እና ክፍፍል ጊዜ ውስጥ እንኳን ብዙም ተግባር ላይ አይውልም። ይህም ብዙውን ጊዜ በስፖርት ውስጥ ይጠቀሳል—እርጋታ ያለው ተጫዋች በተቀራራቢ ጨዋታ ውስጥ የሰከነ ነው ወይም ቡድን በመረጋጋት እጥረት ምክንያት ይቀላል። ነገር ግን ይህ አስደናቂ ባህርይ ከስፖርት በላይ አልፎ ይሄዳል። እርጋታ ለሕይወት በጣም ሰፊ የሆነ አተገባበር አለው እናም ወላጆችን፣ መሪዎችን፣ ሚስዮናውያንን፣ መምህራንን፣ ተማሪዎችን እና ሌሎች የህይወት ማዕበሎችን የሚጋፈጡ ሰዎችን ሁሉ ሊባርክ ይችላል።

መንፈሳዊ እርጋታ ሰከን እንድንል እና በተለይም ጫና በሚፈጠርብን ጊዜ በጣም አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች ላይ እንድናተኩር ይባርከናል። ፕሬዘደንት ህዩ ቢ. ብራውን፣ “በእግዚአብሔር ላይ ያለ እምነት እና በመጨረሻም የጽድቅ ድል፣ በችግር ጊዜ ለአእምሮ እና ለመንፈሳዊ እርጋታ አስተዋፅኦ ያደርጋል” በማለት አስተምረዋል። 1

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የመንፈሳዊ እርጋታ ድንቅ ምሳሌ ናቸው። አንድ ጊዜ፣ ዶክተር ኔልሰን በልብ የደም ስሮች ቀዶ ህክምና ላይ እያለ የታካሚው የደም ግፊት በድንገት ቀነሰ። ዶክተር ኔልሰን በእርጋታ ሁኔታውን ገመገመ እናም መቆንጠጫው በአጋጣሚ ከቡድኑ አባላት በአንዱ እንደተወገደ አወቀ። ወዲያውኑ ተተካ እና ዶክተር ኔልሰን የቡድኑን አባል፣ “አሁንም እወድሃለሁ” በማለት አፅናኑት እናም በመቀጠል በቀልድ መልክ “አንዳንድ ጊዜ ከሌላ ጊዜ በላይ እወድሃለሁ!” ድንገተኛ ሁኔታ እንዴት መያዝ እንዳለበት አሳየ- በእርጋታ ድንገተኛ ሁኔታን ለመፍታት በጣም አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ በማተኮር። ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳሉት፦ “ይህ በጣም ራስን የመግዛት ጉዳይ ነው። ተፈጥሯዊ ምላሻቹ፣ ‘አሰልጣኝ አስወጣኝ! የሚል ነው። ወደ ቤት መሄድ እፈልጋለሁ’። ነገር ግን በእርግጥ አትችልም። አንድ ሕይወት ሙሉ በሙሉ በቀዶ ሕክምና ቡድኑ ላይ ጥገኛ ነው። ስለዚህ ልክ እንደነበርከው የተረጋጋህ፣ ዘና ያልክ እና የነቃህ መሆን አለብህ።”2

እርግጥ ነው፣ አዳኙ የመረጋጋት የመጨረሻው ምሳሌ ነው።

በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ፣ በማይታሰብ ስቃይ፣ “እንደ ደም ነጠብጣብ”3 ወዙ እየወረደ “ፈቃዴ አይሁን የአንተ እንጂ”4 በሚለው ቀላል እና ግርማ ባለው መለኮታዊ እርጋታ ምሳሌ ሰጠ። ኢየሱስ የሰው ልጆችን ሁሉ ማዳን እንዲያስችለው በተደረገው ከፍተኛ ጫና ሥር ታላቅ እርጋታውን እንድንገነዘብ የሚረዱን ሦስት አስፈላጊ ሁኔታዎችን አሳይቷል። በመጀመሪያ፣ ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበር እናም ለመለኮታዊ ተልዕኮው እውነተኛ ነበር። በመቀጠልም ታላቅ የደስታ እቅድ እንዳለ ያውቅ ነበር። እናም በሽማግሌ ዴል ጂ. ረንለንድ በወብታማ እንዳስተማሩት፣ በመጨረሻም፣ ወሰን በሌለው የኃጢያት ክፍያው፣ በክህነት ስነስርዓቶች የተቀበሉትን ቅዱሳን ቃል ኪዳኖች በመፈጸም እና በመጠበቅ ራሳቸውን ከእርሱ ጋር በታማኝነት የሚያጣብቁ ሁሉ ይድናሉ።

