አጠቃላይ ጉባኤ
የሰላሙ ልዑል ተከታዮች
የሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:35

የሰላሙ ልዑል ተከታዮች።

እንደ አዳኙ አይነት ያሉ ባህሪያትን ለመገንባት ስንሞክር፣ በአለም ላይ የሱ የሰላም መሳሪያዎች መሆን እንችላለን።

ለዘካሪያስ በተሰጠው የትንቢት ፍጻሜ1 ኢየሱስ በድል አድራጊነት በአህያ ላይ ሆኖ ቅዱስ ወደሆነችው ከተማ ገባ ይህም በስነ ጽሑፍ የጥንት አይሁዳዊያን የንጉሳዊ አገዛዝ ምልክት ተደርጎ ይቆጠር ነበር። 2በእርግጠኝነትም ለንጉሶች ንጉስ እና ለሰላም ልኡል እንደሚገባው።3 ኢየሱስ ባለፈበት መንገድ ላይ ልብሳቸውን፣ የዘምባባ ቅጠሎችን እና ሌላ ቅጠል ባነጠፉ በብዙ ደስተኛ ደቀ መዛሙርት ተከበበ። ከፍ ባለ ድምጽ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉስ የተባረከ ይሁን፣ በገነት ሰላም እና በአርያምም ክብር” እያሉ አመለኩት።4 አሁንም በድጋሚ፣ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፦ “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም”። 5 የሆሳዕና በዓል በመባል በሚታወቀው በዚህ ቀን የምናከብረው ይህ ግሩም ሞገስ ያለው በዓል በአዳኙ ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነ መስዋት እና በመቃብሩ ባዶ የመሆን አስገራሚ ተአምር፣ የተደመደመበት በዚያ አስጨናቂ ሳምንት ውስጥ ለተከሰቱት አስጨናቂ ክስተቶች አስደሳች ቅድመ ዝግጅት ነበር።

እንደእርሱ ተከታዮች፣ እኛ የእርሱ የተመረጥን ህዝብ ነን፣ የእርሱን ጽድቅ ለማወጅ የተጠራን ፣ በእርሱ እና በእርሱ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት በልግስና የተሰጠውን ሰላም አስተዋዋቂዎች ነን።6 ይህ ስጦታ ልባቸውን ወደእርሱ ለሚመልሱ እና በጽድቅ ለሚኖሩ ሁሉ ቃል የተገባ ስጦታ ነው። ይህን የመሰለ ሰላም ምድራዊ ህይወትን በጥሩ ሁኔታ እንድናሳልፍ እና በጉዞዋችን ላይ በሚገጥሙን ከባድ ፈተናዎች እንድንጸና ይረዳናል።

በ1847(እ አ አ)፣ ወደ ምዕራብ ባደረጉት ጉዟቸው ላይ ያልተጠበቁ ችግሮችን ሲጋፈጡ ተረጋግቶ ለመቆየት እና አንድ ለመሆን ሰላም ለሚያስፈልጋቸው አቅኚ ቅዱሳን ጌታ ግልጽ የሆኑ መመሪያዎችን ሰጥቷቸዋል። ከሌሎች ነገሮች ውስጥ፣ ጌታ ቅዱሳንን “እርስ በራስም መጣላትን አቁሙ፣ እርስ በራስም ክፋት መነጋገርን አቁሙ” ሲል መመሪያ ሰጥቷቸዋል።7 ቅዱሳት መጽሃፍት የጽድቅ ስራን ለሚለማመዱ እና በጌታ የትሁት መንፈስ ውስጥ ለመራመድ ለሚጥሩ ዛሬ በምንኖርበትን የችግር ቀናት ለማለፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰላም እንደሚያገኙ ቃል እንደተገባላቸው ያረጋግጣሉ።8

የሰላም ንጉስ ደቀመዛሙርት እንደመሆናችን፣ “[ልባችን] በአንድ ላይ በአንድነትና፣ አንዱ ሌላኛውን ባለው ፍቅር [እንድንጣበቅ]” ታዘናል።9 ውድ ነብያችን ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን፣ “ክርክር አዳኙ የቆመለትን እና ያስተማራቸውን ነገሮች ሁሉ እንደሚጥስ” በቅርቡ አሳውቀው ነበር።10 እንዲሁም ነብያችን በልባችን እና በህይወታችን ውስጥ በአሁኑ ወቅት እየተነሱ ያሉትን የግል ግጭቶች ለማስወገድ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ተማጽነውናል።11

