ሆሳዕና ለልዑል እግዚአብሔር
የኢየሱስ ክርስቶስ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም መግባት እና ከዚያ በኋላ የተከናወኑት የሳምንቱ ክንውኖች ዛሬ በሕይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ የምንችላቸው ትምህርት ምሳሌዎች ይሆኑናል።
ዛሬ፣ እንደተባለው፣ በዚህ የሆሳዕና በዓል በዓለም ዙሪያ ካሉ ክርስቲያኖች ጋር ኢየሱስ ክርስቶስን ለማክበር ተሰብስበናል። ከ 2,000 ዓመታት ገደማ በፊት፣ የሆሳዕና ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎት የመጨረሻ ሳምንት መጀመሩን አመልክቷል። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጣም አስፈላጊው ሳምንት ነበር።
በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም በገባበት ወቅት ኢየሱስ ተስፋ የተደረገበት መሲህ እንደሆነ በመሰበክ የጀመረው በስቅለቱ እና በትንሳኤው ተዘግቷል።1 በመለኮታዊ ንድፍ፣ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ምድራዊ አገልግሎቱን ጨርሷል፣ ይህም ከሰማይ አባታችን ጋር ለዘለአለም እንድንኖር አስችሎናል።
ሳምንቱ ሲጀምር “ከገሊላ ናዝሬት የመጣውን ነቢዩ ኢየሱስን” ለማየት ብዙ ሰዎች በከተማይቱ በር ላይ ቆመው እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል።2 “የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና“ ሆሣዕና፦ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከነው እያሉ ጮኹ።”3
ያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የጥንት ታሪክ በቤተክርስቲያኗ የስራ ምድብ በታኮራዲ፣ ጋና የነበርኩበትን ጊዜ ያስታውሰኛል። በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ ለሆሳዕና በዓል እዚያ ነበርኩኝ።
የሜፒንትሲን ጋና ካስማን ለመፍጠር የታኮራዲ ጋና ካስማን ለሁለት መክፈል ነበረብኝ። ዛሬ፣ በጋና ውስጥ ከ100,000 በላይ የቤተክርስቲያኗ አባላት አሉ።4 (ዛሬ በመካከላችን የሚገኙትን የጋና አክራውን ግርማዊነታቸው ዳግማዊ ኒ ታኪ ቴይኮ ሱሩ እንኳን ደህና መጡ እንላለን።) ከእነዚህ ቅዱሳን ጋር ስገናኝ ለጌታ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር እና ታማኝነት ተሰማኝ። እኔ ለእነሱ ያለኝን ታላቅ ፍቅር እንዲሁም የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት እንደሚወዳቸውም ገለጽኩ። በዮሐንስ የተዘገበውን “እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ” የሚሉትን የአዳኙን ቃላት ጠቅሼ ነበር፡-5 “የእወዳችኋለሁ ጉባኤ” አድርገው ቆጥረውታል።6
በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ውድ ወንድሞች እና እህቶች እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው የተቀመጡባቸውን ረድፎች ወደላይ እና ወደ ታች ስመለከት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን የምስክርነት እና የእምነት ብርሃን በፊታቸው አየሁ። እሩቅ የምትደርሰው የእርሱ ቤተክርስቲያን አካል ሆነው ለመቆጠር ያላቸው ፍላጎት ተሰማኝ። እንዲሁም መዘምራኑ ሲዘምሩ፣ ዝማሬያቸው እንደ መላእክት ነበር።