እርጋታን በማጣት እና በመጠበቅ መካከል ያለውን ልዩነት ለማነፃፀር፣ ክርስቶስ እና ሐዋርያቱ ከጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲወጡ የሆነውን አስቡ። ወታደሮች ኢየሱስን ለመያዝ በመጡ ጊዜ፣ ጴጥሮስ በዚያ ድርጊት የነበረው ምላሽ መረጋጋትን በማጣት በሃይል ተቆጥቶ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ፣ የማልኮስን ጆሮ መቁረጥ ነበር። በሌላ በኩል የኢየሱስ ክርስቶስ ምላሽ መረጋጋት እና ማልኮስን በመፈወስ በአስጨናቂ ሁኔታ መሃል እርጋታ እንዲሰፍን ማድረግ ነበር።5

እርጋታን ለማግኘት ለምንቸገር እና ምናልባትም ተስፋ ቆርጠን ላለነው የቀረውን የጴጥሮስን ታሪክ እናስብ። ከዚህ ክስተት ከጥቂት ጊዜ በኋላ እና ልብ የሚሰብር ከክርስቶስ ጋር በነበረው ግንኙነት ክህደት6፣ ጴጥሮስ አዳኙን በኮነኑት በእኚው ተመሳሳይ የሃይማኖት መሪዎች ፊት ቆመ። በታላቅ ጥያቄ መሃል በመረጋጋት የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ።7

ማን እንደሆናችሁ እወቁ እና ለመለኮታዊ ማንነታችሁ እውነተኛ ሁኑ

ክርስቶስን መሰል እርጋታን ባህርያት እንመልከት። ለመጀመር ያህል፣ ማን እንደሆንን ማወቅ እና ለመለኮታዊ ማንነታችን ታማኝ መሆን መረጋጋትን ያመጣል። የክርስቶስ ዓይነት እርጋታ ራሳችንን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ወይም ያልሆንነውን አይነት ሰው ከመሆን መቆጠብን ይጠይቃል።8 ጆሴፍ ስሚዝ ፣ “ሰዎች የእግዚአብሔርን ባህርይ ካልተረዱ እራሳቸውን አይረዱም” ሲል አስተምሯል። 9 እኛ የአፍቃሪው የሰማይ አባት መለኮታዊ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች መሆናችንን ሳናውቅ መለኮታዊ እርጋታን ማግኘት የሚቻል አይደለም።

ፕሬዘደንት ኔልሰን “የዘላለም ምርጫዎች” በሚለው ንግግራቸው ውስጥ ስለ ማንነታችን እነዚህን ዘላለማዊ እውነቶች አስተምረዋል፡ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ እኛ የቃል ኪዳን ልጆች ነን፣ እናም እኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን። በመቀጠልም፣ “እነዚህን እውነቶች ስትቀበሉ፣ የሰማይ አባታችን ቅዱስ በሆነው ስፍራው ውስጥ ለዘላለም የመኖር የመጨረሻ ግባችሁ ላይ እንድትደርሱ ይረዳችኋል።10 እኛ በእውነት ሟች የሆነ ልምድ ያለን መለኮታዊ መንፈሳውያን ነን። ማን እንደሆንን ማወቅ እና ለዛ መለኮታዊ ማንነት ታማኝ መሆን የክርስቶስን መሳይ እርጋታ እድገት መሰረት ናቸው።

