አጠቃላይ ጉባኤ
ኢየሱስ ክርስቶስ እፎይታ ነው
የሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:19

ኢየሱስ ክርስቶስ እፎይታ ነው

ለተቸገሩ ስጋዊ እና መንፈሳዊ እፎይታን ለመስጠት ከአዳኙ ጋር መተባበር —እናም በሂደቱ የራሳችንን እፎይታ ማግኘት እንችላለን።

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና ስላደረጋቸው ተዓምራት በሰሙት ነገር ተስፋ በማድረግ፣ የሽባው ሰው ተንከባካቢዎች ወደ ኢየሱስ ይዘውት መጡ። እሱን እዚያ ለመውሰድ አዲስ ፈጠራን ተጠቅመው ነበር— ጣራውን ከፍተው ሰውየውን በአልጋው ላይ በማድረግ ኢየሱስ እያስተማረ በነበረት ቦታ ቁልቁል አወረዱት። ኢየሱስም “እምነታቸውን አይቶ [ሽባውን ሰው] …ኃጢያትህ ተሰረየችልህ አለው።”1 ከዚያም “ ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ወደቤትህ ሂድ አለው።”2 እና ወዲያውም ሽባው ሰው ተነሳና አልጋውን ተሸክሞ “እግዚአብሔርን እያመሰገነ“ ወደ ቤቱ ሄደ።3

እንክብካቤ ስላደረጉለት ስለሽባው ሰው ጓደኞች ምን ተጨማሪ ነገር እናውቃለን? አዳኙ ለእምነታቸው እውቅና እንደሰጠ እናውቃለን። አዳኙን ስላዩ እና ስለሰሙ እንዲሁም የተዓምራቱ ምስክር የነበሩ በመሆናቸው ”መገረም ያዛቸው” እንዲሁም ”እግዚአብሔርን አከበሩ።”4

ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋ የተደረገበትን ፈውስ—ይኸውም ከህመም እና የጸና በሽታ ከሚያስከትለው የሽባነት ውጤቶች አካላዊ እፎይታ ሰጥቶ ነበር። በተጨማሪም፣ አዳኙ ሰውየውን በአስደናቂ ሁኔታ ከኃጢአት በማንጻት መንፈሳዊ እፎይታ ሰጥቷል።

ጓደኞቹ ደግሞ—የተቸገረን ሰው ለመንከባከብ ባደረጉት ጥረት፣ የእፎይታ ምንጭ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አግኝተዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እፎይታ እንደሆነ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት፣ ከኃጢያት ሸክም እና ውጤቶች እፎይታ እናገኛለን እንዲሁም ስንደክም እርዳታ እናገኛለን።

ደግሞም እግዚአብሔርን ስለምንወድ እና እሱን ለማገልገል ቃል ኪዳን የገባን ስለሆነ ለተቸገሩ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት የአዳኙ አጋር መሆን እንችላለን—እንዲሁም በሂደቱ በኢየሱስ ክርስቶስ በአማካኝነት የራሳችንን እፎይታ እናገኛለን።5

ውድ ነቢያችን ራስል ኤም. ኔልሰን፣ ዓለምን እንድናሸንፍ እና እረፍት እንድናገኝ ጋብዘውናል።6 “እውነተኛ ዕረፍት“ “እፎይታና ሰላም“ እንደሆነ ገልጸዋል። ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “በአዳኙ አማካኝነት፣ መጨረሻ በሌለው የኃጥያት ክፍያ በኩል እያንዳንዳችንን ከደካማነት፣ ከስህተቶች እና ከኃጥያት ስላዳነንና እናንተ የነበሩባችሁን ህመሞች፣ ሀሳቦች፣ እና ሽክሞች ስለተለማመዳቸው፣ እናንተ በእውነት ንስሀ ስትገቡና እርዳታውን ስትሹ ከዚህች አስጨናቂ አለም ከፍ ለማለት ትችላላችሁ።”7 ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጠን እፎይታ ያ ነው!

