የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፮


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፮፥፫–፮።ማርቆስ ፲፮፥፬–፯ሉቃስ ፳፬፥፪–፬ ጋር አነጻፅሩ

ሁለት መላእክቶች ሴቶችን በአዳኝ መቃብር አጠገብ ሰላም አሏቸው።

ነገር ግን ሲመለከቱ፣ ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ (ይህም እጅግ ትልቅ ነበርና፣) እና ነጭ ልብስ የተጎናጸፉ ሁለት መላእክቶች በዚህ ላይ ተቀምጠው አዩና ደነገጡ።

ነገር ግን መላእክቶቹ አትደንግጡ አሉአቸው፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።

እና ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው።

እና እነርሱ ወደመቃብር ውስጥ በመግባት ኢየሱስን ያኖሩበትን ስፍራ ተመለከቱ።