የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱


ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱፥፫።ማርቆስ ፱፥፬ ጋር አነጻፅሩ

መጥምቁ ዮሐንስ በመለወጫ ተራራ ላይ ነው።

እና ኤልያስ ከሙሴም ጋር ታዩአቸው፣ ወይም በሌላ ቃላት፣ መጥምቁ ዮሐንስ እና ሙሴ፤ እና ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር።

ጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፱፥፵–፵፰።ማርቆስ ፱፥፵፫–፵፰ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ የሚያሰናክል እጅን ወይም እግርን መቁረጥ ወደ ተሳሳተው መንገድ ከሚመራ ሰው ጓደኝነት ማስወገድ ጋር አነጻፅሯል።

ስለዚህ፣ እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ወይም ወንድምህ ካሰናከለህ እና ካልተናዘዘ እና ካልተወው፣ እርሱም ይቆረጣል። ሁለት እጅ ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።

፵፩ አንተ እና ወንድምህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄዳችሁ፣ አንተ ወደ ህይወት ካለወንድምህ መግባት ይሻላልና።

፵፪ እንደገናም፣ እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ መሰረትህ የሆነው፣ የምትራመድበት፣ ተላላፊ ከሆነ፣ እርሱም ይቆረጣል።

፵፫ ሁለት እግር ኖሮህ እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

፵፬ ስለዚህ እያንዳንዱም ሰው ለሌላ፣ ወይም ሌላን በማመን ሳይሆን፣ ለእራሱ ይቁም ወይም ይውደቅ።

፵፭ አባቴን ጠይቁ፣ እና እንደምትቀበሉ እምነት ኖሮአችሁ፣ በእምነት ከጠየቃችሁ በምትጠይቁበት ወዲያው ይደረግላችኋል።

፵፮ የሚያይላችሁ አይናችሁ፣ ብርሀን እንዲያሳያችሁ እንዲጠብቃችሁ የተመደበላችሁ፣ ተላላፊ ሆኖ ካሰናከላችሁ፣ አውጡት።

፵፯ ሁለት አይኖች ኖሮህ ወደ ገሃነም እሳት ከመጣል በአንድ አይን ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት ይሻልሃል።

፵፰ አንተ ከወንድምህ ጋር ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመሄዳችሁ፣ አንተ ብትድን ይሻላልና።