የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፰


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፰፥፴፯–፴፰።ማርቆስ ፰፥፴፭ ጋር አነጻፅሩ

ስለኢየሱስ ለመሞት ፈቃደኛ የሆነ ደህንነትን ይቀበላል።

፴፯ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ወይም ነፍሱን ሊያድን የሚወድ፣ ስለእኔ ይህችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ይሆናል፤ እናም ስለእኔ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ያለሆነ፣ እርሱም ያጠፋታል።

፴፰ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን ለማጥፋት ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ ግን ያድናታል።

ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፰፥፵፪–፵፫።ማርቆስ ፰፥፴፰ ጋር አነጻፅሩ

በክርስቶስ የሚያፍሩት በመጀመሪያው ትንሳኤ ምንም ክፍል የላቸውም፣ ስለክርስቶስ ለመሞት ፈቃደኛ የሆኑት ግን ከእርሱ ጋር በክብሩ ይመጣሉ።

፵፪ ሲመጣም በዚያ ትንሳኤ ክፍል አይኖራቸውም።

፵፫ በእውነት እላችኋለሁ፣ እርሱም ይመጣል፤ እና ስለእኔ እና ስለወንጌል ህይወትን የሚሰጥ፣ ከእርሱ ጋር ይመጣል፣ እናም በሰው ልጅ ቀኝ በኩልም በዳመና ውስጥም በክብሩ ይለበሳል።