እነዚህን መርሆች ክርስቶስ ለእኛ ባለው የንጹህ ፍቅር እይታ ታሳቢ እናድርግ እንዲሁም እንደ ተከታዮቹ አንዳችን ለሌላችን ይህ እንዲኖረን እንሻ። ቅዱሳት መጻህፍት ይህን አይነቱን ፍቅር ልግስና ብለው ይጠሩታል።12 ስለልግስና ስናስብ፣ አእምሮአችን በተለምዶ አካላዊ፣ ቁሳዊ ወይም ስሜታዊ ችግሮች ለሚያጋጥማቸው፣ ከስቃያቸው ለመገላገል የምናደርገው መልካም ተግባር ወይም በነጻ ወደምንሰጠው ነገር ይሄዳል። ሆኖም፣ ልግስና ለአንድ ሰው በነጻ ከምንሰጠው ገንዘብ ወይም ቁስ ጋር ብቻ የተዛመደ አይደለም፣ ነገር ግን የአዳኙ ባህርይ ነው እንዲሁም የባህሪያችን አካል መሆን ይችላል። ጌታ “የፍጹምነት እና የሰላም ማሰሪያ የሆነውን” የልግስናን ካባ እራሳችንን እንድናለብስ መመሪያ መስጠቱ የሚያስገርም አይደለም።13 ያለልግስና ምንም አይደለንም፣14 እናም ደግሞ በሰማይ አባታችን የመኖሪያ ስፍራ ውስጥ ጌታችን ያዘጋጀልንን ቦታ ልንወርስ አንችልም።15

በተለይም ኢየሱስ ሰማዕት ከመሆኑ በፊት የመጡትን አስጨናቂ ሁኔታዎች ሲጋፈጥ፣ ይህ የፍጹምነት እና የሰላም ማሰሪያን የራስ ማድረግ ምን ማለት እንደሆነ ፍጹም በሆነ መልኩ በምሳሌ አሳይቷል። ለአፍታ ያህል፣ ኢየሱስ በዚያን ምሽት ከመካከላቸው አንዱ እንደሚክደው እያወቀ በትህትና የደቀመዝሙርቱን እግሮች ሲያጥብ ምን ተሰምቶት ሊሆን እንደሚችል አስቡ።16 ወይም፣ ከሰአታት በኋላ ኢየሱስ እሱን ለማሰር ከይሁዳ ጋር ከመጡት ሰዎች የአንዱን ሰው ጆሮ በምህረት የፈወሰውን አስቡ።17 ወይም አዳኙ በጲላጦስ ፊት ለፊት ቆሞ አላግባብ በካህናት አለቃው እና በሽማግሌዎች በተወነጀለ ጊዜ እና በእርሱ ለይ ለቀረቡት የሃሰት ክሶች ምንም መቃወሚያ ቃል አላሰማሰማቱ የሮማውን ገዢ አስደነቀው።18

በእነዚህ ሶስት አሳዛኝ ገጠመኞች ውስጥ፣ ከልክ ያለፈ ሃዘን እና ጭንቀት ቢሸከምም እንኳን “ፍቅር ይታገሳል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ … አይቀናም፣ … ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም ፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም” የሚለውን በምሳሊው አስተምሮናል።19

ሌላው ትኩረት ሲሰጠው የሚገባው ወሳኝ የሆነ ገጽታ እና ደቀመዝሙር በመሆናችን ላይ ቀጥተኛ የሆነ አንደምታ ያለው እንዲሁም አዳኙን የምናስተዋውቅበት መንገድ አንዳችን ሌሎችን የምንይዝበት መንገድ ነው። በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት፣ የአዳኙ አስተምህሮ ያተኮረው በእነዚህ ላይ ብቻ አይደለም ነገር ግን በተለይ ወደእርሱ ለመቅረብ እና ሰላሙን ለማስተዋወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች መሰረታዊ በሆኑት ባህሪያት —በፍቅር፣ በልግስና፣ በትግስት፣ እና በርህራሄ ላይ ያተኮሩ ነበር። እንዲህ አይነት ባህርያት ከእግዚሐብሄር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው እናም ልናጠናከራቸው ስንጥር ከጎረቤቶቻችን ጋር ያሉንን ልዩነቶች እና ድክመቶች በይበልጥ በርህራሄ፣ በቅን ስሜት፣ በክብር እና በመቻቻል መንገድ ማየት እንችላለን። በይበልጥ ወደ ክርስቶስ እየቀረብን እደሆነ እንዲሁም እርሱን እየመሰልን እንደሆነ ከሚያሳዩት ግልጽ ማረጋገጫዎች መካከል አንዱ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ሌሎችን የምንወድበት፣ የምንታገስበት እና የምንይዝበት የመልካምነት መንገድ ነው።