ልክ እንደ ጥንቱ የሆሳዕና በዓል፣ እነዚህ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ምስጋና ሊያቀርቡለት በኢየሩሳሌም ደጃፍ ተሰብስበው “ሆሣዕና…: በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው” ብለው እንደጮሁት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነበሩ።7
በአቅራቢያው ባለ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ምዕመናን እንኳን የሆሳዕና በዓልን እያከበሩ ነበር። መድረክ ላይ ሆኜ እየተናገርኩ ሳለሁ፣ በዚህ ፎቶ ላይ እንዳሉት የዘንባባ ዝንጣፊ እያወዛወዙ ሲሄዱ በመስኮት አስተዋልኩ። መቼም የማልረሳው እይታ ነበር—ያን ቀን ሁላችንም የነገስታት ንጉሱን እያመለክን ነበር።
ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “የኢየሱስን ወደ እየሩሳሌም መግባት ለማክበር የተወዛወዙትን ዘንባባዎች ብቻ ሳይሆን የእጆቹን መዳፍ በማስታወስ የሆሳዕና በአልን በእውነት ቅዱስ እንድናደርግ መክረውናል። ከዚያም ፕሬዚዳንት ኔልሰን “እነሆ፣ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ” በሚሉ ቃላት አዳኙ ‘በፍጹም አልረሳሽም’ ሲል ስለሰጠው ተስፋ የተናገረውን ኢሳይያስን ጠቅሰዋል።8
ምድራዊ ህይወት ከባድ እንደሆነ ጌታ በራሱ ያውቃል። ቁስሎቹ እርሱ “ከሁሉ በታች እንደወረደ”9 ያስታውሱናል፣ ስንሰቃይ እኛን ለመርዳት እና “መንገ[ዳችን]ን ለመቀጠል”10 ለኛ ምሳሌ ለመሆን፣ “እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም [ከእኛ ጋር] ይሆናል።”11
የሆሳዕና በዓል፣ ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ያለው ሌላ የታሪክ ገጽ ክስተት ብቻ አልነበረም። የኢየሱስ ክርስቶስ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም መግባት እና ከዚያ በኋላ የተከናወኑት የሳምንቱ ክንውኖች ዛሬ በሕይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ የምንችላቸው ትምህርት ምሳሌዎች ይሆኑናል።
አገልግሎቱን በእየሩሳሌም ውስጥ ሲያጠናቅቅ የነበሩትን አንዳንድ ዘላለማዊ ትምህርቶች እንመልከት።
በመጀመሪያ፣ ትንቢት። ለምሳሌ፣ የብሉይ ኪዳን ነቢይ የነበረው ዘካርያስ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ላይ እንደሚሄድ ጭምር በመግለጽ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚገባ ተንብዮአል።12 ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ ለመግባት ሲዘጋጅ እንዲህ በማለት ስለ ትንሳኤው አስቀድሞ ተናግሯል፡-
“እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ተላልፎ ይሰጣል፣ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል።
“ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።”13