እያንዳንዳችን ምሳሌያዊ የጀርባ ቦርሳ ተሸክመናል። ሚዛኑ ተጠብቆ ጭንቅላታችሁ ላይ የተደረገ ቅርጫት ወይም ከረጢት ወይም በጨርቅ ተጠቅልሎ ትከሻችሁ ላይ የተንጠለጠለ ነገር ሊሆን ይችላል። ሆኖም ለኛ አስተሳሰብ፣ የጀርባ ቦርሳ ብለን እንጥራው።

ይህ ምሳሌያዊ የጀርባ ቦርሳ በወደቀው ዓለም ውስጥ ስንኖር ያሉትን ሸክሞች የምንሸከምበት ነው። ሸክሞቻችን በጀርባ ቦርሳው ውስጥ እንዳሉ ድንጋዮች ናቸው። በአጠቃላይ፣ ሶስት ዓይነት አሉ፤

  • ራሳችን በሰራነው ኃጢአት ምክንያት ወደቦርሳችን የገቡ ድንጋዮች።

  • በደካማ ውሳኔዎቻችን፣ በስነምግባር ጉድለታችን እና በሌሎች ደግነት በጎደላቸው ሰዎች ምክንያት በቦርሳችን ውስጥ የገቡ ድንጋዮች።

  • ይህ ምሳሌያዊ ቦርሳ በወደቀው ዓለም ውስጥ ስንኖር ያሉትን ሸክሞች የምንሸከምበት ነው። እነዚህም የበሽታ፣ የህመም፣ የጽኑ ሕመም፣ የሀዘን፣ ተስፋ የመቁረጥ፣ የብቸኝነት እና የተፈጥሮ አደጋዎች ውጤቶች ድንጋዮችን ያካትታሉ።

ሥጋዊ ሸክሞቻችን ይኸውም በምሳሌያዊው ቦርሳችን ውስጥ ያሉት እነዚህ ድንጋዮች ከባድ ሆነው ሊሰሙን እንደማይገባ በደስታ እናገራለሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሸክማችንን ሊያቀልልን ይችላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሸክማችንን ከላያችን ላይ ሊያነሳ ይችላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአት ሸክም እፎይታ የምናገኝበትን መንገድ አዘጋጅቶልናል።

ኢየሱስ ክርስቶስ እፎይታችን ነው።

እንዲህ ብሏል፦

“እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ[ያ እፎይታ እና ሰላም ነው]።

“ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።

“ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”8

ቀንበሩ ልዝብ እንዲሁም ሸክሙ ቀሊል መሆኑ ከአዳኝ ጋር በቀንበር እንደምንጣመር፣ ሸክማችንን ከእርሱ ጋር እንደምንጋራ፣ ሸክማችንን እንዲያነሳልን እንደምንፈቅድለት ግምት ውስጥ ያስገባል። ያ ማለት ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳብራሩት ከእግዚአብሔር ጋር “ስለሕይወት ሁሉንም ነገር የሚያቀልል” የቃል ኪዳን ግንኙነት ውስጥ መግባት እና ቃል ኪዳኑን መጠበቅ ማለት ነው። እንዲህ ብሏል፣ “ነገር ግን ራስችሁን ከአዳኝ ጋር ማጣመር ማለት የእሱ ጥንካሬ እና የማዳን ሃይል አላችሁ ማለት ነው።”9

ታዲያ ድንጋዮቻችንን የምንሰስተው ለምንድን ነው? ጨዋታውን ለመጨረስ ዝግጁ የሆነ ተቀያሪ እያለ የደከመው የቤዝቦል ወርዋሪ ጉብታውን ለቆ ለመውጣት ፈቃደኛ የማይሆነው ለምንድን ነው? እፎይታ ሰጪው ከእኔ ጋር ለመጠበቅ ዝግጁ ሆኖ እያለ ቦታዬን ብቻዬን ልጠብቅ የምለው ለምንድን ነው?

ፕሬዘደንት ኔልሰን እንዳሰተማሩት “ኢየሱስ ክርስቶስ … ሊያድነን፣ ይቅር ሊለን፣ ሊያነጻን እና ሊቀድሰን እየፈለገ እና ተስፋ እያደረገ እጆቹን ከፍቶ [ቆሟል]።”10

ታዲያ ድንጋዮቻችንን እንሸከም የምንለው ለምንድን ነው?