ብዙውን ጊዜ፣ በተለይ እንደዚህ አይነት ባህሪያት እና አስተያየቶች እነርሱ ከሚያከናውኑበት እና ከሚያስቡበት መንገድ ሲለይ ወይም ሲጋጭ ሰዎች ስለሌሎች የሚታዩ ባህርያት፣ ድክመቶች እና አመለካከቶች አሉታዊ እንዲሁም ነውር የሆኑ አስተያየቶችን ሲሰጡ እናያለን። እነዚህ ሰዎች እንዲህ ያሉትን አስተያየቶች በአንድ ሁኔታ ዙሪያ ያለውን ሁኔታ በትክክል ሳያውቁ የሰሙትን ለሚደግሙ ለሌሎች ሲያስተላልፉ ማየት የተለመደ ነው። አለመታደል ሆኖ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች ይህንን አይነቱን ባህርይ በአንጻራዊ እውነትነት እና በግልጽነት ስም ያበረታቱታል። ገደብ የማይደረግባቸው ዲጂታል ውይይቶች ብስጭት በመፍጠር፣ ልብን በማቀሰል እና ሃይለኛ ጥላቻን በመፍጠር ብዙውን ጊዜ ሰዎችን ወደ ግላዊ ጥቃቶች እና ወደ ጦፈ አለመግባባት ይመራቸዋል።

ኔፊ በኋለኛው ቀናት ውስጥ ጠላት፣ “በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ይቆጣል እናም ጥሩ በሆነውም ላይ በቁጣ ያነሳሳቸዋል ሲል ተንብዩዋል።20 ቅዱሳት መጻህፍት “የእግዚአብሄር የሆነ ያለማቋረጥ መልካምን እንዲሰሩ ይጋብዛል እናም ይገፋፋል ስለዚህ መልካምን ለመስራት እና እግዚአብሄርን እንድናፈቅር እናም እንድናገለግለው የሚጋብዝ እናም የሚገፋፋ ማንኛውም ነገር ከእግዚሐብሄር የሆነ ነው” ሲሉ ያስተምራሉ።21 በሌላ በኩል፣ “መጥፎ የሆኑ ከዲያቢሎስ ይመጣሉ ዲያቢሎስም የእግዚሐብሄር ጠላት በመሆኑ ያለማቃረጥ ከእርሱ ጋር ይዋጋል እናም ሰዎች ሃጢያት እንዲሰሩ፣ እናም ያለማቋረጥ ክፉ የሆኑትን እንዲሰሩ ይጋብዛቸዋል፣ እንዲሁም ይገፋፋቸዋል።”22

ይህን ትንቢታዊ አስተምህሮ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በእግዚሐብሄር ልጆች ልብ ውስጥ ጠላትነትን እና ጥላቻን ማነሳሳት ከጠላት ዘዴዎች አንዱ መሆኑ የሚገርም አይድለም። ሰዎች አንዳቸው ሌላውን ሲተቹ፣ አንዳቸው በሌላው ላይ ሲሳለቁ፣ እና ሲሰዳደቡ ሲያይ ይደሰታል። ይህ ባህርይ በተለይም ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ሰውዬው በሚፈረድበት ጊዜ፣ የአንድን ሰው ባህሪይ፣ መልካም ስም እና በራስ መተማመን ሊያጠፋ ይችላል። ይህን አይነት ባህርይ በህይወታችን እንዲመጣ ስንፈቅድ ጠላት በልባችን ውስጥ አለመግባባቶችን እንዲፈጥር ቦታ እንደምንሰጥ እዲሁም በጠላት ወጥመድ ውስጥ የመውደቅ አደጋን እንደምንፈጥር መግለጹ አስፈላጊ ነው።

በሃሳቦቻችን፣ በቃላቶቻችን እና በተግባሮቻችን የማንጠነቀቅ ከሆኑ፣ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር እና ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነቶች በሚያጠፋ በጠላት የሚያጭበረብሩ ተንኮሎች ልንጠመድ እንችላልን።