መለኮታዊ እቅድ እንዳለ እወቁ

በመቀጠል፣ ታላቅ እቅድ እንዳለ ማስታወስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ድፍረትን እና እርጋታን ይሰጠናል። ኔፊ ጌታ እንዳዘዘው “[መሄድ እና ማድረግ]”11 የቻለው የሚያደርገውን ነገር አስቀድሞ ሳያውቅ12 ነበር፣ ምክንያቱም እሱ የአፍቃሪውን የሰማይ አባትን ዘለአለማዊ እቅድ ለመፈጸም በመንፈስ እንደሚመራ ስላወቀ ነው። ነገሮችን ከዘላለማዊ እይታ ስንመለከት መረጋጋት ይመጣል። ጌታ ደቀ መዛሙርቱን “ዓይኖቻችሁን አንሡ” 13 እና “የዘለአለም ማስተዋልም በአዕምሮዎቻችሁ ላይ ይረፍ” 14 በማለት መክሯቸዋል። ፈታኝ ጊዜዎችን በዘላለማዊ እቅድ ውስጥ በማድረግ፣ ጫና የመውደድ፣ የማገልገል፣ የማስተማር እና የመባረክ እድል ይሆናል። ዘላለማዊ እይታ የክርስቶስን አይነት እርጋታ ያስችላል።

ችሎታ የሚሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስን እና የኃጢያት ክፍያውን ሃይል እወቁ።

እና በመጨረሻም፣ በኃጢያት ክፍያ መሥዋዕቱ የተቻለው የክርስቶስ የማስቻል ኃይል፣ እንድንጸና እና እንድናሸንፍ ብርታት ይሰጠናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን መግባት እንችላለን እንዲሁም ያንን ቃል ኪዳን በመጠበቅ እንበረታታለን። ጊዜያዊ ሁኔታችን ምንም ይሁን ምን በደስታ እና በተረጋጋ መንፈስ ከአዳኙ ጋር ልንተሳሰር እንችላለን።15 አልማ ምዕራፍ 7ስለ ክርስቶስ የማስቻል ኃይል በሚያምር ሁኔታ ያስተምራል። አዳኙ እኛን ከኃጢያት ከመዋጀቱ በተጨማሪ በዚህ ህይወት ውስጥ በድካማችን፣ በፍርሀታችን እና በፈተናዎቻችን ሊያጠነክረን ይችላል።

በክርስቶስ ላይ ስናተኩር፣ የአልማ ሰዎች በሄላም እንዳደረጉት ፍርሃታችንን ዝም ማሰኘት እንችላለን።16 አስፈሪ ሠራዊት በተሰበሰበበት ወቅት እነዚያ ታማኝ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መረጋጋትን አሳይተዋል። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናር እንዲ አስተምረዋል፦ “አልማ አማኞች ጌታን እና እሱ ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን መዳን እንዲያስታውሱ መክሯቸዋል። እናም የአዳኙን የጥበቃ እንክብካቤ ማወቃቸው ሰዎቹ የራሳቸውን ፍርሀት እንዲያቆሙ አስችሏቸዋል።17 ይህ የመረጋጋት ምሳሌ ነው።