እያንዳንዳችሁ እንደግል ጥያቄ ግምት ውስጥ እንድታስገቡት የታሰበ ነው።

እንደኔ እንደኔ ለዘመናት የቆየ የኩራት ክፉ ባህሪ ነው። “እራሴ ማድረግ እችላለሁ” እላለሁ። “ችግር የለም፤ አደርገዋለሁ።” ከእግዚአብሔር እንድደበቅ፣ ከእርሱ እንድርቅ፣ ብቻዬን እንዳደርገው የሚፈልገው ታላቁ አታላይ ነው።

ወንድሞች እና እህቶች፣ እኔ ብቻዬን ላደርገው አልችልም እንዲሁም አይገባኝም እናም አላደርገውም። ከእግዚአብሔር ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን አማካኝነት ከአዳኜ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መጣመርን በመምረጥ “ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።”11

ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ በአዳኙ እፎይታ ይባረካሉ።

የአልማ ህዝቦች “ሃላፊነቱን በእነርሱ ላይ [በማድረግ]፣ አስገባሪዎችንም በእነርሱ ላይ [በማድረግ]“ ሥደት ደርሶባቸው ነበር የሚለውን ምሳሌ ልብ በሉ።12 ድምጽ አውጥተው መጸለይ በመከልከላቸው ”ልባቸውን ወደ [እግዚአብሄር] አፈሰሱ፤ እናም እርሱ የልባቸውን ሐሳብ ያውቅ ነበር።”13

እናም “የጌታ ድምፅ በስቃያቸው እንዲህ በማለት መጣ፥ ራሳችሁን አቅኑም መልካም መፅናኛ ይኑራችሁም፤ ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አውቀዋለሁና፤ ከህዝቤም ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ እናም ከባርነት አስለቅቃቸዋለሁ።

“እናም …በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፣ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቀልላችኋለሁ”።14

እናም ሸክሞቻቸው “ቀለውላቸው ነበር“፣ እንዲሁም “ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ እናም በደስታና በትዕግስት ለጌታ ፈቃድ ተቀባይ እንዲሆኑ ጌታ ብርታትን ሰጥቷቸዋል”15

ቃል ኪዳን የሚጠብቁ በመጽናኛ፣ በላቀ ትዕግስት እና በደስታ ፣ በጀርባቸው እንኳን ሊሰማቸው እንዳይቻላቸው በትከሻቸው ያለውን በማቅለል እንዲሁም በመጨረሻ ከባርነት በመላቀቅ መልክ እፎይታን አግኝተዋል።16

አሁን ወደራሳችን ምሳሌያዊ የጀርባ ቦርሳ እንመለስ።

ከኃጢአት ድንጋዮች ሸክም የሚያገላግለን በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ንስሀ መግባት ነው። እንዲሁም በዚህ ቆንጆ ስጦታ አማካኝነት፣ የእግዚአብሔር ምሕረት ከከባድ እና ያለ እርሱ ለመቋቋም ከማይቻሉት የፍትህ ጥያቄዎች እፎይታ ይሰጠናል።17

በተጨማሪም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ይቅርታ ለማድረግ የሚያስችለንን ጥንካሬ ይሰጠናል፣ ይህም በሌሎች በደል የተነሳ የተሸከምነውን ሸክም ከላያችን እንድናወርድ ያስችለናል።18

ታድያ አዳኙ ለሀዘን እና ለህመም በተጋለጡ ሟች አካላት በወደቀው አለም ውስጥ በመኖር ከሚመጣ ሸክም እፎይታ የሚሰጠን እንዴት ነው?

አብዛኛውን ጊዜ፣ እርሱ እንደዚያ ዓይነቱን እፎይታ የሚሠጠው በእኛ በኩል ነው! እንደ ቤተክርስቲያኑ የቃልኪዳን አባል “ከሚያለቅሱ ጋር ለማልቀስ እናም መጽናናት የሚያስፈልጋቸውን ለማጽናናት” ቃል ኪዳን ገብተናል።19 “ወደ እግዚአብሔር በአንድ አላማ ስለመጣን እና “ህዝቡ [እንባል] ዘንድ“ “አንዳችን የአንዳችንን ሸከም ለመሸከም ፍቃደኞች ነን”20

የቃል ኪዳን በረከታችን ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ሥጋዊ እና መንፈሳዊ እርዳታን ለመስጠት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አጋር መሆን ነው። እርሱ እፎይታን የሚሠጠው እኛን በመጠቀም ነው።21

ስለዚህ እንደሽባው ሰው ጓደኞች “ደካሞ[ችን ] [እንረዳለን]፣ የወረዱ እጆችን ወደ ላይ [እናነሳለን] እና የደከሙ ጉልነቶች[ን] [እናጠነክራለን]”22። “እያንዳን[ዳችን] የአንዱን ሸክም [እንሸከማለን] እንዲሁም የክርስቶስን ህግ [እንፈጽማለን]።”23 ይህንን ስናደርግ፣ እርሱን እያወቅን እንመጣለን፣ እንደ እርሱ እንሆናለን እንዲሁም የእርሱን እፎይታ እናገኛለን።24

እፎይታ ምንድን ነው?

