መፅሐፈ አብርሐም
በጆሴፍ ስሚዝ ከፓፓይረስ የተተረጎመ
ከግብፅ መቃብር ስፍራዎች በእጆቻችን ውስጥ ከገቡት አንዳንድ የጥንት መዛግብት ትርጉም። መፅሐፈ አብርሐም ተብሎ የተጠራው፣ አብርሐም በግብፅ እያለ በፓፓይረስ ላይ በእራሱ እጆች የተጻፉ ፅሁፎች።
ምዕራፍ ፩
አብርሐም የፔትሪያርካዊ ስርዓት በረከትን ፈለገ—በከላውዴዎ ውስጥ በሐሰት ቀሳውስት ተንገላታ—ያህዌህ አዳነው—የግብፅ ጅማሬ መንግስትም ተከለሰ።
፩ በአባቴ መኖሪያ በከለዳውያን ምድር ውስጥ፣ እኔ አብርሐም ሌላ የመኖሪያ ስፍራን ማግኘት እንዳለብኝ አወቅሁኝ።
፪ እና ታላቅ ደስታና ሰላም እናም እረፍት ለእኔ እንዳሉም ስላወቅሁኝ፣ የአባቶችን በረከቶች ለማግኘት እና ይህንንም ለማስተዳደር መብትም ለማግኘት ለመሾምም ፈለግሁኝ፤ የጻድቅ ተከታይ በመሆኔ፣ እና ታላቅ እውቀቶችን ለመረከብ፣ እናም ከዚህም በላይ ታላቅ ጻድቅ ተከታይ ለመሆን፣ እና ከዚህም ታላቅ የሆኑ እውቀቶችን ለመረከብ፣ እና የብዙ ሀገሮች አባትና የሰላም መስፍን ለመሆንም ፍላጎት ስለነበረኝ፣ እናም ትምህርትንም ለመቀበል፣ እናም የእግዚአብሔርን ትእዛዛትን አክባሪ ለመሆን ስለፈለግሁኝ፣ መብት ያለው ወራሽ፣ የአባቶችን መብት የሚይዘው ሊቀ ካህን ሆንኩኝ።
፫ ይህም ከአባቶች ተሰጥቶኝ ነበር፤ ይህም ከጊዜ መጀመሪያ፣ አዎን፣ እንዲሁም ከመጀመሪያው፣ ወይም ከምድር መመስረት በፊት እስከ አሁን ድረስ ከአባቶች የመጣው፣ በአባቶች በኩል ወደ እኔ የመጣው፣ እንዲሁም የበኩር ልጅ፣ ወይም የአዳም የመጀመሪያ ሰው፣ ወይም የመጀመሪያው አባት መብት ነበር።
፬ እግዚአብሔር ስለዘር በሚመለከት ለአባቶች እንደመደበው የራሴን ወደ ክህነት መመደብን ፈለግሁኝ።
፭ አባቶቼም፣ ከፅድቅና ከጌታ አምላካቸው ከሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዛቱ ዞር ብለው፣ የአሕዛብ አማልክትን እያመለኩ፣ ድምጼንም ለመስማትም በፍጹም እምቢ አሉ።
፮ ልባቸውም ክፉ ለማድረግ ፈቅደው ነበርና፣ እናም ወደ ኤልከናኽ አምላክ፣ ሊብናኽ አምላክ፣ ማህማርከራኽ አምላክ፣ ቆራሽ አምላክ፣ እናም ወደ ግብፅ ንጉስ ፈርዖን አምላክ በጠቅላላ ዞረዋል።
፯ ስለዚህ ልጆቻቸውን ለመናገር ወደማይችለው ጣኦት ለመሰዋት ልቦቻቸውን ወደ አሕዛብ መስዋዕት ዞረዋል፣ እና ድምጼንም አያደምጡም፣ ነገር ግን ህይወቴን በኤልከናኽ ቄስ ለመውሰድ ፍላጎት ነበራቸው። የኤልከናኽ ቄስ የፈርዖን ቄስም ነበር።
፰ አሁን፣ በዚህ ጊዜ በከለዳውያን ሀገር ውስጥ በተሰራው መሰዊያ ድንጋይ ላይ ለእነዚህ ልዩ አማልክቶች ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን መሰዋት በግብፅ ንጉስ በፈርዖን ቄስ በኩል የማቅረብ ልምድ ነበር።
፱ እንዲህም ሆነ በግብጻዊው ልምድ በኩል ቄሱ ለፈርዖው አማልክት እና ደግሞም ለሻግሪል አማልክት መስዋዕት አቀረበ። አሁን የሻግሪል አማልክት ጸሀይ ነበር።