ታላቁ ሰው በዐውሎ ነፋስ ውስጥ

ኖህ ስለ ማዕበል ውስጥ ትዕግስት ብዙ አስተምሮናል፣ ነገር ግን አዳኙ ከአውሎ ነፋስ እንዴት መትረፍ እንደሚቻል ያስተማረ ታላቅ አስተማሪ ነበር። እርሱ በማዕበል ውስጥ ያለ ታላቅ ሰው ነው። ከሐዋርያቱ ጋር ከየረዥም ቀን አስተምሮትት በኋላ፣ አዳኙ የተወሰነ እረፍት ፈለገ እና በጀልባ ወደ ገሊላ ባህር ማዶ እንዲሻገሩ ሀሳብ አቀረበ። አዳኙ ሲያርፍ፣ ከባድ ማዕበል ተነሳ። ንፋሱና ማዕበሉ ጀልባውን ሊያሰምጥ ሲል ሐዋርያቶቹ ለሕይወታቸው መፍራት ጀመሩ። እናም ደግሞ አስታውሱ፣ ከእነዚያ ሐዋርያት መካከል ብዙዎቹ በዚያ ባህር ላይ ስላለው ማዕበል ጠንቅቀው የሚያውቁ አሳ አጥማጆች ነበሩ! ሆኖም፣ ተጨንቀው18 ጌታን ከእንቅልፉ ቀስቅሰው “[ጌታ ሆይ]፣ ስንጠፋ አይገድህምን?” ብለው ጠየቁት። ከዚያም አርአያነት ባለው እርጋታ “ኢየሱስ ተነሳ እና ንፋሱን አዘዘው እናም የሚናጋውን ባህር እንዲህ አለው፣ “ዝም በል፥ ፀጥ በል። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።”19

ከዚያም ለሐዋርያቱ ታላቅ የእርጋታ ትምህርት። “እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም” 20 በማለት ጠየቃቸው። እርሱ የዓለም አዳኝ መሆኑን እና የእግዚአብሔርን ልጆች ዘላለማዊነትን እና ዘላለማዊ ህይወትን ለማምጣት ከአብ እንደተላከ እያስታወሳቸው ነበር። በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ በጀልባ ላይ አይጠፋም። አምላክነቱን ስለሚያውቅ እና የመዳን እና የከፍታ እቅድ እንዳለ እናም የኃጢያት ክፍያው ለዛ እቅድ ዘላለማዊ ስኬት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ስለሚያውቅ መለኮታዊ እርጋታን አሳይቷል።

ሁሉም መልካም ነገሮች ወደ ህይወታችን የሚመጡት በክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ነው። ማን እንደሆንን ስናስታውስ፣ መለኮታዊ የምሕረት ዕቅድ እንዳለ በማወቅ፣ እና በጌታ ብርታት ድፍረትን በመሳብ፣ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን። እርጋታን እናገኛለን። በማንኛውም ማዕበል ውስጥ መልካም ሴቶች እና ወንዶች እንሆናለን።

በአስቸጋሪ ጊዜያት እራሳችንን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ለመባረክ እና በሕይወታቸው ውስጥ ባሉ ማዕበሎች ውስጥ ለመርዳት የክርስቶስን መሰለ የእርጋታ በረከቶችን እንፈልግ። በዚህ የሆሳዕና በአል ዋዜማ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ። እርሱ ተነስቷል። እርሱ ብቻ ወደ ሕይወታችን ስለሚያመጣው ሰላም፣ መረጋጋት እና ሰማያዊ እርካታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለሁ፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሒው ቢ. ብራውን፣ በጉባኤ ሀተታ፣ ጥቅምት 1969 (እ.አ.አ)፣ 105።

  2. ሼሪ ዱው፣ Insights from a Prophet’s Life: Russell M. Nelson [2019 (እ.አ.አ)]፣ 66–67።

  3. የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ሉቃስ 22፡44 (በሉቃስ 22፥44, የግርጌ ማስታወሻ 

  4. ሉቃስ 22፥42

  5. ሉቃስ 22፥50–51ዮሐንስ 18፥10–11 ይመልከቱ።

  6. ማቴዎስ 26፥34–35፣ 69–75 ይመልከቱ።

  7. የሐዋርያት ሥራ 4፥8-10፤ ኔል ኤ. ማክስዌል፣ “በተሰጡን ነገሮች መርካት፣” ኤንዛይን፣ ግንቦት 2000 (እ.አ.አ)፣ 74፤ ሊያሆና፣ ሐምሌ 2000 (እ.አ.አ)፣ 89፦ “በመንፈሳዊ ሁኔታ ስንጣመር፣ ‘የሁሉንም ነገር ትርጉም’ ባናውቅም እርጋታ ሊመጣ ይችላል (1 ኔፊ 11፥17)።”