የሚያሳምምን፣ የሚያስቸግርን ወይም ሸክም የሆነን ነገር ማስወገድ ወይም ማቃለል ወይም እሱን ለመቋቋም የሚያስችል ጥንካሬ ነው። የሌላን ሰው ቦታ የወሰደን ሰው ያመለክታል። የሥህተት ህጋዊ እርማት ነው።25 የአንግሎ-ፈረንሳዩ ቃል የመጣው ሬሌቨርወይም “ወደላይ መነሳት“ ከሚለው የጥንት ፈረንሳይኛ ወይንም ከላቲኑ ሬለቬርወይም “እንደገና መነሳት“ ከሚለው ቃል ነው።26

ወንድሞች እና እህቶች፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እፎይታ ነው። በርግጥ በሦስተኛው ቀን እንደተነሳና የፍቅር እና ወሰን የሌለውን የኃጢያት ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ለመነሳት፣ ለመዳን እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ ለማለት እንዲሁም እርሱን እንመስል ዘንድ እድል ለመስጠት እጆቹን ከፍቶ እንደቆመ እመሰክራለሁ። እርሱ የሚሰጠን እፎይታ ዘላለማዊ ነው።

በዚያ በመጀመሪያው የትንሳኤ ማለዳ በመልአኩ እንደተጎበኙት ሴቶች “ፈጥኜ መሄድ” እና “በታላቅ ደስታ” እርሱ ተነስቷል የሚለውን ቃል ለመናገር እመኛለሁ።27 በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሉቃስ 5፥20

  2. ማርቆስ 2፥11

  3. ሉቃስ 5፥25

  4. ሉቃስ 5፥26

  5. ዲ ቶድ ክርስቶፈርሰንThe First Commandment First(ብሪገም ያንግ ዩኒቨርሲቲ ዲቮሽናል የካቲት 22፣2022) (እ.አ.አ)፣ 2 speeches.byu.edu መልከቱ፦ “ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ሌሎችን በተሟላ ሁኔታ እና ፍጹም በሆነ መልኩ የመውደድ ችሎታችንን ከፍ ያደርገዋል። በመሠረቱ ከእግዚአብሔር ጋር በልጆቹ እንክብካቤ ውስጥ አጋር እንሆናለን” (አጽንዖት ተጨምሯል)።

  6. የራስል ኤም.ኔልሰንን፣ “አለምን ማሸነፍ እና እረፍትን ማግኘት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 95–98 ይመልከቱ።

  7. ራስል ኤም.ኔልሰን፣ “አለምን ማሸነፍ እና እረፍትን ማግኘት” 96።

  8. ማቴዎስ 11፥28–30

  9. ራስል ኤም.ኔልሰን፣ “Overcome the World and Find Rest፣ ” 97 ይመልከቱ።

  10. ራስል ኤም ኔልሰን፣ “የተሻለ ማድረግ እንችላለን እንዲሁም የተሻልን መሆን እንችላለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67።

  11. ፊልጵስዩስ 4፥13

  12. ሞዛያ 24፥9

  13. ሞዛያ 24፥12

  14. ሞዛያ 24፥13–14፤ ትኩረት ተጨምሯል።

  15. ሞዛያ 24፥15

  16. ሞዛያ 24፥13-14ይመልከቱ፡፡

  17. አልማ 34፥14–16፤ እንዲሁም ሞዛያ 15፥8–9 ይመልከቱ፡፡

  18. ራስል ኤም ኔልሰን “Four Gifts That Jesus Christ Offers to You” [የመጀመርያ አመራር የገና አምልኮ፣ ታህሳስ፣ 2 ፣ 2019 (እ.አ.አ)]፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org፣ “ሁለተኛው ስጦታ አዳኙ የሚሰጣችሁ ይቅርታየማድረግ ችሎታ ነው። “በእሱ ማለቂያ በሌለው የኃጢያት ክፍያ በኩል፣ እናንተን የጎዱትን እና በእናንተ ላይ ላደረጉት ጭካኔ ሃላፊነትን በጭራሽ የማይቀበሉትን ይቅር ማለት ትችላላችሁ።

    “ብዙውን ጊዜ ይቅርታችሁን ከልብ እና በትህትና ለሚፈልግ ይቅር ማለት ቀላል ነው። ነገር ግን አዳኙ በማንኛውም መንገድ የበደላችሁን ማንኛውንም ሰው ይቅር ለማለት ችሎታ ይሰጣችኋል። ከዚያም የሚጎዳ ተግባራቸው ነፍሳችሁን ሊያሳምም አይችልም።”