፲ ኦሊሸም ሰፈር መጀመሪያ ላይ በሚገኘው በጲጥፋራ ተራራ ላይ ባለው መሰዊያ ላይ የፈርዖኑ ቄስ ለምስጋና ልጅን እንደመስዋዕት አቀረበ።
፲፩ አሁን፣ ከካመን የንጉሳዊ ቤተሰብ የተወለዱትን ሶስት የኦኒታን ድንግል ሴት ልጆችን በዚህ መሰዊያ ላይ መስዋዕትን ይህም ቄስ አቀረበ። እነዚህ ደናግል እንደ መስዋዕት የቀረቡት በምግባረ መልካምነታቸው ምክንያት ነበር፤ እነርሱም ለእንጨት ወይም ለድንጋይ አምላክት አናመልክም ስላሉ፣ በመሰዊያው ድንጋይ ላይ ተገደሉ፣ እና ይህም የተደረገው የግብጻውያንን ስርአት በመከተል ነበር።
፲፪ እና እንዲህ ሆነ ቀሳውስትም በመሰዊያው ላይ ደናግሉን መስዋዕት እንዳደረጉት፣ እኔን ይገደሉ ዘንድ በሀይል ያዙኝ፤ እና መሰዊያው ምን አይነት እንደሆነ ታውቁ ዘንድ፣ ከዚህ መዝገብ መጀመሪያ ላይ ያለውን ስእል እንድትመለከቱ እመራችኋለሁ።
፲፫ በከለዳውያን ሀገር ውስጥ እንደሚሰራው አይነት መኝታ የሚመስል ነበር፣ እና ከኤልከናኽ፣ ሊብናኽ፣ ማህማርከራኽ፣ ቆራሽ አምላክቶች፣ ደግሞም እንደ ግብፅ ንጉስ በፈርዖን አምላክ ፊትም የቆመ ነበር።
፲፬ ስለነዚህ አማልክት ይገባችሁ ዘንድ፣ መግለጫን ከዚህ መጀመሪያ ላይ በቅርስነት ሰጥቻችኋለሁ፣ ቅርሶቹም ሃይሮግሊፊኮችን የሚገልጡ የከለዳውያን ራህሊኖስ አይነት ነበሩ።
፲፭ በመስዋዕት ህይወቴን ለማሳለፍ እጆቻቸውን ሲያነሱም፣ እነሆ፣ ድምጼን ወደ ጌታ አምላክ ከፍ አደረግሁኝ፣ እና ጌታም አደመጠ እና ሰማ፣ እና ሁሉን በሚገዛው ራዕይ ሞላኝ፣ እና ከእርሱ ፊት የሚገኝ መልአክ በአጠገቤ ቆመ፣ እና ወዲያው እጄን ፈታው።
፲፮ ድምጹም ለእኔ ነበር፥ አብርሐም፣ አብርሐም፣ እነሆ፣ ስሜ ያህዌህ ነው፣ እና ሰምቼሀለሁ፣ ላድንህና ከአባትህ ቤትና ከቤተሰቦችህ ወስጄህ ወደማታውቀው እንግዳ ምድር ልወስድህ መጥቼአለሁ።
፲፯ ይህም የኤልከናኽ፣ የሊብናኽ፣ የማህማርከራኽ፣ የቆራሽ አምላክቶች እናም የግብፅ ንጉስ ፈርዖን አምላክን በማምለክ ልቦቻቸውን ከእኔ ዞር አድርገው ስለነበር ነው፤ ስለዚህ እነርሱን ለመጎብኘትና የአንተ የልጄን አብርሐምን ህይወት ለመውሰድ እጁን ያነሳውን ለማጥፋት መጥቼአለሁ።
፲፰ እነሆ፣ በእጄም እመራሀለሁ፣ እናም የእኔን ስም እንዲሁም የአባቶችህን ክህነት በአንተ ላይ ለማድረግ እወስድሀለሁ፣ ሀይሌም በአንተ ላይ ያርፋል።
፲፱ በኖህም እንደነበረም ለአንተም ይሆናል፤ ነገር ግን በአንተ አልግሎት ምክንያት በኩል የእኔ ስም ለዘለአለም ይታወቃል፣ እኔም የአንተ አምላክ ነኝና።
፳ እነሆ፣ የጲጥፋራ ተራራ በከላውዳውያን ምድር በዑር ከተማ ውስጥ የሚገኝ ነበር። ጌታም የኤልከናኽንና የሌሎቹን የምድር አማልክት መሰዊያ ሰበረ፣ እና ፈጽሞም አጠፋቸው፣ እና ቄሱንም ገደለው፤ በከለዳውያንና በፈርዖን ቤትም ታላቅ ሀዘን ነበር፤ ፈርዖንም የንጉሳዊ ደምን የሚያመለክት ነበር።