ሁለተኛ፣ የመንፈስ ቅዱስ ወዳጅነትት። ጆሴፍ ስሚዝ ፣ “በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ማንም ሊያውቅ አይችልም፣ ሲል አስተምሯል።”14 አዳኙ በሰገነቱ ላይ በተደረገው15 የመጨረሻው እራት ላይ16 ፣17 “መጽናናት እንደሌለው አልተዋችሁም።”18 ሲል ለደቀ መዛሙርቱ ቃል ገብቷል። የወንጌልን እውነት ወደፊት ለማስኬድ ብቻቸውን አይሆኑም ነገር ግን የሚመራቸው የመንፈስ ቅዱስ ፍፁም ስጦታ ይኖራቸዋል። “ሰላምን እተውላችኋለሁ፡ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፣ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እነደሚሰጣችሁ አይደለም”19 ሲል ቃል ገብቷል። በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ “መንፈሱ ሁልጊዜ [ከእኛ] ጋር ይሆን ዘንድ”20 እንዲሁም “በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሁሉንም ነገር እውነታ እናውቅ ዘንድ” 21 ያ ተመሳሳይ ማረጋገጫ አለን።
ሶስተኛ፣ ደቀመዝሙርነት። እውነተኛ ደቀመዝሙርነት የማይሻር ቁርጠኝነት፣ ለዘላለማዊ ህግጋቶች መታዘዝ እና፣ ከሁሉም በፊት እግዚአብሔርን መውደድ ነው። ያለ ምንም መወላወል። ዘንባባ በመያዝ ያመሰገኑት ብዙዎቹ ሰዎች መሲህ ብለው አወድሰውታል። እርሱ በትክክል ያ ነበር። ወደ እርሱ፣ ወደ ተአምራቱ፣ እና ወደ ትምህርቶቹ ተስበው ነበር። የብዙዎቹ አድናቆት ግን አልዘለቀም። ቀደም ሲል “ሆሣዕና”22 ብለው የጮኹ አንዳንዶች ብዙም ሳይቆይ ዘወር ብለው “ስቀለው”23 እያሉ ጮኸዋል።
አራተኛ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ።24 በእርሱ የመጨረሻ ቀናት፣ የሆሳዕና በዓልን ተከትሎ፣ ከጌቴሴማኒ ስቃይ እስከ ችሎቱ ስላቅ፣ በመስቀል ላይ ከነበረው ስቃይ ተውሶ መቃብር እስከመቀበር ድረስ አስደናቂ የኃጢያት ክፍያውን ፈጽሟል። ግን በዚህ ብቻ አላቆመም። ለአባቱ ልጆች ሁሉ ቤዛ በሆነው ታላቅ ጥሪው፣ እንደተነበየው ከሶስት ቀናት በኋላ ከዚያ መቃብር ወጣ፣ ትንሰኤን25 አደረገ።
ወደር ለሌለው የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ያለማቋረጥ አመስጋኞች ነን? የማንጻት ኃይሉ አሁን ይሰማናል? ለዚህ ነበር የእምነታችን ራስና ፈፃሚው ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችንን ለማዳን ወደ ኢየሩሳሌም የሄደው። በአልማ ውስጥ ያሉት እነዚህ ቃላት ጥሩ ስሜት ይፈጥራሉ፦ “የልብ መለወጥን የሚሰማችሁ ከሆነ፣ እናም የቤዛነት የፍቅር ዜማ ለመዘመር ከተሰማችሁ አሁንም ሊሰማችሁ ይችላል?”26 በዚያ የሆሳዕና በዓል በታኮራዲ ውስጥ ያሉ መዘምራን በእውነት “የቤዛ ፍቅር መዝሙር” ዘመሩ ብዬ መናገር እችላለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ የምድራዊ አገልግሎቱ የመጨረሻ ሳምንት ስለ አስሩ ደናግላን ምሳሌ ተናግሯል።27 እርሱን ለመቀበል ለተዘጋጁት በእጃቸው በያዙት ዘንባባ ሳይሆን ነገር ግን በውስጣቸው ባለው የወንጌል ብርሃን ስለ ዳግም ምጽዓቱ ያስተምር ነበር፣። የተለኮሱ እና የሚነዱ መብራቶችን እና እሳቱ መንደዱን እንዲቀጥል የሚያስፈልገውን የተጨማሪ ዘይት ምስል መንገዶቹን፣ እውነቶቹን እና ብርሃኑን ለማካፈል ፈቃደኛ መሆንን ለመግለፅ ተጠቅሞባቸዋል።
ታሪኩን ታውቁታላችሁ። አስሩ ደናግላን የቤተክርስቲያን አባላትን ይወክላሉ፣ እና ሙሽራው ኢየሱስ ክርስቶስን ይወክላል።