  19. ሞዛያ 18፥9

  20. ሞዛያ 18፥8

  21. የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሴቶች ድርጅት የሆነው በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተደራጀው የሴቶች መረዳጃ ማህበር በማርች 17፣ 1842 “እንደክህነት ቅጥያ በመለኮታዊ የተቋቋመ” ነበር (ዳሊን ኤች. ኦክስ፣ “The Keys and Authority of the Priesthoodሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)፣ 51)። ለአዲሱ ድርጅት ስም ሲመረጥ፣ በጎ አድራጊ የሚለው ቃል ግምት ውስጥ ገብቶ ነበር፣ ነገር ግን መረዳጃ የሚለው በሴቶች ዘንድ ተመራጭ ሆነ። የድርጅቱ የመጀመሪያ ፕሬዘደንት የነበረችው ኤማ ስሚዝ እና የድርጅቱ ፀሐፊ በኋላም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሁለተኛ ፕሬዘደንት በመሆን ያገለገለችው ኤሊዛ አር. ስኖው፣ በጎ አድራጊ የሚለው ቃል በዘመኑ በነበሩት ተቋማት ዘንድ ታዋቂ ቃል እንደነበር አብራርተዋል—ነገር ግን ያ ታዋቂ የሆነው “መመሪያችን መሆን የለበትም።“ ኤማ መረዳጃ የሚለው ቃል ተልእኳቸውን በተሻለ ሁኔታ እንደሚገልጽ አብራርታለች። “አንድ ልዩ የሆነ ነገር እናደርጋለን … ልዩ የሆኑ ወቅቶች እና አስቸኳይ ጥሪዎችን እንጠብቃለን።” (ኤማ ስሚዝ፣ በናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ቃለ ጉባኤ ውስጥ የሰፈረ፣ መጋቢት 17፣ 1842 (እ.አ.አ)፣ 12)። በእርግጥ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሥልጣን ሥጋዊ እና መንፈሳዊ እርዳታን መስጠት ነው። ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲል አስተምሯል፣ “ማህበሩ ድሆችን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን ነፍሳትን ለማዳንም ነው” (በናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ቃለ ጉባኤ ውስጥ የሰፈረ፣ ሰኔ 9፣ 1842 (እ.አ.አ)፣ 63፣ josephsmithpapers.org)። ስለዚህ የመረዳጃ ማህበሩ እርዳታ መስጠቱን ይቀጥላል፦ “የድህነት እርዳታ፣ የበሽታ እርዳታ፤ የጥርጣሬ እርዳታ፣ የድንቁርና እርዳታ—የሴቶችን ደስታ እና እድገት የሚያግዱ ነገሮች ሁሉ እርዳታ (ጆን ኤ. ዊድሶ፣ Evidences and Reconciliations፣ arr. ጂ. ሆሜር ዱርሃም፣ 3 ቅጽ በአንድ፣ [1960]፣ 308)።

  22. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥5፤ በተጨማሪም ዕብራውያን 12፥12ይመልከቱ፤

  23. ገላትያ 6፥2

  24. በአዲስ በተደራጀው የሴቶች መረዳጃ ማህበር በተደረጉት የመጀመሪያ ስብሰባዎች በአንዱ ላይ፣ የነቢዩ እናት ሉሲ ማክ ስሚዝ እንዲህ ብላለች፥ “በሰማይ ሁላችንም አብረን እንድንቀመጥ ዘንድ፣ እርስ በራስ መፈቃቀር፣ እርስ በራስ መጠባበቅ፣ እርስ በራስ መፅናናትና ትምህርትን ማግኘት ይገባናል።” የታሪክ ጸሃፊው ጄኒፈር ሪደር ስለዚህ ጽፈዋል፣ “እርዳታን ለመስጠት በነበራቸው የተባበረ ዓላማ ሴቶቹ ከክርስቶስ ጋር አጋር ሆነዋል እንዲሁም ይህን በማድረግ የእሱን እርዳታ አግኝተዋል”(First: The Life and Faith of Emma Smith [2021(እ.አ.አ)]፣ 130)።

  25. Merriam-Webster.com Dictionary፣ “relief” ይመልከቱ።

  26. Dictionary.com፣ “relief” ይመልከቱ።

  27. ማቴዎስ 28፥1–8ይመልከቱ።