፳፩ አሁን ይህ የግብፅ ንጉስም ከካምን ትውልድ ዘር ነበር፣ እና በትውልድም የከነዓናዊ ደም ተካፋይ ነበር።
፳፪ ከዚህም ትውልድ ግብጻውያን ሁሉ መጡ፣ በዚህም የከነዓናዊያን ደም በምድር ላይ ተጠበቀ።
፳፫ የግብፅ ምድርም መጀመሪያ የተገኘው በካምን ሴት ልጅ በሆነች ሴት፣ እና በከላውዴዎን ግብፅን በሚያመለክተው፣ ክልክል ማለት በሆነው በግብፅዎስ ሴት ልጅ ነበር።
፳፬ ይህን ምድር ስታገኘውም በውሃ የተዋጠ ነበር፣ ከዚያም ወንድ ልጆቿን እንዲሰፍሩበት አደረገች፤ እና እንደዚህ ከካምን እርግማኑን በምድር ላይ እንዲቀጥሉ የሚያደርጉ ዘሮች ተነሱ።
፳፭ የመጀመሪያው የግብፅ መንግስት የተመሰረተውም በካምን ሴት ልጅ ግብፅዎስ ልጅ ፈርዖን ነበር፣ እና ይህም እንደካምን መንግስት አይነት፣ ከአባት ወደ ወንድ ልጅ የሚተላለፍ፣ ነበር።
፳፮ ፈርዖንም ጻድቅ ሰው ስለነበረ፣ በህይወቱ ሁሉ በመጀመሪያ ትውልድ አባቶች እንዲሁም በመጀመሪያው ከአባት ወደ ወንድ ልጅ በሚተላለፍበት አገዛዝ፣ እንዲሁም በአዳምም አገዛዝ፣ በኩል፣ እና በምድርና በአስተዋይነት በረከቶች በባረከውና ክህነትን በሚመለከት በረገመው በአባቱ ኖህ የተመሰረተውንም መንግስት ስርዓት አይነት ለመመስረትም በቅንነት በመሞከር፣ መንግስቱን የመሰረተውና ህዝቡን የፈረደው በአስተዋይነትና በፍትሀ ነበር።
፳፯ አሁን፣ ምንም እንኳን ፈርዖኖች ከኖህና በካነምን በኩል ይህ ይገባናል ብለው ቢዋሹምና አባቴንም ወደ ጣኦት አምልኮ ቢወስዱትም፣ ፈርዖን ክህነት መብት ከሌለው ወገን ነበር።
፳፰ ነገር ግን መዛግብቱ በእጄ ላይ ስላረፉና ከእኔም ጋር አሁንም ስላሉ፣ ከዚህ በኋላ፣ ከፍጥረት መጀመሪያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ራሴ ድረስ ያለውን የቅድመ ተከተልን ለመዘርዘር እሞክራለሁ።
፳፱ አሁን፣ የኤልከናኽ ቄስም በመመታት ከሞተ በኋላ፣ ፅኑ ራብም በምድሩ እንደሚመጣ ከላውዴዎን በሚመለከት ለእኔ የተነገሩኝ ነገሮችም በሙሉ እየተሟሉ መጡ።
፴ እንደዚህም ፅኑ ራብም በከላውዴዎ ሀገር በሙሉ ገባ፣ እና አባቴም በረሀብ ምክንያት በጣም ተሰቃየ፣ እና እኔ ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ፣ ህይወቴን ለመውሰድ፣ ላደረጋቸው ጥፋትም ንስሀ ገባ።
፴፩ ነገር ግን የአባቶችን፣ እንዲሁም የፔትርያርኮቹን፣ የክህነት መብትን የሚመለከቱ መዛግብትን ግን ጌታ አምላኬ በእጆቼ ጠበቃቸው፤ ስለዚህ የፍጥረት መጀመሪያ እውቀቶች፣ እና ደግሞም የአለማትና የከዋክብት እውቀቶችም ለአባቶች እንደተገለጹላቸው፣ እኔም እስከዚህ ቀን ድረስ ጠብቄአለሁ፣ እና አንዳንድ እነዚህን ነገሮች በዚህ መዝገብ ላይ ከእኔ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶች ጥቅም ለመጻፍ እሞክራለሁ።