ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬፥፳–፳፮። ከማርቆስ ፲፬፥፳፪–፳፭ ጋር አነጻፅሩ
ኢየሱስ ቅዱስ ቁርባንን ለእርሱ ስጋ እና ደም መታሰቢያነት መሰረተ።
፳ ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና አላቸው፣ እንካችሁ፣ ብሉ።
፳፩ እነሆ፣ ይህም ሰውነቴን ለማስታወስ ነው፤ ይህን በየጊዜው ስታደርጉም ከእናንተ ጋር የነበርኩበትን ሰአት ታስታውሳላችሁና።
፳፪ ጽዋንም አንሥቶ፣ እና ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።
፳፫ እና እንዲህም አላቸው፣ ይህም ለብዙዎች የሚፈስ፣ እና የምሰጣችሁ የአዲስ ኪዳን ደሜን ለማስታወስ ነው፤ ስለእኔ ለአለም ሁሉ ምስክር ትሰጣላችሁና።
፳፬ ይህን ስነስራአት በየጊዜው ስታደርጉም፣ ከእናንተ ጋር የነበርኩበትን እና ከጸዋው ከእናንተ ጋር የጠጣሁበትን፣ እንዲሁም የአግልግሎቴ የመጨረሻ ጊዜን፣ ይህን ሰአት ታስታውሳላችሁ።
፳፭ እውነት እላችኋለሁ፣ ስለዚህ ምስክር ስጡ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከእናንተ ጋር ደግሞ አልጠጣውምና።
፳፮ እና አሁን እነርሱም አዝነው ነበር፣ በእርሱም ላይ አለቀሱ።
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬፥፴፮–፴፰። ከማርቆስ ፲፬፥፴፪–፴፬ ጋር አነጻፅሩ
በጌቴሴማኒ፣ አስራ ሁለቱም ቢሆኑ የኢየሱስን መሲህነት ሚና ሙሉ በሙሉ አልተረዱትም።
፴፮ ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ቦታ መጡ፣ ይህም አትክልት ስፍራ ነበር፤ እና ደቀመዛሙርቱ መደነቅ ጀመሩ፣ እና በጣምም ተጨነቁ፣ እና ይህ መሲህ እንደሆነ እያሰቡ በልቦቻቸውም ቅሬታ ተሰማቸው።
፴፯ እና ኢየሱስ ልቦቻቸውን በማወቅ ደቀ መዛሙርቱንም፣ ስጸልይ ሳለሁ፣ በዚህ ተቀመጡ አላቸው።
፴፰ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ እና ገሰጻቸው፣ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ትጉም አላቸው።