ወንድሞች እና እህቶች፣ የጌታ የተለየን ህዝብ እንደመሆናችን እና የእርሱን ሰላም እንደምናስተዋውቅ ህዝብ፣ የዚህን ክፉ ማጭበርበሪያዎች በልቦቻችን ውስጥ እንዲካሄዱ መፍቀድ አንችልም። ስሜቶችን፣ ግንኙነቶችን እና ህይወትን የሚያጠፋ የሚያበላሽ ሸክምን መሸከም አንችልም። ወንጌል የታላቅ ደስታ ምስራችን ይወክላል።

እርግጥ ነው፣ ማናችንም ፍጹም አይደለንም እንዲሁም በርግጠኝነት ወደዚህ አይነቱ ባህርይ ተታልለን የምንገባባቸው ጊዜያቶች አሉ። ፍጹም በሆነው ፍቅሩ እና ስለሰብዓዊ ዝንባሌዎቻችን ባለው ፍጹም እውቀት፣ አዳኙ ሁል ጊዜ ስለእንደዚህ አይነት አደጋዎች ሊያስጠነቅቀን ይሞክራል። “በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና ፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።” ሲል አስተምሮናል።23

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እንደ አዳኙ አይነት ያሉ ባህሪያትን ለመገንባት ስንሞክር፣ እሱ ራሱ ባቋቋመው ምሳሌ መሰረት፣ በአለም ላይ የእሱ የሰላም መሳሪያዎች መሆን እንችላለን። ምግባረ መልካም፣ የሚያስደስት ወይም መልካም ሃተታ ወይም ምስጋና የሚገባውን ነገር እንፈልጋለን፣ እራሳችንን ወደ አበረታች እና አጽናኝ፣ የሚረዳና ይቅር የሚል ልብ ያለው እና በሌሎች ሰዎች ውስጥ ምርጡን የሚፈልግ ሰው መሆን የምንችልበትን መንገድ ከግንዛቤ ውስጥ እንድታስገቡ እጋብዛችኋለሁ።” 24

እነዚህን ባህሪያት ስንፈልግ እና ስናዳብር፣ የበለጠ ወዳጃዊ እና የወገኖቻችን ፍላጎቶች የሚሰሙን እንደምንሆን እና የደስታ፣ የሰላም፣ እና 25 የመንፈሳዊ እድገት ተሞክሮን እንደምናገኝ ቃል እገባላችኋለው። 26 ያለጥርጥር ጌታ ለጥረታችን እውቅና ይሰጣል እንዲሁም በመካከላችን ባሉ ልዩነቶች፣ ድክመቶች እና ጉድለቶች ይበልጥ እንድንቻቻል እና አንዳችን ሌላችንን በትዕግስት መያዝ እንድንችል ስጦታዎችን ይሰጠናል። በተጨማሪም፣ እንድንቀየም ወይም የጎዱንን ሰዎች እንድናስቀይም የሚገፋፋንን ስሜት ይበልጥ መቃወም የምንችል እንሆናለን። አዳኙ እንዳደረገው፣ የሚበድሉንን ወይም ስለኛ ክፉ የሚናገሩትን ይቅር ለማለት ያለን ፍላጎት በእርግጠኝነት ይጨምራል እንዲሁም የባህሪያችን አካል ይሆናል።

መቃብሩ ባዶ የሆነበትን ተአምር ለማክበር ስንዘጋጅ፣ በሚመጣው ሳምንት በዚህ የሆሳዕና በዓል የፍቅር ልብሳችንን እና የልግስና የዘንባባ ቅጠሎችን ዘርግተን በሰላሙ ልኡል መንገዶች ዛሬ እንራመድ። በክርስቶስ ወንድም እና እህት እንደመሆናችን፣ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፦ “በጌታ ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፣ ሆሳዕና በዓርያም” እያልን በደስታ እናውጅ። 27

ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ እንዲሁም በሃጢያት ክፍያው በኩል የተገለጸው ፍጹም ፍቅሩ ክእርሱ ጋር ለመራመድ እና በዚህ አለም እንዲሁም በሚመጣው አለም በእርሱ ሰላም ለመደሰት ለሚፈልጉ ሁሉ እንደሚሰጥ እመሰክራለሁ። እነዚህን ነገሮች የምለው በተቀደሰው በአዳኙ እና በቤዛው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።