አሥሩ ደናግላን መብራታቸውን ይዘው “ሙሽራውን ሊቀበሉ ወጡ።”28 አምስቱ ልባሞች ነበሩ ለመብራታቸው መጠባበቂያ ዘይት ይዘው ተዘጋጅተው ነበር፥ አምስቱም ሰነፎች ነበሩ፥ መጠባበቂያ ዘይት አልያዙም ነበር። “እነሆ፣ ሙሽራው ይመጣል፣ ልትቀበሉት ውጡ፣” የሚለው ጥሪ በመጣ ጊዜ፣ 29 አምስቱ “ጥበበኞችና እውነትን የተቀበሉ መንፈስ ቅዱስንም መሪያቸው ያደረጉ፣”30 31 “ክብሩ [በእነርሱ] ላይ [ይሆን]”32ዘንድ “ንጉሣቸውንና ሕግ ሰጪያቸውን” ለመቀበል ዝግጁ ነበሩ። የተቀሩት አምስቱ ዘይት ለማግኘት በጥድፊያ እየሞከሩ ነበር። ነገር ግን በጣም ዘግይተው ነበር። ዝግጅቱ ያለ እነርሱ ተከነናወነ። አንኳኩተውም ለመግባት ሲለምኑ፣ ጌታ፣ “አላውቃችሁም” ሲል መለሰ።33
“አላውቃችሁም!” ቢለን ምን ይሰማናል።
እንደ አስሩ ደናግላን፣ መብራቶች አሉን፤ ነገር ግን ዘይት አለን? በትክክል ለመዘጋጀት እንዳይችሉ በዓለማዊ ግፊቶች በጣም የተጠመዱ ትንሽ ዘይት ብቻ ያላቸው አንዳንድ አሉ ብዬ እፈራለሁ። ዘይት፣ በህይወት ያሉ ነብያት፣ በተለይም ፕሬዚዳንት ኔልሰን፣ አማካሪዎቹ እና አስራ ሁለቱ ሐዋርያት የሚናገሩትን ትንቢት እና ቃል በማመን እና በመተግበር ይመጣል። መንፈስ ቅዱስን ስንሰማ እና በዚያ መለኮታዊ መመሪያ ላይ ተግባራዊ እርምጃ ስንወስድ ዘይቱ ነፍሳችንን ይሞላል። ምርጫዎቻችን ጌታን እንደምንወደው እና እርሱ የሚወደውን እንደምንወድ በሚያሳይበት ጊዜ ዘይት ወደ ልባችን ይፈስሳል። ዘይት ንስሐ በመግባት እና የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ ፈውስ በመፈለግ ይመጣል።
አንዳንዶች “ማጠራቀሚያ ዝርዝር” ብለው የሚጠሩትን ለመሙላት የምትፈልጉ ከሆነ ይህን አድርጉ፦ በኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ውኃ መልክ ማጠራቀሚያችሁን በዘይት ሙሉ፣34 ይህም የሕይወቱና የትምህርቱ ምሳሌ ነው። በተቃራኒው፣ ራቅ ያለ ቦታን ወይም አስደናቂ ዝግጅትን ማየት አለማየትን ማረጋገጥ ነፍሳችሁ ሙሉ እንድትሆን ወይም እርካታ እንዲሰማት በጭራሽ አያደርግም። ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው ትምህርት መሠረት መኖር ነፍሳችሁ እንደዚያ እንዲሰማት ያደርጋል። ምሳሌዎችን ቀደም ብዬ ጠቅሻለሁ፦ ትንቢትን እና ትንቢታዊ ትምህርቶችን ተቀበሉ፣ በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት ላይ ተግባራዊ እርምጃ ውሰዱ፣ እውነተኛ ደቀ መዝሙር ሁኑ እንዲሁም የጌታችንን የሀጢያት ክፍያ የፈውስ ሀይል ፈልጉ። ያ የማጠራቀሚያ ዝርዝር መሄድ ወደምትፈልጉበት በሰማይ ወዳለው አባታችሁ ቦታ ይወስዳችኋል።
በታኮራዲ የነበረው ያ የሆሳዕና በዓል ለእኔ በጣም ልዩ ተሞክሮ ነበር፤ ምክንያቱም ታሪኩን ለታማኝ ወንድሞችና እህቶች ጉባኤ ስላካፈልኩ ነበር። ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ባሉ አህጉሮች እና ደሴቶች ላይ አለ። ልቤም ነፍሴም እንደ አናንተ “ሆሣዕና ለልዑል እግዚአብሔር” ብላ መጮህ ትፈልጋለች።35
ዛሬ በኢየሩሳሌም ደጃፍ ላይ ዘንባባ በእጃችን ይዘን ባንቆምም በራእይ በትንቢት እንደተነገረው “እነሆም አንድም እንኳን ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም የሆነ እጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት የሚቆሙበት” ጊዜ ይመጣል። 36
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ በጽድቅ ለመኖር እንድትተጉ እንዲሁም በእጃቸው ዘንባባ ይዘው የሁላችንም ታላቅ ቤዛ ስለሆነው ስለእግዚአብሔር ልጅ ከሚያበስሩት መካከል እንድትሆኑ በረከቴን እተውላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።