  8. ጆን አር. ውድን Wooden on Leadership፣ (2005 (እ.አ.አ)] ይመልከቱ፦ “መረጋጋትን ለራስ እውነት መሆንን፣ ሁኔታው ምንም ይሁን ምን አለመናደድ፣ አለመበሳጨት ወይም ሚዛናዊ መሆን ብዬ እገልጻለሁ። ይህ ቀላል ሊመስል ይችላል፣ ግን እርጋታ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ የማይቻል ባህሪ ሊሆን ይችላል። እርጋታ የሌላቸው መሪዎች ጫና ውስጥ ይደናገጣሉ።

    “ሁኔታው ምንም ያህል መጥፎ ወይም ጥሩ ቢሆን፣ እምነትን አጥብቆ መያዝ እና በዚያ መሰረት እርምጃ መውሰድ ማለት ነው። እርጋታ ማለት ማስመሰልን፣ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደርን እና እናንተ እንዳልሆናችሁት አይነት ሰው መሆንን ማስወገድ ማለት ነው። እርጋታ ማለት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ደፋር ልብን መያዝ ማለት ነው።”

  9. Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 40.

  10. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Choices for Eternity” (worldwide devotional for young adults, May 15, 2022), broadcasts.ChurchofJesusChrist.org.

  11. 1 ኔፊ 3፥7

  12. 1 ኔፊ 4፥6

  13. ዮሀንስ 4፥35

  14. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 43፥34፤ በተጨማሪም ጄምስ ኢ. ፋስትን፣ “የራስ ክብርኢንዛይን ግንቦት 1981 (እ.አ.አ)፣ 10 ይመልከቱ፦ “የራስ ክብር ከፍ ያለ የሚሆነው ቅድስናን ፍለጋ ወደ ላይ በማየት ነው። ልክ እንደ ግዙፉ ዛፎች ወደ ብርሃን መድረስ አለብን። ልናውቀው የምንችለው በጣም አስፈላጊው የብርሃን ምንጭ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። እሱ የውስጣዊ ጥንካሬ እና የሰላም ምንጭ ነው።”

  15. ረስል ኤም ኔልሰን፣ “ደስታ እና በመንፈሳዊነት መትረፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ) ይመልከቱ፦ “ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የሚሰማን ደስታ ካሉን የህይወታችን ሁኔታዎች ጋር የተያያዙበት የቀነሰ ነው እናም የህይወታችን ትኩረት ጋር ያላቸው ዘመዴታ ታላቅ ነው።”

  16. ሞዛያ 23፥27–28ን ይመልከቱ።

  17. David A. Bednar, “Therefore They Hushed Their Fears,” Liahona, May 2015, 46–47.

  18. See Jeffrey R. Holland, Our Day Star Rising: Exploring the New Testament with Jeffrey R. Holland (2022), 61–62፦ “ከዚህም በተጨማሪ፣ እነዚህ ከእርሱ ጋር አብረውት የተጓዙ ልምድ ያላቸው ሰዎች ነበሩ—ከመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለቱ አስራ አንዱ የገሊላ ሰዎች ነበሩ (የአስቆሮቱ ይሁዳ ብቻ ነበር አይሁዳዊ)። ከአሥራ አንዱም ስድስቱ ዓሣ አጥማጆች ነበሩ። በዚህ ሐይቅ ላይ ኖረዋል። ከዛ ውስጥ ዓሣ በማጥመድ ነበር የሚተዳደሩት። ከልጅነታቸው ጀምሮ እዚያ ነበሩ። አባቶቻቸው ገና በልጅነታቸው በጀልባው ላይ መረባቸውን እንዲጠግኑ ያደርጉ ነበር። ይህን ባሕር ያውቃሉ፣ ነፋሱንና ማዕበሉን ያውቃሉ። ልምድ ያላቸው ወንዶች ናቸው -ነገር ግን በጣም ፈርተዋል። እና እነሱ ከፈሩ ይህ እውነተኛ ማዕበል ነው።

  19. ማርቆስ 4፥35–39 ይመልከቱ።

  20. ማርቆስ 4፥40

አትም