ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፬፥፳፭–፵። ከዘፍጥረት ፲፬፥፲፰–፳ ጋር አነጻፅሩ
መልከ ጼዴቅ አብርሐምን ባረከ። የመልከ ጼዴቅ ታላቅ አገልግሎት እና የመልከ ጼዴቅ ክህነት በረከቶች ተዘርዝረዋል።
፳፭ እና መልከ ጼዴቅ ደምጹን ከፍ አደረገ እና አብራምን ባረከው።
፳፮ አሁን መልከ ጼዴቅ ጽድቅን ያደረገ የእምነት ሰው ነበር፤ እና በልጅነት እግዚአብሔርን የፈራ፣ እና የአንበሳን አፍ የዘጋ፣ እና የእሳትን ሀይል ያጠፋ ነበር።
፳፯ በእግዚአብሔር ተቀባይ ከሆነ በኋላ፣ እግዚአብሔር ከሔኖክ ጋር በገባው ቃል ኪዳን ስርዓት መሰረት እንደ ሊቀ ካህን ተሹሞ ነበር።
፳፰ ይህም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስርዓት አይነት ነበር፤ ይህም ስርዓት ከእግዚአብሔር እንጂ፣ በሰው ወይም በሰው ፍላጎት፤ በአባት ወይም እናት፣ መጀመሪያ ቀናት ወይም መጨረሻ አመታት የሌለው ነበር።
፳፱ ለሰዎችም፣ በስሙ ለሚያምኑት ሁሉ፣ የተሰጠው በእራሱ ድምፅ ጥሪ፣ በእራሱ ፍላጎት በኩል ነበር።
፴ እያንዳንዱ በዚህ ስርዓት የሚሾመውና የሚጠራው በእምነት ተራራዎችን ለመስበር፣ ባህሮችን ለመከፋፈል፣ ውሀዎችን ለማድረቅ፣ ከመንገዳቸው ለማዞር ሀይል እንደሚኖረው እግዚአብሔር በራሱ ለሔኖክ እና ለዘሩ መሀላ ምሏልና፤
፴፩ የህዝቦችን ሰራዊቶች በግልፅ ለመቃወም፣ ምድርን ለመከፋፈል፣ እያንዳንዱን ቡድን ለመስበር፣ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም፣ ሁሉንም ነገሮች በፍላጎቱ መሰረት፣ በትእዛዙ መሰረት ለማድረግ፣ ግዛትንና ሀይላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘንድ ሀይል እንደሚኖረው እግዚአብሔር ለሔኖክ እና ለዘሩ በራሱ መሃላ ገብቶላቸዋልና፤ እና ይህም ከአለም መሰረት በፊት በነበረው በእግዚአብሔር ልጅ ፍላጎት ነው።
፴፪ እና ሰዎች ይህ እምነት ኖሮአቸው፣ ወደዚህ የእግዚአብሔር ስርዓት በመምጣት ተለውጠዋል እና ወደሰማይም አርገዋል።
፴፫ አሁን መልከ ጼዴቅ በዚህ ስርዓት ውስጥ ካህን ነበር፤ ስለዚህ በሳሌም ቦታ አገኘ፣ እና የሰላም ልዑል ተብሎም ተጠርቶ ነበር።
፴፬ እና ህዝቦቹ ጻድቅነትን አመጡ፣ ሰማይንም አገኙ፣ እና እግዚአብሔር ከምድር አለያይቶ በፊት የወሰዳትን፣ ለኋለኛው ቀናት ወይም ለአለም መጨረሻ የያዛትን፣ የሔኖክን ከተማ ፈለጉ፤
፴፭ እና ሰማያት እና ምድር እንደገና አብረው እንዲጠቀለሉ፣ እና የእግዚአብሔር ልጆች እንደ እሳት እንዲፈተኑ ዘንድ እንዲህም አለ፣ መሀላ ማለ።
፴፮ እና ይህ መልከ ጼዴቅ እንደዚህም ጻድቅነትን በመመስረት የሰማይ ንጉስ ተብሎ በህዝቡ ተጠርቶ ነበር፣ ወይም በሌላ ቃሎችም፣ የሰላም ንጉስ።
፴፯ እና ድምጹን ከፍ አደረገ፣ እና ሊቀ ካህን እና የእግዚአብሔር ጎተራ ጠባቂ ስለሆነም አብራምን ባረከ፤
፴፰ እርሱም ለደሀዎች አስራት እንዲቀበል እግዚአብሔር መደበው።
፴፱ ስለዚህ፣ አብራም ላላቸው ሁሉ፣ ከሚያስፈልገው በላይ እግዚአብሔር ለሰጠው ካለው ሀብቶች ሁሉ አስራት ለእርሱ ከፈለ።
፵ እና እንዲህ ሆኖ አለፈ፣ እግዚአብሔር አብራምን ባረከው፣ እና በገባው ቃል ኪዳን መሰረት፣ እና በመልከ ጼዴቅ በባረከው በረከቶች መሰረት፣ ሀብቶችን፣ ክብርን፣ እና መሬቶችን ለዘለአለም የእራሱ እንዲያደርጋቸው ሰጠው።